Skip to content
← Ezekiel

Chapter 11 · Amharic

Ezekiel

1መንፈስም፡አነሣኝ፤ወደፀሓይ፡መውጫ፡ወደሚመለከት፡ወደእግዚአብሔር፡ቤትም፡ወደምሥራቁ፡በር፡ አመጣኝ።እንሆም፥በበሩ፡መግቢያ፡ኻያ፡ዐምስት፡ሰዎች፡ነበሩ፥በመካከላቸውም፡የሕዝቡን፡አለቃዎች፡ የዓዙርን፡ልጅ፡ያእዛንያንና፡የበናያስ፡ልጅ፡ፈላጥያን፡አየኹ።

2ርሱም፡እንዲህ፡አለኝ፦የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥እነዚህ፡ክፋትን፡የሚያስቡ፡በዚችም፡ከተማ፡ክፉን፡ምክር፡ የሚመክሩ፡ሰዎች፡ናቸው።

3እነርሱም፦በእውኑ፡ቤቶችን፡የምንሠራበት፡ዘመን፡የቀረበ፡አይደለምን፧ይህች፡ከተማ፡ድስት፡እኛም፡ ሥጋ፡ነን፡ብለዋል።

4ስለዚህ፥የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ትንቢት፡ተናገርባቸው፤ትንቢት፡ተናገር።

5የእግዚአብሔርም፡መንፈስ፡ወደቀብኝ፡እንዲህም፡አለኝ፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፡ብለኽ፡ ተናገር።የእስራኤል፡ቤት፡ሆይ፥ይህን፡ነገር፡ተናግራችዃል፥እኔም፡የልባችኹን፡ዐሳብ፡ዐውቃለኹ።

6በዚች፡ከተማ፡ውስጥ፡ግዳዮቻችኹን፡አብዝታችዃል፥በጐዳናዎቿም፡ግዳዮችን፡ሞልታችዃል።

7ስለዚህ፥ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦በመካከሏ፡ያኖራችዃቸው፡ግዳዮቻችኹ፡እነርሱ፡ሥጋው፡ ናቸው፥ይህችም፡ከተማ፡ድስቱ፡ናት፤እናንተን፡ግን፡ከመካከሏ፡አወጣችዃለኹ።

8ሰይፍን፡ፈርታችዃል፡እኔም፡ሰይፍን፡አመጣባችዃለኹ፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።

9ከመካከሏም፡አወጣችዃለኹ፥በእንግዳዎችም፡እጅ፡አሳልፌ፡እሰጣችዃለኹ፥በላያችኹም፡ፍርድ፡ አደርጋለኹ።

10በሰይፍ፡ትወድቃላችኹ፡በእስራኤልም፡ድንበር፡እፈርድባችዃለኹ፤እኔም፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ ታውቃላችኹ።

11ይህች፡ከተማ፡ድስት፡አትኾንላችኹም፡እናንተም፡በመካከሏ፡ሥጋ፡አትኾኑም፥እኔም፡በእስራኤል፡ድንበር፡ እፈርድባችዃለኹ፤እኔም፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ታውቃላችኹ።

12በትእዛዜ፡አልኼዳችኹምና፥ፍርዴንም፡አላደረጋችኹምና፤በዙሪያችኹም፡እንደሚኖሩት፡እንደ፡አሕዛብ፡ ሕግ፡አድርጋችዃል።

13ትንቢትም፡በተናገርኹ፡ጊዜ፡የበናያስ፡ልጅ፡ፈላጥያ፡ሞተ፤እኔም፡በግንባሬ፡ተደፍቼ፦ጌታ፡ እግዚአብሔር፡ሆይ፥ወዮ! በእውኑ፡የእስራኤልን፡ቅሬታ፡ፈጽመኽ፡ታጠፋለኽን፧ብዬ፡በታላቅ፡ድምፅ፡ ጮኽኹ።

14የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦

15የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥በኢየሩሳሌም፡የሚኖሩ፦ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ራቁ፤ይህች፡ምድር፡ርስት፡ኾና፡ ለእኛ፡ተሰጥታለች፡የሚሏቸው፡ወንድሞችኽና፡ዘመዶችኽ፡የወገኖችኽም፡ሰዎች፡ዅሉ፡የእስራኤልም፡ቤት፡ ዅሉ፡ናቸው።

16ስለዚህ፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እኔ፡ወደ፡አሕዛብ፡አርቄያቸዋለኹ፥ወደ፡አገሮችም፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org በትኛቸዋለኹ፤ይኹን፡እንጂ፥በመጡባቸው፡አገሮች፡በእነዚያ፡ትንሽ፡መቅደስ፡እኾናቸዋለኹ፡በል።

17ስለዚህም፡በል፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ከአሕዛብ፡ዘንድ፡አከማቻችዃለኹ፡ ከተበተናችኹባቸውም፡አገሮች፡እሰበስባችዃለኹ፥የእስራኤልንም፡ምድር፡እሰጣችዃለኹ።

18ወደዚያም፡ይመጣሉ፥ጸያፉንና፡ርኩሱንም፡ነገር፡ዅሉ፡ከርሷ፡ያወጣሉ።

20በትእዛዜም፡ይኼዱ፡ዘንድ፡ፍርዴንም፡ይጠብቁና፡ያደርጉ፡ዘንድ፡አንድ፡ልብ፡ እሰጣቸዋለኹ፥በውስጣቸውም፡ዐዲስ፡መንፈስ፡እሰጣለኹ፥ከሥጋቸውም፡ውስጥ፡የድንጋዩን፡ልብ፡አወጣለኹ፡ የሥጋንም፡ልብ፡እሰጣቸዋለኹ፤እነርሱም፡ሕዝብ፡ይኾኑኛል፡እኔም፡አምላክ፡እኾናቸዋለኹ።

21ልባቸውም፡ጸያፍንና፡ርኩስን፡ነገር፡በሚከተል፡በእነርሱ፡ራስ፡ላይ፡መንገዳቸውን፡እመልሳለኹ፥ይላል፡ ጌታ፡እግዚአብሔር።

22ኪሩቤልም፡ክንፎቻቸውን፡ዘረጉ፥መንኰራኵሮችም፡በአጠገባቸው፡ነበሩ፤የእስራኤልም፡አምላክ፡ክብር፡ በላያቸው፡ላይ፡ነበረ።

23የእግዚአብሔርም፡ክብር፡ከከተማዪቱ፡ውስጥ፡ተነሥቶ፡በከተማዪቱ፡ምሥራቅ፡በኩል፡ባለው፡ተራራ፡ላይ፡ ቆመ።

24መንፈስም፡አነሣኝ፥በእግዚአብሔርም፡መንፈስ፡በራእይ፡ወደከላውዴዎን፡ምድር፡ወደ፡ምርኮኛዎቹ፡ አመጣኝ።ያየኹትም፡ራእይ፡ከእኔ፡ወጥቶ፡ተለየ።

25እግዚአብሔርም፡ያሳየኝን፡ነገር፡ዅሉ፡ለምርኮኛዎች፡ተናገርኹ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source