Skip to content
← Ezekiel

Chapter 13 · Amharic

Ezekiel

1የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦

2የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ትንቢት፡በሚናገሩ፡በእስራኤል፡ነቢያት፡ላይ፡ትንቢት፡ተናገር፥ከገዛ፡ልባቸውም፡ ትንቢት፡የሚናገሩትን፦የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ስሙ፡በላቸው፤

3ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ምንም፡ምን፡ሳያዩ፡የገዛ፡መንፈሳቸውን፡ለሚከተሉ፡ለሰነፎች፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ነቢያት፡ወዮላቸው!

4እስራኤል፡ሆይ፥ነቢያትኽ፡በምድረ፡በዳ፡እንደሚኖሩ፡ቀበሮዎች፡ናቸው።

5ወደተሰበረው፡ቅጥር፡አልወጣችኹም፥በእግዚአብሔርም፡ቀን፡በሰልፍ፡ትቆሙ፡ዘንድ፡ለእስራኤል፡ቤት፡ ቅጥር፡አልሠራችኹም።

6እግዚአብሔር፡ሳይልካቸው።እግዚአብሔር፡ይላል፡የሚሉ፡ሰዎች፡ከንቱ፡ነገርንና፡ውሸተኛ፡ሟርትን፡ አይተዋል፤ቃሉም፡ይጠና፡ዘንድ፡ተስፋ፡አስደርገዋል።

7እኔም፡ሳልናገር፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ብሏል፡ስትሉ፥ከንቱ፡ራእይን፡ያያችኹ፡ውሸተኛንም፡ሟርት፡ የተናገራችኹ፡አይደላችኹምን፧

8ስለዚህ፥ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ከንቱ፡ነገርን፡ስለ፡ተናገራችኹ፥ውሸተኛ፡ራእይንም፡ ስላያችኹ፥ስለዚህ፥እንሆ፥እኔ፡በእናንተ፡ላይ፡ነኝ፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።

9እጄም፡ከንቱ፡ራእይን፡በሚያዩ፥በውሸትም፡በሚያሟርቱ፡ነቢያት፡ላይ፡ትኾናለች፤እነርሱም፡በሕዝቤ፡ ማኅበር፡ውስጥ፡አይገኙም፥በእስራኤልም፡ቤት፡መጽሐፍ፡አይጻፉም፥ወደእስራኤልም፡ምድር፡ አይገቡም፤እኔም፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ያውቃሉ።

10ሰላም፡ሳይኖር፦ሰላም፡እያሉ፡ሕዝቤን፡አታለ፟ዋልና፤አንዱም፡ሰው፡ቅጥር፡ሲሠራ፥እንሆ፥ገለባ፡ በሌለበት፡ጭቃ፡ይመርጉታልና፥

11ገለባ፡በሌለበት፡ጭቃ፡ለሚመርጉት፡ሰዎች፦ይወድቃል፡በላቸው።የሚያሰጥም፡ዝናብ፡ ይዘንባል፥ታላቅም፡የበረዶ፡ድንጋይ፡ይወድቃል፥ዐውሎ፡ነፋስም፡ይሰነጣጥቀዋል።

12እንሆ፥ግንቡ፡በወደቀ፡ጊዜ፦የመረጋችኹት፡ጭቃ፡ወዴት፡አለ፧አይሏችኹምን፧

13ስለዚህ፥ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦በመዓቴ፡በዐውሎ፡ነፋስ፡እሰነጣጥቀዋለኹ፥ያጠፋውም፡ ዘንድ፡በቍጣዬ፡የሚያሰጥም፡ዝናብ፥በመዓቴም፡ታላቅ፡የበረዶ፡ድንጋይ፡ይወርዳል።

14ገለባም፡በሌለበት፡ጭቃ፡የመረጋችኹትን፡ቅጥር፡አፈርሳለኹ፥ወደ፡ምድርም፡እጥለዋለኹ፥መሠረቱም፡ ይታያል።ርሱም፡ይናዳል፥በመካከሉም፡ትጠፋላችኹ፤እኔም፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ታውቃላችኹ።

15መዓቴንም፡በግንቡ፡ላይ፡ገለባም፡በሌለበት፡ጭቃ፡በመረጉት፡ላይ፡እፈጽማለኹ፤እኔም፦ግንቡና፡ መራጊዎቹ፡የሉም፡እላችዃለኹ።

16እነርሱም፡ስለ፡ኢየሩሳሌም፡ትንቢት፡የሚናገሩ፡የሰላምን፡ራእይ፡የሚያዩላት፡የእስራኤል፡ነቢያት፡ ናቸው፥ሰላምም፡የለም፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።

17አንተም፥የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ከገዛ፡ልባቸው፡ትንቢት፡በሚናገሩ፡በሕዝብኽ፡ሴቶች፡ልጆች፡ላይ፡ ፊትኽን፡አድርግ፤ትንቢትም፡ተናገርባቸው፥

18እንዲህም፡በል፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ነፍስን፡ለማጥመድ፥ለእጅ፡ድጋፍ፡ዅሉ፡መከዳ፡ ለሚሰፉ፥ለሰውም፡ዅሉ፡ራስ፡እንደ፡እየቁመቱ፡ሽፋን፡ለሚሠሩ፡ሴቶች፥ወዮላቸው! የሕዝቤንም፡ነፍስ፡ ብታጠምዱ፡በእውኑ፡ነፍሳችኹን፡ታድናላችኹን፧

19ውሸታችኹን፡ለሚሰሙት፡ሕዝቤ፡እየዋሻችኹ፡ሞት፡የማይገ፟ባ፟ቸውን፡ነፍሳት፡ትገድሉ፡ዘንድ፡ በሕይወትም፡መኖር፡የማይገ፟ባ፟ቸውን፡ነፍሳት፡በሕይወት፡ታኖሩ፡ዘንድ፥ስለ፡ጭብ፟ጥ፡ገብስና፡ስለ፡ቍራሽ፡ እንጀራ፡በሕዝቤ፡ዘንድ፡አርክሳችኹኛል።

20ስለዚህ፥ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥እኔ፡ነፍሳትን፡እንደ፡ወፍ፡በምታጠምዱባት፡ በመከዳችኹ፡ላይ፡ነኝ፥ከክንዳችኹም፡ወስጄ፡እቀዳ፟ታለኹ፥እንደ፡ወፍም፡የምታጠምዷቸውን፡ነፍሳት፡ እለቃ፟ለኹ።

21ሽፋኖቻችኹን፡ደግሞ፡እቀዳ፟ለኹ፡ሕዝቤንም፡ከእጃችኹ፡አድናለኹ፥ከዚያም፡ወዲያ፡በእጃችኹ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ለመታደን፡አይኾኑም፤እኔም፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ታውቃላችኹ።

22እኔም፡ያላሳዘንኹትን፡የጻድቁን፡ልብ፡በውሸት፡አሳዝናችዃልና፥በሕይወትም፡ይኖር፡ዘንድ፡ከክፉ፡ መንገድ፡እንዳይመለስ፡የኀጢአተኛውን፡እጅ፡አበርትታችዃልና፥

23ስለዚህ፥ከንቱን፡ራእይ፡እንግዲህ፡አታዩም፡ሟርትንም፡አታሟርቱም፥ሕዝቤንም፡ከእጃችኹ፡ አድናለኹ፤እኔም፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ታውቃላችኹ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source