1በሦስተኛውም፡ቀን፡አስቴር፡ልብሰ፡መንግሥቷን፡ለብሳ፡በንጉሡ፡ቤት፡ትይዩ፡በንጉሡ፡ቤት፡ በውስጠኛው፡ወለል፡ቆመች፤ንጉሡም፡በቤቱ፡መግቢያ፡ትይዩ፡በቤተ፡መንግሥቱ፡ውስጥ፡በንጉሡ፡ዙፋን፡ ላይ፡ተቀምጦ፡ነበር።
2ንጉሡም፡ንግሥቲቱ፡አስቴር፡በወለሉ፡ላይ፡ቆማ፡ባየ፡ጊዜ፡በዐይኑ፡ሞገስ፡አገኘች፤ንጉሡም፡በእጁ፡ የነበረውን፡የወርቁን፡ዘንግ፡ለአስቴር፡ዘረጋላት፤አስቴርም፡ቀርባ፡የዘንጉን፡ጫፍ፡ነካች።
3ንጉሡም፦ንግሥት፡አስቴር፡ሆይ፥የምትለምኚኝ፡ምንድር፡ነው፧የምትሺውስ፡ምንድር፡ነው፧እስከ፡ መንግሥቴ፡እኩሌታ፡እንኳ፡ቢኾን፡ይሰጥሻል፡አላት።
4አስቴርም፦ለንጉሡ፡መልካም፡ኾኖ፡ቢታይ፡ንጉሡ፡ወዳዘጋጀኹለት፡ግብዣ፡ከሐማ፡ጋራ፡ዛሬ፡ይምጣ፡ አለች።
5ንጉሡም፦አስቴር፡እንዳለች፡ይደረግ፡ዘንድ፡ሐማን፡አስቸኵሉት፡አለ።ንጉሡና፡ሐማ፡አስቴር፡ ወዳዘጋጀችው፡ግብዣ፡መጡ።
6ንጉሡም፡በወይኑ፡ጠጅ፡ግብዣ፡ሳለ፡አስቴርን፦የምትሺው፡ምንድር፡ነው፧ይሰጥሻል፤ልመናሽስ፡ ምንድር፡ነው፧እስከ፡መንግሥቴ፡እኩሌታ፡እንኳ፡ቢኾን፡ይደረግልሻል፡አላት።
7አስቴርም፡መልሳ፦ልመናዬና፡የምሻው፡ነገር፡ይህ፡ነው፤ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
8በንጉሡ፡ዘንድ፡ሞገስ፡አግኝቼ፡እንደ፡ኾነ፥ልመናዬንም፡ይፈጽም፡ዘንድና፡የምሻውን፡ያደርግ፡ዘንድ፡ ንጉሡ፡ደስ፡ቢያሠኘው፥ንጉሡና፡ሐማ፡ወደማዘጋጅላቸው፡ግብዣ፡ይምጡ፤እንደ፡ንጉሡም፡ነገር፡ነገ፡ አደርጋለኹ፡አለች።
9በዚያም፡ቀን፡ሐማ፡ደስ፡ብሎት፡በልቡም፡ተደስቶ፡ወጣ፤ነገር፡ግን፥መርዶክዮስ፡በንጉሡ፡በር፡ ያለመነሣትና፡ያለመናወጥ፡ተቀምጦ፡ባየ፡ጊዜ፡ሐማ፡በመርዶክዮስ፡ላይ፡እጅግ፡ተቈጣ።
10ሐማ፡ግን፡ታግሦ፡ወደ፡ቤቱ፡ኼደ፤ልኮም፡ወዳጆቹንና፡ሚስቱን፡ዞሳራን፡አስጠራ።
11ሐማም፡የሀብቱን፡ክብርና፡የልጆቹን፡ብዛት፥ንጉሡም፡ያከበረበትን፡ክብር፡ዅሉ፥በንጉሡም፡ዐዛውንትና፡ ባሪያዎች፡ላይ፡ከፍ፡ከፍ፡እንዳደረገው፡አጫወታቸው።
12ሐማም፦ንግሥቲቱ፡አስቴር፡ወዳዘጋጀችው፡ግብዣ፡ከእኔ፡በቀር፡ከንጉሡ፡ጋራ፡ማንንም፡ አልጠራችም፤ደግሞ፡ነገ፡ከንጉሡ፡ጋራ፡ወደ፡ርሷ፡ተጠርቻለኹ።
13ነገር፡ግን፥አይሁዳዊው፡መርዶክዮስ፡በንጉሡ፡በር፡ተቀምጦ፡ካየኹ፡ይህ፡ዅሉ፡ለእኔ፡ምንም፡ምን፡ አይጠቅምም፡አለ።
14ሚስቱም፡ዞሳራና፡ወዳጆቹ፡ዅሉ፦ቁመቱ፡ዐምሳ፡ክንድ፡የኾነ፡ግንድ፡ይደረግ፥ነገም፡መርዶክዮስ፡ ይሰቀልበት፡ዘንድ፡ለንጉሡ፡ተናገር፤ደስም፡ብሎኽ፡ከንጉሡ፡ጋራ፡ወደ፡ግብዣው፡ግባ፡ አሉት።ነገራቸውም፡ሐማን፡ደስ፡አሠኘው፥ግንዱንም፡አስደረገ።