1ርሱም፦እያንዳንዳቸው፡የሚያጠፋ፡መሣሪያን፡በእጃቸው፡ይዘው፡ከተማዪቱን፡የሚቀሥፉ፡ይቅረቡ፡ብሎ፡ በታላቅ፡ድምፅ፡በዦሮዬ፡ጮኸ።
2እንሆም፥እያንዳንዳቸው፡አጥፊውን፡መሣሪያ፡በእጃቸው፡ይዘው፡ስድስት፡ሰዎች፡ወደ፡ሰሜን፡ ከሚመለከተው፡ከላይኛው፡በር፡መንገድ፡መጡ፤በመካከላቸውም፡የበፍታ፡ልብስ፡የለበሰ፡የጸሓፊም፡ቀለም፡ ቀንድ፡በወገቡ፡የያዘ፡አንድ፡ሰው፡ነበረ።እነርሱም፡ገብተው፡በናሱ፡መሠዊያ፡አጠገብ፡ቆሙ።
3የእስራኤልም፡አምላክ፡ክብር፡በበላዩ፡ከነበረበት፡ኪሩብ፡ተነሥቶ፡ወደቤቱ፡መድረክ፡ኼዶ፡ነበር፤በፍታም፡ የለበሰውን፡የጸሓፊውንም፡ቀለም፡ቀንድ፡በወገቡ፡የያዘውን፡ሰው፡ጠራ።
4እግዚአብሔርም፦በከተማዪቱ፡በኢየሩሳሌም፡መካከል፡ዕለፍ፥በመካከሏም፡ስለ፡ተሠራው፡ርኵሰት፡ዅሉ፡ በሚያለቅሱና፡በሚተክዙ፡ሰዎች፡ግንባር፡ላይ፡ምልክት፡ጻፍ፡አለው።
5እኔም፡እየሰማኹ፡ለሌላዎቹ፦ርሱን፡ተከትላችኹ፡በከተማዪቱ፡መካከል፡ዕለፉ፡ግደሉም፤ዐይናችኹ፡ አይራራ፥አትዘኑም፤
6ሽማግሌውንና፡ጐበዙን፡ቈንዦዪቱንም፡ሕፃናቶቹንና፡ሴቶቹን፡ፈጽማችኹ፡ግደሉ፤ነገር፡ግን፥ምልክቱ፡ ወዳለበት፡ሰው፡ዅሉ፡አትቅረቡ፤በመቅደሴም፡ዠምሩ፡አላቸው።በቤቱም፡አንጻር፡ባሉ፡ሽማግሌዎች፡ ዠመሩ።
7ርሱም፦ቤቱን፡አርክሱ፥በተገደሉትም፡ሰዎች፡አደባባዮችን፡ሙሉ፤ውጡ፡አላቸው።እነርሱም፡ወጥተው፡ በከተማዪቱ፡ገደሉ።
8ሲገድሉም፡እኔ፡ብቻዬን፡ቀርቼ፡ሳለኹ፡በግንባሬ፡ተደፍቼ፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡ሆይ፥ወዮ! መዓትኽን፡ በኢየሩሳሌም፡ላይ፡ስታፈስ፟፡የእስራኤልን፡ቅሬታ፡ዅሉ፡ታጠፋለኽን፧ብዬ፡ጮኽኹ።
9ርሱም፦የእስራኤልና፡የይሁዳ፡ቤት፡ኀጢአት፡እጅግ፡በዝቷል፡ምድሪቱም፡ደም፥ከተማዪቱም፡ዐመፅን፡ ተሞልታለች፤እነርሱም፦እግዚአብሔር፡ምድሪቱን፡ትቷታል፡እግዚአብሔርም፡አያይም፡ብለዋል።
10እኔም፡ደግሞ፡በዐይኔ፡አልራራም፡አላዝንምም፥መንገዳቸውንም፡በራሳቸው፡ላይ፡እመልሳለኹ፡አለኝ።
11እንሆም፥በፍታ፡የለበሰው፡የቀለም፡ቀንድም፡በወገቡ፡የያዘው፡ሰው፦ያዘዝኸኝን፡አድርጌያለኹ፡ብሎ፡ በቃሉ፡መለሰ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org