Skip to content
← Ezekiel

Chapter 14 · Amharic

Ezekiel

1ከእስራኤልም፡ሽማግሌዎች፡ዐያሌ፡ሰዎች፡ወደ፡እኔ፡መጥተው፡በፊቴ፡ተቀመጡ።

2የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦

3የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥እነዚህ፡ሰዎች፡ጣዖቶቻቸውን፡በልባቸው፡አኑረዋል፡የበደላቸውንም፡መቅሠፍት፡ በፊታቸው፡አቁመዋል፤እኔስ፡ከነርሱ፡ልጠየቅን፧

5ስለዚህ፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ዅሉም፡በጣዖቶቻቸው፡ከእኔ፡ ተለይተዋልና፥የእስራኤልን፡ቤት፡በልባቸው፡እይዝ፡ዘንድ፡ከእስራኤል፡ቤት፡ጣዖቶቹን፡በልቡ፡ የሚያኖር፥የበደሉንም፡መቅሠፍት፡በፊቱ፡የሚያቆም፡ሰው፡ዅሉ፡ወደ፡ነቢዩ፡በመጣ፡ጊዜ፥እኔ፡ እግዚአብሔር፡እንደ፡ጣዖታቱ፡ብዛት፡እመልስለታለኹ፡ብለኽ፡ንገራቸው።

6ስለዚህ፥ለእስራኤል፡ቤት፡እንዲህ፡በል፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ንስሓ፡ ግቡ፥ከጣዖቶቻችኹም፡ተመለሱ፥ፊታችኹንም፡ከርኵሰታችኹ፡ዅሉ፡መልሱ።

7ከእስራኤልም፡ቤት፥በእስራኤልም፡ዘንድ፡ከሚቀመጡ፡መጻተኛዎች፡የሚኾን፥ከእኔ፡ተለይቶ፡ጣዖቶቹን፡ በልቡ፡የሚያኖር፥የበደሉንም፡መቅሠፍት፡በፊቱ፡የሚያቆም፡ሰው፡ዅሉ፥ስለ፡እኔ፡ይጠይቅ፡ዘንድ፡ወደ፡ ነቢዩ፡በመጣ፡ጊዜ፥እኔ፡እግዚአብሔር፡በራሴ፡እመልስለታለኹ፤

8ፊቴንም፡በዚያ፡ሰው፡ላይ፡አደርጋለኹ፡ምልክትና፡ምሳሌም፡አደርገዋለኹ፡ከሕዝቤም፡መካከል፡ አጠፋዋለኹ፤እኔም፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ታውቃላችኹ።

9ነቢዩም፡ቢታለል፡ቃልንም፡ቢናገር፥ያንን፡ነቢይ፡ያታለልኹ፡እኔ፡እግዚአብሔር፡ነኝ፥እጄንም፡በርሱ፡ ላይ፡እዘረጋለኹ፡ከሕዝቤም፡ከእስራኤል፡መካከል፡አጠፋዋለኹ።

10ኀጢአታቸውን፡ይሸከማሉ፡እንደሚጠይቀውም፡ሰው፡ኀጢአት፡እንዲሁ፡የነቢዩ፡ኀጢአት፡ይኾናል።

11ይኸውም፡የእስራኤል፡ቤት፡ደግሞ፡ከእኔ፡ርቀው፡እንዳይስቱ፡በኀጢአታቸውም፡ዅሉ፡እንዳይረክሱ፡ ነው።እነርሱም፡ሕዝብ፡ይኾኑኛል፡እኔም፡አምላክ፡እኾናቸዋለኹ፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።

12የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦

13የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ምድር፡በማመፅ፡በእኔ፡ላይ፡ኀጢአት፡ስትሠራ፥እኔም፡እጄን፡ስዘረጋባት፡ የእንጀራዋንም፡በትር፡ስሰብር፡ራብን፡ስሰድ፟ባት፡ሰውንና፡እንስሳውንም፡ከርሷ፡ሳጠፋ፥

14እነዚህ፡ሦስት፡ሰዎች፥ኖኅና፡ዳንኤል፡ኢዮብም፥ቢኖሩባት፡በጽድቃቸው፡የገዛ፡ነፍሳቸውን፡ብቻ፡ ያድናሉ፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።

15ክፉዎቹን፡አራዊት፡በምድር፡ባሳልፍ፡እነርሱም፡ልጆቿን፡ቢያጠፉ፡ስለ፡አራዊትም፡ማንም፡እንዳያልፍባት፡ ባድማ፡ብትኾን፥

16እነዚህ፡ሦስት፡ሰዎች፡ቢኖሩባት፥እኔ፡ሕያው፡ነኝና፡እነርሱ፡ብቻቸውን፡ይድናሉ፡እንጂ፡ወንዶችንና፡ ሴቶች፡ልጆቻቸውን፡አያድኑም፥ምድሪቱም፡ባድማ፡ትኾናለች፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።

17ወይም፡በዚያች፡ምድር፡ላይ፡ሰይፍ፡አምጥቼ፦ሰይፍ፡ሆይ፥በምድሪቱ፡ላይ፡ዕለፊ፡ብል፥ሰውንና፡ እንስሳውንም፡ከርሷ፡ባጠፋ፥ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

18እነዚህ፡ሦስት፡ሰዎች፡ቢኖሩባት፥እኔ፡ሕያው፡ነኝና፡እነርሱ፡ብቻቸውን፡ይድናሉ፡እንጂ፡ወንዶችንና፡ ሴቶች፡ልጆቻቸውን፡አያድኑም፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።

19ወይም፡በዚያች፡ምድር፡ላይ፡ቸነፈር፡ብሰድ፟፡ሰውንና፡እንስሳውንም፡ከርሷ፡አጠፋ፡ዘንድ፡መዓቴን፡ በደም፡ባፈስ፟ባት፥

20ኖኅና፡ዳንኤል፡ኢዮብም፡ቢኖሩባት፥እኔ፡ሕያው፡ነኝና፡በጽድቃቸው፡ነፍሳቸውን፡ብቻ፡ያድናሉ፡እንጂ፡ ወንዶችንና፡ሴቶች፡ልጆቻቸውን፡አያድኑም፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።

21ጌታ፡እግዚአብሔርም፡እንዲህ፡ይላል፦ይልቁንስ፡ሰውንና፡እንስሳን፡ከርሷ፡አጠፋ፡ዘንድ፡በኢየሩሳሌም፡ ላይ፡አራቱን፡ክፉ፡ፍርዶቼን፥ሰይፍንና፡ራብን፡ክፉዎችንም፡አውሬዎች፡ቸነፈርንም፥ስሰድ፟ባት!

22ነገር፡ግን፥እንሆ፥የሚያመልጡና፡ወንዶችና፡ሴቶች፡ልጆችን፡የሚያመጡ፡ይቀሩላታል፤እንሆ፥ወደ፡ እናንተ፡ይወጣሉ፡እናንተም፡መንገዳቸውንና፡ሥራቸውን፡ታያላችኹ፤በኢየሩሳሌምም፡ላይ፡ስላመጣኹት፡ክፉ፡ ነገር፡ዅሉ፡ስላመጣኹባትም፡ነገር፡ዅሉ፡ትጽናናላችኹ።

23መንገዳቸውንና፡ሥራቸውን፡ባያችኹ፡ጊዜ፡ያጽናኗችዃል፤ያደረግኹባትንም፡ዅሉ፡በከንቱ፡ እንዳላደረግኹባት፡ታውቃላችኹ፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source