1እኔም፡አየኹ፥እንሆም፥በኪሩቤል፡ራስ፡ላይ፡ባለው፡ጠፈር፡በላያቸው፡እንደ፡ሰንፔር፡ድንጋይ፡ያለ፡ እንደ፡ዙፋን፡የሚመስል፡መልክ፡ተገለጠ።
2በፍታም፡የለበሰውን፡ሰው፦በመንኰራኵሮች፡መካከል፡ከኪሩብ፡በታች፡ግባ፥ከኪሩቤልም፡መካከል፡ ካለው፡እሳት፡ፍም፡እጆችኽን፡ሙላ፦በከተማዪቱም፡ላይ፡በትናት፡ብሎ፡ተናገረው።እኔም፡እያየኹ፡ገባ።
3ሰውዬውም፡ሲገባ፡ኪሩቤል፡በቤቱ፡ቀኝ፡በኩል፡ቆመው፡ነበር፥ደመናውም፡ውስጠኛውን፡አደባባይ፡ሞላ።
4የእግዚአብሔር፡ክብርም፡ከኪሩቤል፡ወጥቶ፡በቤቱ፡መድረክ፡ላይ፡ቆመ፤ቤቱም፡በደመናው፡ ተሞላ፥አደባባዩም፡በእግዚአብሔር፡ክብር፡ጸዳል፡ተሞላ።
5ዅሉንም፡የሚችል፡አምላክ፡እንደሚናገረው፡ያለ፡ድምፅ፡እንዲሁ፡የኪሩቤል፡ክንፎች፡ድምፅ፡እስከ፡ ውጭው፡አደባባይ፡ድረስ፡ተሰማ።
6በፍታም፡የለበሰውን፡ሰው፦ከመንኰራኵሮች፡ከኪሩቤል፡መካከል፡እሳት፡ውሰድ፡ብሎ፡ባዘዘው፡ጊዜ፡ ርሱ፡ገብቶ፡ባንድ፡መንኰራኵር፡አጠገብ፡ቆመ።
7ኪሩብም፡ከኪሩቤል፡መካከል፡እጁን፡በኪሩቤል፡መካከል፡ወዳለው፡እሳት፡ዘርግቶ፡ከዚያ፡ ወሰደ፥በፍታም፡በለበሰው፡ሰው፡እጅ፡አኖረው፤ርሱም፡ይዞ፡ወጣ።
8በኪሩቤልም፡ከክንፎቻቸው፡በታች፡የሰው፡እጅን፡መሳይ፡ታየ።
9እኔም፡አየኹ፥እንሆም፥በኪሩቤል፡አጠገብ፡አራት፡መንኰራኵሮች፡ነበሩ፤አንዱ፡መንኰራኵር፡በአንዱ፡ ኪሩብ፥አንዱ፡መንኰራኵር፡በአንዱ፡ኪሩብ፡አጠገብ፡ነበረ።የመንኰራኵሮቹም፡መልክ፡እንደ፡ቢረሌ፡ ድንጋይ፡ነበረ።
10የአራቱም፡መልክ፡አንድ፡ይመስል፡ነበር፥መልካቸውም፡በመንኰራኵር፡ውስጥ፡እንዳለ፡መንኰራኵር፡ ነበረ።
11ሲኼዱም፡በአራቱ፡ጐድናቸው፡ይኼዱ፡ነበር፥ሲኼዱም፡አይገላመጡም፡ነበር፥ራሱ፡ወደምታመለክትበት፡ ስፍራ፡ወደዚያ፡ይከተሉ፡ነበር፤ሲኼዱም፡አይገላመጡም፡ነበር።
12ገላቸውም፡ዅሉ፣ዠርባቸውም፣እጃቸውም፣ክንፋቸውም፣መንኰራኵሮቹም፥ለአራቱ፡የነበሩ፡ መንኰራኵሮች፥በዙሪያቸው፡ዐይኖች፡ተሞልተው፡ነበር።
13መንኰራኵሮችም፡እኔ፡እየሰማኹ፡ጌልጌል፡ተብለው፡ተጠሩ።
14ለያንዳንዱም፡አራት፡አራት፡ፊት፡ነበሩት፤አንደኛው፡ፊት፡የኪሩብ፡ፊት፥ኹለተኛውም፡የሰው፡ ፊት፥ሦስተኛው፡የአንበሳ፡ፊት፥አራተኛውም፡የንስር፡ፊት፡ነበረ።
15ኪሩቤልም፡ከፍ፡ከፍ፡አሉ፤ይህ፡በኮቦር፡ወንዝ፡ያየኹት፡እንስሳ፡ነው።
16ኪሩቤልም፡ሲኼዱ፡መንኰራኵሮቹ፡በአጠገባቸው፡ይኼዱ፡ነበር፤ኪሩቤልም፡ከምድር፡ከፍ፡ከፍ፡ይሉ፡ ዘንድ፡ክንፎቻቸውን፡ሲዘረጉ፡መንኰራኵሮች፡ደግሞ፡ከአጠገባቸው፡ፈቀቅ፡አይሉም፡ነበር።
17ሕይወት፡ያላቸው፡የእንስሳዎች፡መንፈስ፡በመንኰራኵሮች፡ውስጥ፡ነበረና፡እነዚህ፡ሲቆሙ፡እነዚያ፡ ይቆሙ፡ነበር፥እነዚህም፡ከፍ፡ከፍ፡ሲሉ፡እነዚያ፡ከነርሱ፡ጋራ፡ከፍ፡ከፍ፡ይሉ፡ነበር።
18የእግዚአብሔርም፡ክብር፡ከቤቱ፡መድረክ፡ላይ፡ወጥቶ፡በኪሩቤል፡ላይ፡ቆመ።
19ኪሩቤልም፡ክንፎቻቸውን፡ዘረጉ፡እኔም፡እያየኹ፡ከምድር፡ከፍ፡ከፍ፡አሉ፤በወጡም፡ጊዜ፡ መንኰራኵሮች፡በአጠገባቸው፡ነበሩ፤በእግዚአብሔርም፡ቤት፡በምሥራቁ፡በር፡መግቢያ፡ቆሙ፥የእስራኤልም፡ አምላክ፡ክብር፡በላያቸው፡ላይ፡ነበረ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
20ይህ፡በኮበር፡ወንዝ፡ከእስራኤል፡አምላክ፡በታች፡ያየኹት፡እንስሳ፡ነው፥ኪሩቤልም፡እንደ፡ነበሩ፡ አስተዋልኹ።
21ለያንዳንዱ፡አራት፡አራት፡ፊት፥ለያንዳንዱም፡አራት፡አራት፡ክንፍ፡ነበሩት፥የሰውም፡እጅ፡አምሳያ፡ ከክንፎቻቸው፡በታች፡ነበረ።
22ፊቶቻቸውም፡በኮቦር፡ወንዝ፡ያየዃቸውን፡ፊቶች፡ይመስሉ፡ነበር፤እነርሱና፡መልካቸውም፡እንዲሁ፡ ነበረ፤እያንዳንዱም፡አቅንቶ፡ወደ፡ፊት፡ይኼድ፡ነበር።