1የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
2የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ለኢየሩሳሌም፡ርኵሰቷን፡አስታውቃት፥
3እንዲህም፡በል፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡ለኢየሩሳሌም፡እንዲህ፡ይላል፦ዘርሽና፡ትውልድሽ፡ከከነዓን፡ምድር፡ ነው፤አባትሽ፡አሞራዊ፡ነበረ፡እናትሽም፡ኬጢያዊት፡ነበረች።
4በተወለድሽ፡ጊዜ፡በዚያው፡ቀን፡ዕትብትሽ፡አልተቈረጠም፡ንጹሕም፡ትኾኚ፡ዘንድ፡በውሃ፡ አልታጠብሽም፥በጨውም፡አልተቀባሽም፡በጨርቅም፡አልተጠቀለልሽም። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
5በተወለድሽበት፡ቀን፡ከሰውነትሽ፡ጕስቍልና፡የተነሣ፡በሜዳ፡ላይ፡ተጣልሽ፡እንጂ፡ከዚህ፡አንዳች፡ ይደረግልሽ፡ዘንድ፡ዐይን፡አልራራልሽም፥ማንም፡አላዘነልሽም።
6ባንቺም፡ዘንድ፡ባለፍኹ፡ጊዜ፡በደምሽም፡ውስጥ፡ተለውሰሽ፡ባየኹሽ፡ጊዜ፦በደምሽ፡እንዳለሽ፡ በሕይወት፡ኑሪ፡አልኹሽ፤አዎን፦በደምሽ፡እንዳለሽ፡በሕይወት፡ኑሪ፡አልኹሽ።
7በዕርሻ፡ላይ፡እንዳለ፡ቡቃያ፡አበዛኹሽ፥አንቺም፡አደግሽ፡ታላቅም፡ኾንሽ፥በእጅጉም፡ አጌጥሽ፤ጡቶችሽም፡አጐጠጐጡ፡ጠጕርሽም፡አደገ፥ነገር፡ግን፥ዕርቃንሽን፡ኾንሽ፥ተራቍተሽም፡ነበርሽ።
8ባንቺ፡ዘንድ፡ባለፍኹና፡ባየኹሽ፡ጊዜ፥እንሆ፥ጊዜሽ፡የፍቅር፡ጊዜ፡ነበረ፤እኔም፡መጐናጸፊያዬን፡ በላይሽ፡ዘረጋኹ፡ኀፍረተ፡ሥጋሽንም፡ከደንኹ፤ማልኹልሽም፡ከአንቺም፡ጋራ፡ቃል፡ኪዳን፡ገባኹ፥ይላል፡ ጌታ፡እግዚአብሔር፥አንቺም፡ለእኔ፡ኾንሽ።
9በውሃም፡አጠብኹሽ፡ከደምሽም፡አጠራኹሽ፡በዘይትም፡ቀባኹሽ።
10ወርቀ፡ዘቦም፡አለበስኹሽ፡በአቍስጣ፡ቍርበትም፡ጫማ፡አደረግኹልሽ፤በጥሩ፡በፍታ፡አስታጠቅኹሽ፡ በሐርም፡ከደንኹሽ።
11በጌጥም፡አስጌጥኹሽ፡በእጅሽም፡ላይ፡አንባር፡በዐንገትሽም፡ላይ፡ድሪ፡አደረግኹልሽ።
12በአፍንጫሽም፡ቀለበት፡በዦሮሽም፡ጕትቻ፡በራስሽም፡ላይ፡የክብር፡አክሊል፡አደረግኹ።
13በወርቅና፡በብር፡አጌጥሽ፥ልብስሽም፡ጥሩ፡በፍታና፡ሐር፡ወርቀ፡ዘቦም፡ነበረ፤አንቺም፡መልካምን፡ ዱቄትና፡ማርን፡ዘይትንም፡በላሽ፤እጅግ፡በጣም፡ውብ፡ኾንሽ፡ለመንግሥትም፡ደረስሽ።
14ባንቺ፡ላይ፡ካኖርዃት፡ከክብሬ፡የተነሣ፡ውበትሽ፡ፍጹም፡ነበረና፡ዝናሽ፡በአሕዛብ፡መካከል፡ ወጣ፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
15ነገር፡ግን፥በውበትሽ፡ታምነሻል፡ስለ፡ዝናሽም፡አመንዝረሻል፡ምንዝርናሽንም፡ከመንገድ፡ዐላፊ፡ዅሉ፡ ጋራ፡አበዛሽ።
16ከልብስሽም፡ወስደሽ፡በኰረብታዎች፡ላይ፡በዝንጕርጕር፡ልብስ፡ያስጌጥሻቸውን፡መስገጆች፡ለራስሽ፡ ሠራሽ፡በዚያም፡ገለሞትሽ፤እንዲህም፡ያለ፡ነገር፡ካኹን፡በፊት፡አልነበረም፥ከእንግዲህም፡ወዲያ፡አይኾንም።
17ከሰጠኹሽም፡ከወርቄና፡ከብሬ፡የተሠራውን፡የክብርሽን፡ዕቃ፡ወስደሽ፡የወንድ፡ምስሎች፡ለራስሽ፡ አድርገሻል፥አመንዝረሽባቸውማል።
18ወርቀ፡ዘቦውን፡ልብስሽንም፡ወስደሽ፡ደረብሽላቸው፥ዘይቴንና፡ዕጣኔንም፡በፊታቸው፡አኖርሽ።
19የሰጠኹሽንም፡እንጀራዬን፡ያበላኹሽንም፡መልካሙን፡ዱቄትና፡ዘይቱን፡ማሩንም፡ጣፋጭ፡ሽታ፡አድርገሽ፡ በፊታቸው፡አኖርሽ፥እንዲሁም፡ኾኗል፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
20ለኔም፡የወለድሻቸውን፡ወንዶችና፡ሴቶች፡ልጆችሽን፡ወስደሽ፡መብል፡ይኾኑ፡ዘንድ፡ሠዋሽላቸው።
21ልጆቼን፡ዐረድሽ፤ለእነርሱም፡በእሳት፡በኩል፡አሳልፈሽ፡ሰጠሽ፤በእውኑ፡ግልሙትናሽ፡ጥቂት፡ነውን፧
22በርኩስነትሽና፡በግልሙትናሽ፡ዅሉ፡ዕርቃንሽን፡ኾነሽ፡ተራቍተሽም፡ሳለሽ፡በደምሽም፡ተለውሰሽ፡ሳለሽ፡ የሕፃንነትሽን፡ወራት፡አላሰብሽም።
23ወዮ! ወዮልሽ! ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር፤
24ከክፋትሽም፡ዅሉ፡በዃላ፡የምንዝርናን፡ስፍራ፥በያደባባዩም፡ከፍ፡ያለ፡ቦታን፡ለራስሽ፡ሠራሽ።
25በየመንገዱ፡ራስ፡ከፍ፡ያለውን፡ቦታሽን፡ሠራሽ፥ውበትሽንም፡አረከ፟ሽ፥ለመንገድ፡ዐላፊም፡ዅሉ፡ እግርሽን፡ገለጥሽ፡ግልሙትናሽንም፡አበዛሽ።
26ሥጋቸውም፡ከወፈረ፡ከጎረቤቶችሽ፡ከግብጻውያን፡ጋራ፡አመነዘርሽ፥እኔንም፡ታስቈጪ፡ዘንድ፡ ግልሙትናሽን፡አበዛሽ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
27ስለዚህ፥እንሆ፥እጄን፡ባንቺ፡ላይ፡ዘርግቻለኹ፡ድርጎሽንም፡አጕድያለኹ፤ለሚጠሉሽም፡ከክፉ፡ መንገድሽ፡የተነሣ፡ለሚያፍሩ፡ለፍልስጥኤም፡ሴቶች፡ልጆች፡ፈቃድ፡አሳልፌ፡ሰጥቼሻለኹ።
28አልጠገብሽምና፡ከአሶራውያን፡ጋራ፡ደግሞ፡ገለሞትሽ፡ከዚህም፡ጋራ፡ገና፡አልጠገብሽም።
29እስከነጋዴዎች፡ምድር፡እስከ፡ከላውዴዎን፡ድረስ፡ግልሙትናሽን፡አበዛሽ።ከዚህም፡ጋራ፡ገና፡ አልጠገብሽም።
30የማታፍረውን፡የጋለሞታን፡ሥራ፡ዅሉ፡ሠርተሻልና፥ልብሽ፡ምንኛ፡ደካማ፡ነው፧ይላል፡ጌታ፡ እግዚአብሔር።
31በየመንገዱ፡ራስ፡የምንዝርናሽን፡ስፍራ፡ሠርተሻል፡በያደባባዩም፡ከፍ፡ያለውን፡ቦታሽን፡ አድርገሻል።ዋጋዋን፡እንደምትንቅ፡እንደ፡ጋለሞታ፡አልኾንሽም።
32በባሏ፡ፋንታ፡ሌላዎችን፡ተቀብላ፡የምታመነዝር፡ሴትን፡ትመስያለሽ።
33ለጋለሞታዎች፡ዅሉ፡ዋጋ፡ይሰጧቸዋል፤አንቺ፡ግን፡ለውሽማዎችሽ፡ዅሉ፡ዋጋ፡ትሰጫለሽ፥ከአንቺም፡ ጋራ፡ለማመንዘር፡በዙሪያሽ፡ይገቡብሽ፡ዘንድ፡መማለጃ፡ትሰጫቸዋለሽ።
34ግልሙትናሽ፡ከሌላዎች፡ሴቶች፡ግልብጥ፡ነው፤ማንም፡ለግልሙትና፡የሚከተልሽ፡የለም፤ዋጋ፡ ሳይሰጥሽ፡አንቺ፡ዋጋ፡በመስጠትሽ፡በዚህ፡ነገር፡ልዩ፡ኾነሻል።
35ስለዚህ፥ጋለሞታ፡ሆይ፥የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ስሚ።
36ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ከውሽማዎችሽ፡ጋራ፡ባደረግሽው፡በግልሙትናሽ፡ርኵሰትሽ፡ስለ፡ ፈሰሰ፡ኀፍረተ፡ሥጋሽም፡ስለ፡ተገለጠ፥ስለ፡ርኵሰትሽም፡ጣዖታት፡ዅሉ፡ስለሰጠሻቸውም፡ስለልጆች፡ደም፥
37ስለዚህ፥እንሆ፥ከነርሱ፡ጋራ፡ደስ፡ያለሽን፡የወደድሻቸውንም፡ውሽማዎችሽ፡ዅሉ፥ከጠላሻቸው፡ዅሉ፡ ጋራ፥እሰበስባቸዋለኹ፤ባንቺ፡ላይ፡በዙሪያሽ፡እሰበስባቸዋለኹ፥ኀፍረተ፡ሥጋሽንም፡ዅሉ፡እንዲያዩ፡ በፊታቸው፡ኀፍረተ፡ሥጋሽን፡እገልጣለኹ።
38በአመንዝራዎችና፡በደም፡አፍሳሾች፡ላይ፡የሚፈረደውን፡ፍርድ፡እፈርድብሻለኹ፥የመዓትንና፡የቅንአትን፡ ደምም፡አመጣብሻለኹ።
39በእጃቸውም፡አሳልፌ፡እሰጥሻለኹ፥የምንዝርናሽንም፡ስፍራ፡ያፈርሳሉ፡ከፍ፡ያለውንም፡ቦታሽን፡ ይገለብጣሉ፤ልብስሽንም፡ይገፉሻል፡የክብርሽንም፡ጌጥ፡ይወስዳሉ፥ዕርቃንሽን፡አድርገው፡ዕራቍትሽን፡ ይተዉሻል።
40ጉባኤን፡ያመጡብሻል፡በድንጋይም፡ይወግሩሻል፥በሰይፋቸውም፡ይወጉሻል።
41ቤቶችሽንም፡በእሳት፡ያቃጥላሉ፡በብዙም፡ሴቶች፡ፊት፡በላይሽ፡ፍርድን፡ያደርጉብሻል፤ግልሙትናሽንም፡ አስተውሻለኹ፥እንግዲህስ፡ዋጋ፡አትሰጪም።
42መዓቴንም፡ባንቺ፡ላይ፡እጨርሳለኹ፡ቅንአቴም፡ከአንቺ፡ይርቃል፥እኔም፡ዝም፡እላለኹ፡ደግሞም፡ አልቈጣም።
43የሕፃንነትሽን፡ወራት፡አላሰብሽምና፥በዚህም፡ነገር፡ዅሉ፡አስቈጥተሽኛልና፥ስለዚህ፥እንሆ፥እኔ፡ደግሞ፡ መንገድሽን፡በራስሽ፡ላይ፡አመጣለኹ፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር፥ሌላንም፡ነውር፡በርኵሰትሽ፡ዅሉ፡ላይ፡ አትጨምሪም።
44እንሆ፥በምሳሌ፡የሚናገር፡ዅሉ፦እንደ፡እናቲቱ፡እንዲሁ፡ሴት፡ልጂቱ፡ናት፡እያለ፡ምሳሌ፡ ይመስልብሻል።
45አንቺ፡ባሏንና፡ልጆቿን፡የጠላሽ፡የእናትሽ፡ልጅ፡ነሽ፤አንቺም፡ባሎቻቸውንና፡ልጆቻቸውን፡የጠሉ፡ የእኅቶችሽ፡እኅት፡ነሽ፤እናታችኹ፡ኬጢያዊት፡ነበረች፡አባታችኹም፡አሞራዊ፡ነበረ።
46ታላቂቱም፡እኅትሽ፡ከሴቶች፡ልጆቿ፡ጋራ፡በስተግራሽ፡የምትቀመጥ፡ሰማርያ፡ናት፤ታናሺቱም፡እኅትሽ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ከሴቶች፡ልጆቿ፡ጋራ፡በስተቀኝሽ፡የምትቀመጥ፡ሰዶም፡ናት።
47አንቺ፡ግን፡በመንገዳቸው፡አልኼድሽም፡እንደ፡ርኵሰታቸውም፡አላደረግሽም፡ያው፡ለአንቺ፡ጥቂት፡ ነበረና፡በመንገድሽ፡ዅሉ፡ከነርሱ፡የሚከፋ፡ርኵሰት፡አደረግሽ።
48እኔ፡ሕያው፡ነኝና፡አንቺና፡ሴቶች፡ልጆችሽ፡እንዳደረጋችኹት፡እንዲሁ፡ሰዶምና፡ሴቶች፡ልጆቿ፡ አላደረጉም፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
49እንሆ፥የእኅትሽ፡የሰዶም፡ኀጢአት፡ይህ፡ነበረ፤ትዕቢት፡እንጀራን፡መጥገብ፥መዝለልና፡ሥራ፡ መፍታት፡በርሷና፡በሴቶች፡ልጆቿ፡ነበረ፥የችግረኛውንና፡የድኻውንም፡እጅ፡አላጸናችም።
50ኰርተው፡ነበር፥በፊቴም፡ርኩስ፡ነገር፡አደረጉ፤ስለዚህ፥ባየኹ፡ጊዜ፡አጠፋዃቸው።
51ሰማርያም፡የኀጢአትሽን፡እኩሌታ፡አልሠራችም፤አንቺ፡ግን፡ከእኅቶችሽ፡ይልቅ፡ርኵሰትሽን፡ አበዛሽ፥በሥራሽም፡ርኵሰት፡ዅሉ፡አጸደቅሻቸው።
52አኹንም፡ለእኅቶችሽ፡ስለ፡ፈረድሽ፡ዕፍረትሽን፡ተሸከሚ፤ከነርሱ፡የባሰ፡ኀጢአት፡ሠርተሻልና፥ከአንቺ፡ ይልቅ፡ጻድቃን፡ናቸው፤እኅቶችሽንም፡ስላጸደቅሻቸው፡ዕፈሪ፥ዕፍረትሽንም፡ተሸከሚ።
53ምርኳቸውን፥የሰዶምና፡የሴቶች፡ልጆቿን፡ምርኮ፥የሰማርያንና፡የሴቶች፡ልጆቿንም፡ ምርኮ፥በመካከላቸውም፡ያሉትን፡የምርኮኛዎችሽን፡ምርኮ፡እመልሳለኹ፤
54ስላጽናናሻቸው፥ዕፍረትን፡ትሸከሚ፡ዘንድ፡ስላደረግሽውም፡ዅሉ፡ታፍሪ፡ዘንድ።
55እኅቶችሽም፡ሰዶምና፡ሴቶች፡ልጆቿ፡ወደቀድሞ፡ኹኔታቸው፡ይመለሳሉ፥ሰማርያና፡ሴቶች፡ልጆቿም፡ ወደቀድሞ፡ኹኔታቸው፡ይመለሳሉ፥አንቺና፡ሴቶች፡ልጆችሽም፡ወደቀድሞ፡ኹኔታችኹ፡ትመለሳላችኹ።
56ክፋትሽ፡ሳይገለጥ፡በትዕቢትሽ፡ቀን፡እኅትሽ፡ሰዶም፡በአፍሽ፡መተረቻ፡አልነበረችምን፧
57አኹን፡ለሶርያ፡ሴቶች፡ልጆችና፡ለጎረቤቶቿ፡ዅሉ፥በዙሪያሽም፡ለሚንቁሽ፡ለፍልስጥኤም፡ሴቶች፡ልጆች፡ እንደ፡ርሷ፡መሰደቢያ፡ኾነሻል።
58ምንዝርነትሽንና፡ርኩስነትሽን፡ተሸክመሻል፥ይላል፡እግዚአብሔር።
59ጌታ፡እግዚአብሔርም፡እንዲህ፡ይላል፦አንቺ፡ቃል፡ኪዳንን፡በማፍረስ፡መሐላን፡የናቅሽ፡ሆይ፥አንቺ፡ እንዳደረግሽ፡እኔ፡ደግሞ፡አደርግብሻለኹ።
60ነገር፡ግን፥በሕፃንነትሽ፡ወራት፡ከአንቺ፡ጋራ፡ያደረግኹትን፡ቃል፡ኪዳኔን፡ዐስባለኹ፡የዘለዓለምንም፡ ቃል፡ኪዳን፡አጸናልሻለኹ።
61እኅቶችሽንም፡ታላቂቱንና፡ታናሺቱን፡በተቀበልሽ፡ጊዜ፡መንገድሽን፡ታስቢያለሽ፡ታፍሪማለሽ፤ለአንቺም፡ ልጆች፡ይኾኑ፡ዘንድ፡እሰጣቸዋለኹ፥ስለ፡ቃል፡ኪዳንሽ፡ግን፡አይደለም።
63ስላደረግሽውም፡ዅሉ፡ይቅር፡ባልኹሽ፡ጊዜ፥ታስቢ፡ዘንድ፡ታፍሪም፡ዘንድ፡ስለ፡ዕፍረትሽም፡ ደግሞ፡አፍሽን፡እንዳትከፍቺ፥ቃል፡ኪዳኔን፡ከአንቺ፡ጋራ፡አጸናለኹ፡እኔም፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ ታውቂያለሽ፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።