Skip to content
← Daniel

Chapter 5 · Amharic

Daniel

1ንጉሡ፡ብልጣሶር፡ለሺሕ፡መኳንንቶቹ፡ትልቅ፡ግብዣ፡አደረገ፥በሺሑም፡ፊት፡የወይን፡ጠጅ፡ይጠጣ፡ ነበር።

2ብልጣሶርም፡የወይን፡ጠጅ፡በቀመሰ፡ጊዜ፡ንጉሡና፡መኳንንቶቹ፣ሚስቶቹና፡ቁባቶቹ፡ይጠጡባቸው፡ ዘንድ፦አባቴ፡ናቡከደነጾር፡በኢየሩሳሌም፡ከነበረው፡መቅደስ፡ያመጣቸውን፡የወርቁንና፡የብሩን፡ዕቃዎች፡ አምጡ፡ብሎ፡አዘዘ።

3የዚያን፡ጊዜም፡በኢየሩሳሌም፡ከነበረው፡ከእግዚአብሔር፡ቤተ፡መቅደስ፡የመጡትን፡የወርቁን፡ዕቃዎች፡ አመጡ፤ንጉሡና፡መኳንንቶቹም፡ሚስቶቹና፡ቁባቶቹም፡ጠጡባቸው።

4የወይን፡ጠጅም፡እየጠጡ፡ከወርቅና፡ከብር፣ከናስና፡ከብረት፣ከዕንጨትና፡ከድንጋይ፡የተሠሩትን፡ አማልክት፡አመሰገኑ።

5በዚያም፡ሰዓት፡የሰው፡እጅ፡ጣቶች፡ወጥተው፡በንጉሡ፡ቤት፡በተለሰነው፡ግንብ፡ላይ፡በመቅረዙ፡አንጻር፡ ጻፉ፤ንጉሡም፡የሚጽፉትን፡ጣቶች፡አየ።

6የዚያን፡ጊዜም፡የንጉሡ፡ፊት፡ተለወጠበት፥ዐሳቡም፡አስቸገረው፥የወገቡም፡ዥማቶች፡ ተፈቱ፥ጕልበቶቹም፡ተብረከረኩ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

7ንጉሡም፡አስማተኛዎቹንና፡ከለዳውያኑን፣ቃላ፟ተኛዎቹንም፡ያገቡ፡ዘንድ፡በታላቅ፡ድምፅ፡ጮኸ፤ንጉሡም፡ የባቢሎንን፡ጠቢባን፦ይህን፡ጽሕፈት፡ያነበበ፥ፍቺውንም፡ያሳየኝ፡ሐምራዊ፡ግምጃ፡ይለብሳል፥የወርቅም፡ ማርዳ፡በዐንገቱ፡ዙሪያ፡ይኾንለታል፥በመንግሥትም፡ላይ፡ሦስተኛ፡ገዢ፡ይኾናል፡ብሎ፡ተናገረ።

8የዚያን፡ጊዜም፡የንጉሡ፡ጠቢባን፡ዅሉ፡ገቡ፤ነገር፡ግን፥ጽሕፈቱን፡ያነቡ፟፥ፍቺውንም፡ለንጉሡ፡ ያስታውቁ፡ዘንድ፡አልቻሉም።

9ንጉሡም፡ብልጣሶር፡እጅግ፡ደነገጠ፥ፊቱም፡ተለወጠበት፥መኳንንቶቹም፡ተደናገጡ።

10ንግሥቲቱም፡ስለንጉሡና፡ስለመኳንንቱ፡ቃል፡ወደግብዣ፡ቤት፡ገባች፤ንግሥቲቱም፡ተናገረች፥እንዲህም፡ አለች፦ንጉሥ፡ሆይ፥ሺሕ፡ዓመት፡ንገሥ፤ዐሳብኽ፡አያስቸግርኽ፥ፊትኽም፡አይለወጥ።

11የቅዱሳን፡አማልክት፡መንፈስ፡ያለበት፡ሰው፡በመንግሥትኽ፡ውስጥ፡አለ፤በአባትኽም፡ዘመን፡እንደ፡ አማልክት፡ጥበብ፡ያለ፡ጥበብና፡ማስተዋል፡ዕውቀትም፡ተገኘበት፤አባትኽ፡ንጉሡ፡ናቡከደነጾር፡የሕልም፡ ተርጓሚዎችና፡የአስማተኛዎች፣የከለዳውያንና፡የቃላ፟ተኛዎች፡አለቃ፡አደረገው።

12መልካም፡መንፈስ፣ዕውቀትም፣ማስተዋልም፣ሕልምንም፡መተርጐም፥እንቆቅልሽንም፡ መግለጥ፥የተቋጠረውንም፡መፍታት፡ንጉሡ፡ስሙን፡ብልጣሶር፡ብሎ፡በሰየመው፡በዳንኤል፡ዘንድ፡ ተገኝቷልና።አኹንም፡ዳንኤል፡ይጠራ፥ርሱም፡ፍቺውን፡ያሳያል።

13የዚያን፡ጊዜም፡ዳንኤል፡ወደንጉሡ፡ፊት፡ገባ፤ንጉሡም፡ተናገረው፥ዳንኤልንም፡እንዲህ፡ አለው፦ንጉሡ፡አባቴ፡ከይሁዳ፡ከማረካቸው፣ከይሁዳ፡ምርኮኛዎች፡የኾንኽ፡ዳንኤል፡አንተ፡ነኽን፧

14የአማልክት፡መንፈስ፡እንዳለብኽ፥ዕውቀትና፡ማስተዋልም፣መልካምም፡ጥበብ፡እንደ፡ተገኘብኽ፡ስለ፡ አንተ፡ሰምቻለኹ።

15አኹንም፡ይህን፡ጽሕፈት፡ያነቡ፟፡ዘንድ፥ፍቺውንም፡ያስታውቁኝ፡ዘንድ፥ጠቢባንና፡አስማተኛዎች፡ወደ፡ እኔ፡ገብተው፡ነበር፤ነገር፡ግን፥የነገሩን፡ፍቺ፡ያሳዩ፡ዘንድ፡አልቻሉም።

16አንተ፡ግን፡ፍቺን፡ትሰጥ፡ዘንድ፥የተቋጠረንም፡ትፈታ፡ዘንድ፡እንድትችል፡ሰምቻለኹ፤አኹንም፡ ጽሕፈቱን፡ታነብ፟፡ዘንድ፥ፍቺውንም፡ታስታውቀኝ፡ዘንድ፡ብትችል፥ሐምራዊ፡ግምጃ፡ትለብሳለኽ፥የወርቅም፡ ማርዳ፡በዐንገትኽ፡ዙሪያ፡ይኾንልኻል፥አንተም፡በመንግሥት፡ላይ፡ሦስተኛ፡ገዢ፡ትኾናለኽ።

17የዚያን፡ጊዜም፡ዳንኤል፡መለሰ፥በንጉሡም፡ፊት፡እንዲህ፡አለ፦ስጦታኽ፡ለአንተ፡ይኹን፥በረከትኽንም፡ ለሌላ፡ስጥ፤ነገር፡ግን፥ጽሕፈቱን፡ለንጉሡ፡አነባ፟ለኹ፥ፍቺውንም፡አስታውቃለኹ።

18ንጉሥ፡ሆይ፥ልዑል፡አምላክ፡ለአባትኽ፡ለናቡከደነጾር፡መንግሥትንና፡ታላቅነትን፣ክብርንና፡ግርማን፡ ሰጠው።

19ስለሰጠው፡ታላቅነት፡ወገኖችና፡አሕዛብ፣በልዩ፡ልዩም፡ቋንቋ፡የሚናገሩ፡ዅሉ፡በፊቱ፡ይንቀጠቀጡና፡ ይፈሩ፡ነበር፤የፈቀደውን፡ይገድል፥የፈቀደውንም፡በሕይወት፡ያኖር፡ነበር፤የፈቀደውንም፡ያነሣ፥የፈቀደውንም፡ ያዋርድ፡ነበር።

20ልቡ፡ግን፡በታበየ፥በኵራትም፡ያደርግ፡ዘንድ፡መንፈሱ፡በጠነከረ፡ጊዜ፥ከመንግሥቱ፡ዙፋን፡ ተዋረደ፥ክብሩም፡ተለየው።

21ልዑል፡አምላክም፡በሰዎች፡መንግሥት፡ላይ፡እንዲሠለጥን፥የሚወደ፟ውንም፡እንዲሾምበት፡እስኪያውቅ፡ ድረስ፡ከሰው፡ልጆች፡ተይለቶ፡ተሰደደ፤ልቡም፡እንደ፡አውሬ፡ልብ፡ኾነ፥መኖሪያውም፡ከምድረ፡በዳ፡ አህያዎች፡ጋራ፡ነበረ፤እንደ፡በሬ፡ሣር፡በላ፥አካሉም፡በሰማይ፡ጠል፡ረሰረሰ።

22ብልጣሶር፡ሆይ፥አንተ፡ልጁ፡ስትኾን፡ይህን፡ዅሉ፡እያወቅኽ፡በሰማይ፡ጌታ፡ላይ፡ኰራኽ፡እንጂ፡ ልብኽን፡አላዋረድኽም።

23የመቅደሱንም፡ዕቃዎች፡በፊትኽ፡አመጡ፥አንተም፣መኳንንትኽም፣ሚስቶችኽም፣ቁባቶችኽም፡የወይን፡ ጠጅ፡ጠጣችኹባቸው፤ከብርና፡ከወርቅም፣ከናስና፡ከብረትም፣ከዕንጨትና፡ከድንጋይም፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org የተሠሩትን፥የማያዩትንም፥የማይሰሙትንም፥የማያውቁትንም፡አማልክት፡አመሰገንኽ፤ትንፋሽኽንና፡ መንገድኽን፡ዅሉ፡በእጁ፡የያዘውን፡አምላክ፡አላከበርኸውም።

24ስለዚህም፡እነዚህ፡የእጅ፡ጣቶች፡ከርሱ፡ዘንድ፡ተልከዋል፤ይህም፡ጽሕፈት፡ተጽፏል።

25የተጻፈውም፡ጽሕፈት፦ማኔ፡ቴቄል፡ፋሬስ፡ይላል።

26የነገሩም፡ፍቺ፡ይህ፡ነው፤ማኔ ፡ማለት፥እግዚአብሔር፡መንግሥትኽን፡ቈጠረው፥ፈጸመውም፡ማለት፡ ነው።

27ቴቄል ፡ማለት፥በሚዛን፡ተመዘንኽ፥ቀለ፟ኽም፡ተገኘኽ፡ማለት፡ነው።

28ፋሬስ ፡ማለት፥መንግሥትኽ፡ተከፈለ፥ለሜዶንና፡ለፋርስ፡ሰዎችም፡ተሰጠ፡ማለት፡ነው።

29የዚያን፡ጊዜም፡ብልጣሶር፡ለዳንኤል፡ሐምራዊ፡ግምጃ፡እንዲያለብሱት፥የወርቅ፡ማርዳም፡በዐንገቱ፡ዙሪያ፡ እንዲያደርጉለት፡አዘዘ፤በመንግሥትም፡ላይ፡ሦስተኛ፡ገዢ፡እንዲኾን፡ዐዋጅ፡አስነገረ።

30በዚያ፡ሌሊት፡የከለዳውያን፡ንጉሥ፡ብልጣሶር፡ተገደለ።

31ሜዶናዊውም፡ዳርዮስ፡መንግሥቱን፡ወሰደ፤ዕድሜውም፡ስድሳ፡ኹለት፡ዓመት፡ነበረ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source