Skip to content
← Daniel

Chapter 8 · Amharic

Daniel

1በመዠመሪያ፡ከተገለጠልኝ፡ራእይ፡በዃላ፥ንጉሡ፡ብልጣሶር፡በነገሠ፡በሦስተኛው፡ዓመት፥ለእኔ፡ ለዳንኤል፡ራእይ፡ተገለጠልኝ።

2በራእዩም፡አየኹ፤ባየኹም፡ጊዜ፡በዔላም፡አውራጃ፡ባለው፡በሱሳ፡ግንብ፡ነበርኹ፤በራእዩም፡አየኹ፡ በኡባል፡ወንዝም፡አጠገብ፡ነበርኹ።

3ዐይኔን፡አንሥቼ፡አየኹ፤እንሆም፥ኹለት፡ቀንዶች፡የነበሩት፡አንድ፡አውራ፡በግ፡በወንዙ፡ፊት፡ቆሞ፡ ነበር፥ኹለቱም፡ቀንዶቹ፡ከፍ፡ከፍ፡ይሉ፡ነበር፤አንዱ፡ግን፡ከኹለተኛው፡ከፍ፡ያለ፡ነበረ፥ታላቁም፡ወደ፡ ዃላው፡ወጥቶ፡ነበር።

4አውራውም፡በግ፡ወደ፡ምዕራብ፡ወደ፡ሰሜንም፡ወደ፡ደቡብም፡በቀንዱ፡ሲጐሽም፡አየኹ፤አራዊትም፡ ዅሉ፡ይቋቋሙት፡ዘንድ፡አልቻሉም፥ከእጁም፡የሚያድን፡አልነበረም፤እንደ፡ፈቃዱም፡አደረገ፥ራሱንም፡ ታላቅ፡አደረገ።

5እኔም፡ስመለከት፥እንሆ፥ከምዕራብ፡ወገን፡አንድ፡አውራ፡ፍየል፡በምድር፡ዅሉ፡ፊት፡ላይ፡ ወጣ፥ምድርንም፡አልነካም፤ለፍየሉም፡በዐይኖቹ፡መካከል፡አንድ፡ታላቅ፡ቀንድ፡ነበረው።

6ኹለትም፡ቀንድ፡ወዳለው፡በወንዝም፡ፊት፡ቆሞ፡ወዳየኹት፡አውራ፡በግ፡መጣ፥በኀይሉም፡ቍጣ፡ ፈጥኖ፡ወደ፡ርሱ፡ሮጠ።

7ወደ፡አውራውም፡በግ፡ሲቀርብ፡አየኹት፤ርሱም፡ተመረረበት፥አውራውንም፡በግ፡መታ፥ኹለቱንም፡ ቀንዶች፡ሰበረ፤አውራውም፡በግ፡ሊቋቋመው፡ኀይል፡አልነበረውም፥ርሱም፡በምድር፡ላይ፡ጥሎ፡ ረገጠው፤አውራውንም፡በግ፡ከእጁ፡ያድነው፡ዘንድ፡የሚችል፡አልነበረም። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

8አውራውም፡ፍየል፡ራሱን፡እጅግ፡ታላቅ፡አደረገ፤በበረታም፡ጊዜ፡ታላቁ፡ቀንዱ፡ተሰበረ፥ወደ፡አራቱም፡ የሰማይ፡ነፋሳት፡የሚመለከቱ፡አራት፡ቀንዶች፡ከበታቹ፡ወጡ።

9ከነርሱም፡ከአንደኛው፡አንድ፡ታናሽ፡ቀንድ፡ወጣ፥ወደ፡ደቡብም፡ወደ፡ምሥራቅም፡ወደ፡መልካሚቱም፡ ምድር፡እጅግ፡ከፍ፡አለ።

10እስከሰማይም፡ሰራዊት፡ድረስ፡ከፍ፡አለ፤ከሰራዊትና፡ከከዋክብትም፡ዐያሌዎችን፡ወደ፡ምድር፡ ጣለ፥ረገጣቸውም።

11እስከሰራዊትም፡አለቃ፡ድረስ፡ራሱን፡ታላቅ፡አደረገ፤ከርሱም፡የተነሣ፡የዘወትሩ፡መሥዋዕት፡ ተሻረ፥የመቅደሱም፡ስፍራ፡ፈረሰ።

12ሰራዊቱም፡ከኀጢአት፡የተነሣ፡ከዘወትሩ፡መሥዋዕት፡ጋራ፡ተሰጠው፤ርሱም፡እውነትን፡ወደ፡ምድሩ፡ ጣለ፥አደረገም፡ተከናወነም።

13ከቅዱሳኑም፡አንዱ፡ሲናገር፡ሰማኹ፤ለተናገረው፡ለቅዱሱም፡ኹለተኛው፡ቅዱስ፦ስለዘወትሩ፡ መሥዋዕት፥መቅደሱና፡ሰራዊቱም፡ይረገጡ፡ዘንድ፡ስለሚሰጥና፡ስለሚያጠፋ፡ኀጢአት፡የኾነው፡ራእይ፡እስከ፡ መቼ፡ይኾናል፧አለው።

14ርሱም፦እስከ፡ኹለት፡ሺሕ፡ሦስት፡መቶ፡ማታና፡ጧት፡ድረስ፡ነው፤ከዚያም፡በዃላ፡መቅደሱ፡ ይነጻል፡አለኝ።

15እኔም፡ዳንኤል፡ራእዩን፡ባየኹ፡ጊዜ፡ማስተዋሉን፡ፈለግኹ፤እንሆም፥የሰው፡ምስያ፡በፊቴ፡ቆሞ፡ነበር።

16በኡባልም፡ወንዝ፡መካከል፦ገብርኤል ፡ሆይ፥ራእዩን፡ለዚህ፡ሰው፡አስታውቀው፡ብሎ፡የሚጮኸውን፡ የሰውን፡ድምፅ፡ሰማኹ።

17እኔም፡ወደ፡ቆምኹበት፡ቀረበ፤በመጣም፡ጊዜ፡ፈርቼ፡በግንባሬ፡ተደፋኹ፤ርሱም፦የሰው፡ልጅ፡ ሆይ፥ራእዩ፡ለፍጻሜ፡ዘመን፡እንደ፡ኾነ፡አስተውል፡አለኝ።

18ሲናገረኝም፡ደንግጬ፡በምድር፡ላይ፡በግንባሬ፡ተደፋኹ፤ርሱም፡ዳሰሰኝ፡ቀጥ፡አድርጎም፡አቆመኝ።

19እንዲህም፡አለኝ፦እንሆ፥በመቅሠፍቱ፡በመጨረሻ፡ዘመን፡የሚኾነውን፡አስታውቅኻለኹ፤ይህ፡ ለተወሰነው፡ለፍጻሜ፡ዘመን፡ነውና።

20ባየኸው፡በአውራው፡በግ፡ላይ፡የነበሩ፡ኹለቱ፡ቀንዶች፡እነርሱ፡የሜዶንና፡የፋርስ፡ነገሥታት፡ናቸው።

21አውራውም፡ፍየል፡የግሪክ፡ንጉሥ፡ነው፤በዐይኖቹም፡መካከል፡ያለው፡ታላቁ፡ቀንድ፡መዠመሪያው፡ ንጉሥ፡ነው።

22ርሱም፡በተሰበረ፡ጊዜ፡በርሱ፡ፋንታ፡አራቱ፡እንደ፡ተነሡ፥እንዲሁ፡ከወገኑ፡አራት፡መንግሥታት፡ ይነሣሉ፥ነገር፡ግን፥በኀይል፡አይተካከሉትም።

23በመንግሥታቸውም፡መጨረሻ፥ኀጢአታቸው፡በተሞላች፡ጊዜ፥እንቆቅልሽን፡የሚያስተውል፡ፊተ፡ጨካኝ፡ ንጉሥ፡ይነሣል።

24ኀይሉም፡ይበረታል፥ነገር፡ግን፥በራሱ፡ኀይል፡አይደለም፤በድንቅም፡ ያጠፋል፥ያደርግማል፥ይከናወንማል፤ኀያላንንና፡የቅዱሳንን፡ሕዝብ፡ያጠፋል።

25በመታለሉ፡ተንኰልን፡በእጁ፡ያከናውናል፤በልቡም፡ይታበያል፥ታምነውም፡የሚኖሩትን፡ብዙዎችን፡ ያጠፋል፤በአለቃዎቹም፡አለቃ፡ላይ፡ይቋቋማል፤ያለ፡እጅም፡ይሰበራል።

26የተነገረውም፡የማታውና፡የጧቱ፡ራእይ፡እውነተኛ፡ነው፤ነገር፡ግን፥ከብዙ፡ዘመን፡በዃላ፡ስለሚኾን፡ ራእዩን፡ዝጋ።

27እኔም፡ዳንኤል፡ተኛኹ፥ዐያሌም፡ቀን፡ታመምኹ፤ከዚያም፡በዃላ፡ተነሥቼ፡የንጉሡን፡ሥራ፡እሠራ፡ 270 ዕብ.፥ጋብሪኤል፡(ገብረ፡እግዚእ•የጌታ፡አገልጋይ)። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ነበር፤ስለ፡ራእዩም፡አደንቅ፡ነበር፥የሚያስተውለው፡ግን፡አልነበረም።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source