Skip to content
← Esther

Chapter 6 · Amharic

Esther

1በዚያም፡ሌሊት፡እንቅልፍ፡ከንጉሡ፡ሸሸ፤የዘመኑንም፡ታሪክ፡መጽሐፍ፡ያመጡ፡ዘንድ፡ አዘዘ፥በንጉሡም፡ፊት፡ተነበበ።

2ደጁንም፡ከሚጠብቁት፡ከንጉሡ፡ጃን፡ደረባዎች፡ኹለቱ፡ገበታና፡ታራ፡እጃቸውን፡በንጉሡ፡በአርጤክስስ፡ ላይ፡ያነሡ፡ዘንድ፡እንደ፡ፈለጉ፥መርዶክዮስ፡እንደ፡ነገረው፡ተጽፎ፡ተገኘ።

3ንጉሡም፦ስለዚህ፡ነገር፡ለመርዶክዮስ፡ምን፡ክብርና፡በጎነት፡ተደረገለት፧አለ።ንጉሡንም፡የሚያገለግሉ፡ ብላቴናዎች።ምንም፡አልተደረገለትም፡አሉት።

4ንጉሡም፦በአዳራሹ፡ማን፡አለ፧አለ።ሐማም፡ባዘጋጀው፡ግንድ፡ላይ፡መርዶክዮስን፡ለማሰቀል፡ለንጉሡ፡ ይናገር፡ዘንድ፡ወደንጉሡ፡ቤት፡ወደውጭው፡አዳራሽ፡ገብቶ፡ነበር።

5የንጉሡም፡ብላቴናዎች፦እንሆ፥ሐማ፡በአዳራሹ፡ቆሟል፡አሉት።ንጉሡም፦ይግባ፡አለ።

6ሐማም፡ገባ፤ንጉሡም፦ንጉሡ፡ሊያከብረው፡ለሚወደ፟ው፡ሰው፡ምን፡ይደረግለታል፧አለው።ሐማም፡ በልቡ።ንጉሡ፡ከእኔ፡ይልቅ፡ማንን፡ያከብር፡ዘንድ፡ይወዳ፟ል፧አለ።

7ሐማም፡ንጉሡን፡እንዲህ፡አለው፦ንጉሡ፡ያከብረው፡ዘንድ፡ለሚወደ፟ው፡ሰው፡እንዲህ፡ይደረግ፤

8ንጉሡ፡የለበሰው፡የክብር፡ልብስ፥ንጉሡም፡የተቀመጠበት፡ፈረስ፡ይምጣለት፥የንጉሡም፡ዘውድ፡በራሱ፡ ላይ፡ይደረግ፤

9ልብሱንና፡ፈረሱንም፡ከንጉሡ፡ዐዛውንት፡በዋነኛው፡እጅ፡ያስረክቡት፤ንጉሡም፡ያከብረው፡ዘንድ፡ የሚወደ፟ውን፡ሰው፡ያልብሱት፤በፈረሱም፡ላይ፡አስቀምጠውት፡በከተማዪቱ፡አደባባይ፡ ያሳልፉት፤በፊቱም፦ንጉሡ፡ያከብረው፡ዘንድ፡ለሚወደ፟ው፡ሰው፡እንዲህ፡ይደረግለታል፡ተብሎ፡ዐዋጅ፡ ይነገር።

10ንጉሡም፡ሐማን፦ፍጠን፥እንደ፡ተናገርኸውም፡ልብሱንና፡ፈረሱን፡ውሰድ፤በንጉሡም፡በር፡ ለሚቀመጠው፡አይሁዳዊ፡ለመርዶክዮስ፡እንዲሁ፡አድርግለት፤ከተናገርኸውም፡ዅሉ፡ምንም፡አይቅር፡አለው።

11ሐማም፡ልብሱንና፡ፈረሱን፡ወሰደ፥መርዶክዮስንም፡አለበሰው፥በፈረሱም፡ላይ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org አስቀመጠው፥በከተማዪቱም፡አደባባይ፡በፊቱ፡አሳለፈው።በፊቱም፦ንጉሡ፡ያከብረው፡ዘንድ፡ለሚወደ፟ው፡ ሰው፡እንዲህ፡ይደረግለታል፡ብሎ፡ዐዋጅ፡ነገረ።

12መርዶክዮስም፡ወደንጉሡ፡በር፡ተመለሰ።ሐማ፡ግን፡ዐዝኖና፡ራሱን፡ተከናንቦ፡ቸኵሎ፡ወደ፡ቤቱ፡ኼደ።

13ሐማም፡ለሚስቱ፡ለዞሳራና፡ለወዳጆቹ፡ዅሉ፡ያገኘውን፡ዅሉ፡አጫወታቸው።ጥበበኛዎቹና፡ሚስቱ፡ ዞሳራም፦በፊቱ፡መውደቅ፡የዠመርኽለት፡መርዶክዮስ፡ከአይሁድ፡ወገን፡የኾነ፡እንደ፡ኾነ፡በፊቱ፡ፈጽሞ፡ ትወድቃለኽ፡እንጂ፡አታሸንፈውም፡አሉት።

14እነርሱም፡ሲናገሩት፡ሳሉ፥እንሆ፥የንጉሡ፡ጃን፡ደረባዎች፡መጡ፥አስቴርም፡ወዳዘጋጀችው፡ግብዣ፡ ይመጣ፡ዘንድ፡ሐማን፡አስቸኰሉት።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source