Skip to content
← Esther

Chapter 4 · Amharic

Esther

1መርዶክዮስም፡የተደረገውን፡ዅሉ፡ባወቀ፡ጊዜ፡ልብሱን፡ቀደደ፥ማቅም፡ለበሰ፡ዐመድም፡ ነሰነሰ፥ወደከተማዪቱም፡መካከል፡ወጣ፥ታላቅም፡የመረረ፡ጩኸት፡ጮኸ።

2ማቅም፡ለብሶ፡በንጉሥ፡በር፡መግባት፡አይገ፟ባ፟ም፡ነበርና፥እስከንጉሡ፡በር፡አቅራቢያ፡መጣ።

3የንጉሡም፡ትእዛዝና፡ዐዋጅ፡በደረሰበት፡አገር፡ዅሉ፡በአይሁድ፡ላይ፡ታላቅ፡ሐዘንና፡ጾም፡ልቅሶና፡ ዋይታም፡ኾነ፡ብዙዎችም፡ማቅና፡ዐመድ፡አነጠፉ።

4የአስቴርም፡ደንገጥሮቿና፡ጃን፡ደረባዎቿ፡መጥተው፡ነገሯት፥ንግሥቲቱም፡እጅግ፡ዐዘነች፤ማቁንም፡ ለውጦ፡ልብስ፡ይለብስ፡ዘንድ፡ለመርዶክዮስ፡ሰደደችለት፤ርሱ፡ግን፡አልተቀበለም።

5አስቴርም፡ያገለግላት፡ዘንድ፡ንጉሡ፡ያቆመውን፡አክራትዮስ ን፡ጠራች፥ርሱም፡ከጃን፡ደረባዎች፡አንዱ፡ ነበረ፤ርሷም፡ይህ፡ነገር፡ምንና፡ምን፡እንደ፡ኾነ፡ያስታውቃት፡ዘንድ፡ወደ፡መርዶክዮስ፡እንዲኼድ፡ አዘዘችው። 255 ፋር.፡ሀታክ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

6አክራትዮስም፡በንጉሥ፡በር፡ፊት፡ወደነበረችው፡ወደከተማዪቱ፡አደባባይ፡ወደ፡መርዶክዮስ፡ወጣ።

7መርዶክዮስም፡የተደረገውን፡ዅሉ፥አይሁድንም፡ለማጥፋት፡ሐማ፡በንጉሡ፡ግምጃ፡ቤት፡ይመዝን፡ዘንድ፡ የተናገረውን፡የብሩን፡ቍጥር፡ነገረው።

8ለአስቴርም፡እንዲያሳያት፡ለመጥፋታቸው፡በሱሳ፡የተነገረውን፡የዐዋጁን፡ጽሕፈት፡ቅጅ፡ሰጠው፤ወደ፡ ንጉሡም፡ገብታ፡ስለ፡ሕዝቧ፡ትለምነውና፡ትማልደው፡ዘንድ፡እንዲነግራትና፡እንዲያዛ፟ት፡ነገረው።

9አክራትዮስም፡መጥቶ፡የመርዶክዮስን፡ቃል፡ለአስቴር፡ነገራት።

10አስቴርም፡አክራትዮስን፡ተናገረችው፥ለመርዶክዮስም፡እንዲህ፡የሚል፡መልእክት፡ሰጠችው፦

11የንጉሡ፡ባሪያዎችና፡በአገሮችም፡የሚኖሩ፡ሕዝብ፡ዅሉ፡ወንድ፡ወይም፡ሴት፡ቢኾን፡ሳይጠራ፡ወደ፡ ንጉሡ፡ወደውስጠኛው፡ወለል፡የሚገባ፡ዅሉ፥በሕይወት፡ይኖር፡ዘንድ፡ንጉሡ፡የወርቁን፡ዘንግ፡ካልዘረጋለት፡ በቀር፥ርሱ፡ይሞት፡ዘንድ፡ሕግ፡እንዳለ፡ያውቃሉ፤እኔ፡ግን፡ወደ፡ንጉሡ፡ለመግባት፡ይህን፡ሠላሳውን፡ ቀን፡አልተጠራኹም።

12አክራትዮስም፡የአስቴርን፡ቃል፡ለመርዶክዮስ፡ነገረው።

13መርዶክዮስም፡አክራትዮስን፦ኺድና፡ለአስቴር፡እንዲህ፡በላት፡አለው፦አንቺ፦በንጉሥ፡ቤት፡ስለ፡ ኾንኹ፡ከአይሁድ፡ዅሉ፡ይልቅ፡እድናለኹ፡ብለሽ፡በልብሽ፡አታስቢ።

14በዚህ፡ጊዜ፡ቸል፡ብትዪ፡ዕረፍትና፡መዳን፡ለአይሁድ፡ከሌላ፡ስፍራ፡ይኾንላቸዋል፥አንቺና፡የአባትሽ፡ ቤት፡ግን፡ትጠፋላችኹ፤ደግሞስ፡ወደ፡መንግሥት፡የመጣሽው፡እንደዚህ፡ላለው፡ጊዜ፡እንደ፡ኾነ፡ማን፡ ያውቃል፧

15አስቴርም፡እንዲህ፡ብሎ፡ለመርዶክዮስ፡እንዲመልስ፡አዘዘችው።

16ኼደኽ፡በሱሳ፡ያሉትን፡አይሁድ፡ዅሉ፡ሰብስብ፥ለኔም፡ጹሙ፤ሦስት፡ቀን፡ሌሊቱንና፡ቀኑን፡ አትብሉም፥አትጠጡም፤እኔና፡ደንገጥሮቼ፡ደግሞ፡እንዲሁ፡እንጾማለን፤ምንም፡እንኳ፡ያለሕግ፡ቢኾን፡ወደ፡ ንጉሡ፡እገባለኹ፤ብጠፋም፡እጠፋለኹ።

17መርዶክዮስም፡ኼዶ፡አስቴር፡እንዳዘዘችው፡ዅሉ፡አደረገ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source