1የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
2የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥የወይን፡ግንድ፥በዱር፡ዛፎች፡መካከል፡ያለ፡የወይን፡ዐረግ፥ከዛፍ፡ዅሉ፡ይልቅ፡ ብልጫው፡ምንድር፡ነው፧
3በእውኑ፡ሥራ፡የሚሠራበትን፡ዕንጨት፡ከርሱ፡ይወስዳሉን፧ወይስ፡ሰዎች፡ዕቃ፡የሚንጠለጠልበትን፡ኵላብ፡ ከርሱ፡ይወስዳሉን፧
4እንሆ፥ለመቃጠል፡በእሳት፡ላይ፡ተጥሏል፥እሳቱም፡ኹለቱን፡ጫፎቹን፡በልቷል፥መካከሉም፡ ተቃጥሏል፤በእውኑ፡ለሥራ፡ይጠቅማልን፧
5እንሆ፥ደኅና፡ሳለ፡ለሥራ፡ካልጠቀመ፥ይልቁንስ፡እሳት፡ከበላው፡ርሱም፡ከተቃጠለ፡በዃላ፡እንዴት፡ ሥራ፡ይሠራበታል፧
6ስለዚህ፥ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦በዱር፡ዛፎች፡መካከል፡ያለውን፡የወይን፡ግንድ፡እሳት፡ ይበላው፡ዘንድ፡እንደ፡ሰጠኹት፥እንዲሁ፡በኢየሩሳሌም፡የሚኖሩትን፡አሳልፌ፡እሰጣለኹ።
7ፊቴንም፡በእነርሱ፡ላይ፡አደርጋለኹ፤ከእሳትም፡ይወጣሉ፥እሳት፡ግን፡ይበላቸዋል፤ፊቴንም፡በእነርሱ፡ላይ፡ ባደረግኹ፡ጊዜ፡እኔ፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ታውቃላችኹ።
8ዐመፅን፡አድርገዋልና፥ምድሪቱን፡ባድማ፡አደርጋለኹ፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።