1ዳርዮስም፡በመንግሥቱ፡ዅሉ፡ዘንድ፡እንዲኾኑ፡መቶ፡ኻያ፡መሳፍንት፡በመንግሥቱ፡ላይ፡ይሾም፡ዘንድ፡ ወደደ።
2መሳፍንቱም፡ሒሳቡን፡ያመጡላቸው፡ዘንድ፥ንጉሡም፡እንዳይጐ፟ዳ፥ሦስት፡አለቃዎች፡በላያቸው፡ አደረገ፤ከነርሱም፡አንደኛው፡ዳንኤል፡ነበረ።
3ዳንኤልም፡መልካም፡መንፈስ፡ስለ፡አለው፥ከአለቃዎችና፡ከመሳፍንት፡በለጠ፤ንጉሡም፡በመንግሥቱ፡ ዅሉ፡ላይ፡ይሾመው፡ዘንድ፡ዐሰበ።
4የዚያን፡ጊዜም፡አለቃዎችና፡መሳፍንቱ፡ስለ፡መንግሥቱ፡በዳንኤል፡ላይ፡ሰበብ፡ይፈልጉ፡ነበር፤ነገር፡ ግን፥የታመነ፡ነበረና፥ስሕተትና፡በደልም፡አልተገኘበትምና፥በርሱ፡ላይ፡ሰበብና፡በደል፡ያገኙበት፡ዘንድ፡ አልቻሉም።
5እነዚያም፡ሰዎች፦ከአምላኩ፡ሕግ፡በቀር፥በዚህ፡በዳንኤል፡ላይ፡ሌላ፡ሰበብ፡አናገኝበትም፡አሉ።
6የዚያን፡ጊዜም፡አለቃዎቹና፡መሳፍንቱ፡ወደ፡ንጉሡ፡ተሰብስበው፡እንዲህ፡አሉት፦ንጉሥ፡ዳርዮስ፡ ሆይ፥ሺሕ፡ዓመት፡ንገሥ።
7የመንግሥቱ፡አለቃዎች፡ዅሉ፣ሹማምቶችና፡መሳፍንት፣አማካሪዎችና፡አዛዦች፦ንጉሥ፡ሆይ፥ከአንተ፡ በቀር፡ማንም፡እስከ፡ሠላሳ፡ቀን፡ድረስ፡ልመና፡ከአምላክ፡ወይም፡ከሰው፡ቢለምን፥በአንበሳዎች፡ጕድጓድ፡ ውስጥ፡ይጣ፟ል፥የሚል፡የንጉሥ፡ሕግና፡ብርቱ፡ትእዛዝ፡ይወጣ፡ዘንድ፡ተማከሩ።
8አኹንም፥ንጉሥ፡ሆይ፥እንደማይለወጠው፡እንደ፡ሜዶንና፡እንደ፡ፋርስ፡ሕግ፥እንዳይለወጥ፡ትእዛዙን፡ አጽና፥ጽሕፈቱንም፡ጻፍ።
9ንጉሡም፡ዳርዮስ፡ጽሕፈቱንና፡ትእዛዙን፡ጻፈ።
10ዳንኤልም፡ጽሕፈቱ፡እንደ፡ተጻፈ፡ባወቀ፡ጊዜ፥ወደ፡ቤቱ፡ገባ፤የዕልፍኙም፡መስኮቶች፡ወደኢየሩሳሌም፡ አንጻር፡ተከፍተው፡ነበር፤ቀድሞም፡ያደርግ፡እንደ፡ነበረ፥በየዕለቱ፡ሦስት፡ጊዜ፡በጕልበቱ፡ተንበርክኮ፡ በአምላኩ፡ፊት፡ጸለየ፥አመሰገነም። 267 ሱር.፥ምናህ፡(ሰፈረ፥ቈጠረ፥ፈጸመ፤ኪ.ወ.ክ.598)። 268 ሱር.፥ትቄል፡(ሰቀለ፥ደለወ፥መዘነ፤ኪ.ወ.ክ.902)። 269 ሱር.፥ፋርሲን፡(ከፊል•ፍራ፟ሽ)። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
11እነዚያም፥ሰዎች፡ተሰብስበው፥ዳንኤል፡በአምላኩ፡ፊት፡ሲጸልይና፡ሲለምን፡አገኙት።
12ወደ፡ንጉሡም፡ቀርበው፥ስለንጉሡ፡ትእዛዝ፦ንጉሥ፡ሆይ፥ከአንተ፡በቀር፡እስከ፡ሠላሳ፡ቀን፡ድረስ፡ ከአምላክ፡ወይም፡ከሰው፡የሚለምን፡ሰው፡ዅሉ፡በአንበሳዎች፡ጕድጓድ፡ውስጥ፡እንዲጣል፡ትእዛዝ፡ አልጻፍኽምን፧አሉት።ንጉሡም፡መልሶ፦ነገሩ፡እንደማይለወጠው፡እንደ፡ሜዶንና፡እንደ፡ፋርስ፡ሕግ፡ እውነት፡ነው፡አላቸው።
13የዚያን፡ጊዜም፡በንጉሡ፡ፊት፡መልሰው፦ንጉሥ፡ሆይ፥ከይሁዳ፡ምርኮኛዎች፡የኾነው፡ዳንኤል፡ በየዕለቱ፡ሦስት፡ጊዜ፡ልመናውን፡ይለምናል፡እንጂ፥አንተንና፡የጻፍኸውን፡ትእዛዝ፡አይቀበልም፡አሉት።
14ንጉሡም፡ይህን፡ቃል፡በሰማ፡ጊዜ፡በጣም፡ዐዘነ፥ያድነውም፡ዘንድ፡ልቡን፡ወደ፡ዳንኤል፡ አደረገ፤ሊያድነውም፡ፀሓይ፡እስኪገባ፡ድረስ፡ደከመ።
15የዚያን፡ጊዜም፡እነዚያ፡ሰዎች፡ወደ፡ንጉሡ፡ተሰብስበው፡ንጉሡን፦ንጉሥ፡ሆይ፥ንጉሡ፡ያጸናው፡ ትእዛዝ፡ወይም፡ሥርዐት፡ይለወጥ፡ዘንድ፡እንዳይገ፟ባ፟፡የሜዶንና፡የፋርስ፡ሕግ፡እንደ፡ኾነ፡ዕወቅ፡አሉት።
16የዚያን፡ጊዜም፡ንጉሡ፡አዘዘ፥ዳንኤልንም፡አምጥተው፡በአንበሳዎች፡ጕድጓድ፡ጣሉት፤ንጉሡም፡ ተናገረ፥ዳንኤልንም፦ዅልጊዜ፡የምታመልከው፡አምላክኽ፡ርሱ፡ያድንኽ፡አለው።
17ድንጋይም፡አምጥተው፡በጕድጓዱ፡አፍ፡ላይ፡ገጠሙበት፤ንጉሡም፡በዳንኤል፡ላይ፡የተደረገው፡ እንዳይለወጥ፡በቀለበቱና፡በመኳንንቱ፡ቀለበት፡አተመው።
18ንጉሡም፡ወደ፡ቤቱ፡ኼደ፥ሳይበላም፡ዐደረ፤መብልም፡አላመጡለትም፥እንቅልፉም፡ከርሱ፡ራቀ።
19በነጋውም፡ንጉሡ፡ማልዶ፡ተነሣ፥ፈጥኖም፡ወዳንበሳዎች፡ጕድጓድ፡ኼደ።
20ወደ፡ጕድጓዱም፡ወደ፡ዳንኤል፡በቀረበ፡ጊዜ፥በሐዘን፡ቃል፡ጠራው፤ንጉሡም፡ ተናገረ፥ዳንኤልንም፦የሕያው፡አምላክ፡ባሪያ፡ዳንኤል፡ሆይ፥ዅልጊዜ፡የምታመልከው፡አምላክኽ፡ ከአንበሳዎች፡ያድንኽ፡ዘንድ፡ችሏልን፧አለው።
21ዳንኤልም፡ንጉሡን፦ንጉሥ፡ሆይ፥ሺሕ፡ዓመት፡ንገሥ።
22በፊቱ፡ቅንነት፡ተገኝቶብኛልና፥ባንተም፡ፊት፡ደግሞ፥ንጉሥ፡ሆይ፥አልበደልኹምና፥አምላኬ፡ መልአኩን፡ልኮ፡የአንበሳዎችን፡አፍ፡ዘጋ፥እነርሱም፡አልጐዱኝም፡አለው።
23የዚያን፡ጊዜም፡ንጉሡ፡እጅግ፡ደስ፡አለው፥ዳንኤልንም፡ከጕድጓዱ፡ያወጡት፡ዘንድ፡አዘዘ፤ዳንኤልም፡ ከጕድጓድ፡ወጣ፥በአምላኩም፡ታምኖ፡ነበርና፥አንዳች፡ጕዳት፡አልተገኘበትም።
24ንጉሡም፡አዘዘ፥ዳንኤልንም፡የከሰሱ፡እነዚያን፡ሰዎች፡አመጧቸው፥እነርሱንና፡ ልጆቻቸውንም፣ሚስቶቻቸውንም፡በአንበሳዎች፡ጕድጓድ፡ጣሏቸው፤ወደጕድጓዱም፡መጨረሻ፡ሳይደርሱ፡ አንበሳዎች፡ያዟቸው፥ዐጥንታቸውንም፡ዅሉ፡ሰባበሩ።
25የዚያን፡ጊዜም፡ንጉሥ፡ዳርዮስ፡በምድር፡ዅሉ፡ላይ፡ወደሚኖሩ፡ወገኖችና፡አሕዛብ፥በልዩ፡ልዩም፡ ቋንቋ፡ወደሚናገሩ፡ዅሉ፡ጻፈ፥እንዲህም፡አለ፦ሰላም፡ይብዛላችኹ።
26በመንግሥቴ፡ግዛት፡ዅሉ፡ያሉ፡ሰዎች፡በዳንኤል፡አምላክ፡ፊት፡እንዲፈሩና፡እንዲንቀጠቀጡ፡ አዝዣለኹ፤ርሱ፡ሕያው፡አምላክ፡ለዘለዓለም፡የሚኖር፡ነውና፤መንግሥቱም፡የማይጠፋ፡ነው፥ግዛቱም፡እስከ፡ መጨረሻ፡ድረስ፡ይኖራል።
27ያድናል፥ይታደግማል፤በሰማይና፡በምድርም፡ተኣምራትንና፡ድንቅን፡ይሠራል፤ዳንኤልንም፡ከአንበሳዎች፡ አፍ፡አድኖታል።
28ይህም፡ዳንኤል፡በዳርዮስ፡መንግሥትና፡በፋርሳዊው፡በቂሮስ፡መንግሥት፡ኑሮው፡ተቃናለት።