Skip to content
← Ezekiel

Chapter 12 · Amharic

Ezekiel

1የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦

2የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥በዐመፀኛ፡ቤት፡መካከል፡ተቀምጠኻል፤ያዩ፡ዘንድ፡ዐይን፡አላቸው፡እነርሱም፡ አያዩም፥ይሰሙም፡ዘንድ፡ዦሮ፡አላቸው፡እነርሱም፡አይሰሙም፤እነርሱ፡ዐመፀኛ፡ቤት፡ናቸውና።

3አንተም፥የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥የስደተኛ፡እክት፡አዘጋጅ፡በፊታቸውም፡ቀን፡ለቀን፡ተማረክ፥በፊታቸውም፡ ከስፍራ፡ወደ፡ሌላ፡ስፍራ፡ተማርከኽ፡ኺድ፤እነርሱም፡ዐመፀኛ፡ቤት፡እንደ፡ኾኑ፡ምናልባት፡ያስተውሉ፡ ይኾናል።

4ቀን፡ለቀንም፡በፊታቸው፡እክትኽን፡እንደ፡ስደተኛ፡እክት፡አውጣው፥በማታም፡ጊዜ፡በፊታቸው፡ ስደተኛዎች፡እንደሚወጡ፡እንዲሁ፡ውጣ።

5በፊታቸውም፡ግንቡን፡ንደል፡በርሱም፡አውጣ።

6ለእስራኤልም፡ቤት፡ምልክት፡አድርጌኻለኹና፡በፊታቸው፡በጫንቃኽ፡ላይ፡አንግተው፥በጨለማም፡ ተሸክመኽ፡ውጣ፤ምድሪቱንም፡እንዳታይ፡ፊትኽን፡ሸፍን።

7እንዳዘዘኝም፡አደረግኹ፤ቀን፡ለቀንም፡እክቱን፡እንደ፡ስደተኛ፡እክት፡አወጣኹ፥በማታም፡ጊዜ፡ግንቡን፡ በእጄ፡ነደልኹ፥በጨለማም፡አወጣኹት፡በፊታቸውም፡በጫንቃዬ፡ላይ፡አንግቼ፡ተሸከምኹት።

8በነጋውም፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦

9የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ዐመፀኛ፡ቤት፡የእስራኤል፡ቤት፦የምታደርገው፡ምንድር፡ነው፧አላሉኽምን፧

10አንተም፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ይህ፡ሸክም፡በኢየሩሳሌም፡በሚኖረው፡አለቃ፡ላይ፡ በመካከላቸውም፡በሚኖሩት፡በእስራኤል፡ቤት፡ዅሉ፡ላይ፡ነው፡በላቸው።

11ደግሞም፦እኔ፡ምልክታችኹ፡ነኝ፤እኔ፡እንዳደረግኹ፡እንዲሁ፡ይደረግባቸዋል፥እነርሱም፡በስደት፡ወደ፡ ምርኮ፡ይኼዳሉ፡በል። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

12በመካከላቸውም፡የሚኖረው፡አለቃ፡በጫንቃው፡ላይ፡አንግቶ፡በጨለማ፡ይወጣል፤በዚያ፡ያወጡ፡ዘንድ፡ ግንቡን፡ይነድላሉ፥በዐይኑም፡ምድርን፡እንዳያይ፡ፊቱን፡ይሸፍናል።

13መረቤንም፡በርሱ፡ላይ፡እዘረጋለኹ፡በወጥመዴም፡ይያዛል፥ወደከለዳውያንም፡ምድር፡ወደ፡ባቢሎን፡ አመጣዋለኹ፤ኾኖም፡አያያትም፡በዚያም፡ይሞታል።

14ሊረዱትም፡በዙሪያው፡ያሉትን፡ዅሉ፡ጭፍራዎቹንም፡ዅሉ፡ወደ፡ነፋሳት፡ዅሉ፡ እበትናቸዋለኹ፤በዃላቸውም፡ሰይፍ፡እመዛ፟ለኹ።

15በአሕዛብም፡መካከል፡በበተንዃቸው፡ጊዜ፥በአገሮችም፡በዘራዃቸው፡ጊዜ፥እኔ፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ ኾንኹ፡ያውቃሉ።

16በሚኼዱባቸውም፡አሕዛብ፡መካከል፡ርኵሰታቸውን፡ዅሉ፡ይናገሩ፡ዘንድ፡ከሰይፍና፡ከራብ፡ከቸነፈርም፡ ጥቂቶች፡ሰዎችን፡ከነርሱ፡አስቀራለኹ፤እኔም፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ያውቃሉ።

17የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦

18የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥እንጀራኽን፡በድንጋጤ፡ብላ፡ውሃኽንም፡በመንቀጥቀጥና፡በሐዘን፡ጠጣ፤

19ለምድሪቱም፡ሕዝብ፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡በኢየሩሳሌም፡ስለሚኖሩ፡ስለእስራኤልም፡ምድር፡እንዲህ፡ ይላል፦ስለሚኖሩባት፡ዅሉ፡ግፍ፡ምድሪቱ፡ከነሞላዋ፡ትጠፋ፡ዘንድ፡እንጀራቸውን፡በችግር፡ይበላሉ፡ ውሃቸውንም፡በድንጋጤ፡ይጠጣሉ።

20ሰዎች፡የሚኖሩባቸው፡ከተማዎች፡ባድማ፡ይኾናሉ፡ምድሪቱም፡ውድማ፡ትኾናለች፤እኔም፡እግዚአብሔር፡ እንደ፡ኾንኹ፡ታውቃላችኹ፡በላቸው።

21የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦

22የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥በእስራኤል፡ምድር፦ዘመኑ፡ረዝሟል፡ራእዩም፡ዅሉ፡ጠፍቷል፡የምትሉት፡ምሳሌ፡ ምንድር፡ነው፧

23ስለዚህ፥እንዲህ፡በላቸው፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ይህን፡ምሳሌ፡አስቀረዋለኹ፡ በእስራኤልም፡ዘንድ፡ደግሞ፡ምሳሌ፡አድርገው፡አይናገሩትም፤አንተ፡ግን፦ዘመኑና፡የራእዩ፡ዅሉ፡ነገር፡ ቀርቧል፡በላቸው።

24ከዚህም፡በዃላ፡በእስራኤል፡ቤት፡መካከል፡ከንቱ፡ራእይና፡ውሸተኛ፡ሟርት፡አይኾንም።

25እኔ፡እግዚአብሔር፡ነኝ፤እናገራለኹ፡የምናገረውም፡ቃል፡ይፈጸማል፥ደግሞም፡አይዘገይም፤እናንተ፡ ዐመፀኛ፡ቤት፡ሆይ፥በዘመናችኹ፡ቃሌን፡እናገራለኹ፡እፈጽመውማለኹ፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።

26የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦

27የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥እንሆ፥የእስራኤል፡ቤት፦ይህች፡የሚያያት፡ራእይ፡ለብዙ፡ዘመን፡ናት፥ርሱም፡ ለሩቅ፡ወራት፡ትንቢት፡ይናገራል፡ይላሉ።

28ስለዚህ፥በላቸው፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦የምናገረው፡ቃል፡ይፈጸማል፡እንጂ፡ከቃሌ፡ ዅሉ፡ደግሞ፡የሚዘገይ፡የለም፥ይላል፡እግዚአብሔር።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source