Skip to content
← Ezekiel

Chapter 17 · Amharic

Ezekiel

1የእግዚአብሔር፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦

2የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥በእንቆቅልሽ፡አጫውት፥ለእስራኤልም፡ቤት፡ምሳሌ፡ንገር፥እንዲህም፡በል፦

3ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ታላቅ፡ክንፍ፡ረዥምም፡ማርገብገቢያ፡ያለው፡ላባም፡ የተሞላ፥መልከ፡ዝንጕርጕር፡ታላቅ፡ንስር፡ወደ፡ሊባኖስ፡መጣ፥የዝግባንም፡ጫፍ፡ወሰደ።

4ቀንበጡንም፡ቀነጠበ፡ወደከነዓንም፡ምድር፡ወሰደው፡በነጋዴዎችም፡ከተማ፡አኖረው። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

5ከምድርም፡ዘር፡ወሰደ፡በፍሬያማ፡ዕርሻ፡ተከለው፡በብዙም፡ውሃ፡አጠገብ፡እንደ፡አሓያ፡ዛፍ፡አኖረው።

6በበቀለም፡ጊዜ፡ቁመቱ፡ያጠረ፡ዐረጉም፡ወደ፡ርሱ፡የሚመለስ፡ሥሩም፡በበታቹ፡የነበረ፡ሰፊ፡ወይን፡ ኾነ፥እንዲሁ፡ወይን፡ኾነ፡ዐረግም፡ሰደደ፡ቀንበጥም፡አወጣ።

7ታላቅ፡ክንፍና፡ብዙ፡ላባም፡ያለው፡ሌላ፡ታላቅ፡ንስር፡ነበረ፤እንሆም፥ያጠጣው፡ዘንድ፡ይህ፡ወይን፡ ሥሩን፡ወደ፡ርሱ፡አዘነበለ፡ዐረጉንም፡ከተተከለበት፡ከመደቡ፡ወደ፡ርሱ፡ሰደደ።

8ዐረግም፡ያወጣ፡ፍሬም፡ያፈራ፡የከበረም፡ወይን፡ይኾን፡ዘንድ፡በመልካም፡መሬት፡ውስጥ፡በብዙም፡ ውሃ፡አጠገብ፡ተተክሎ፡ነበር።

9እንዲህም፡በል፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦በእውኑ፡ይከናወንለት፡ይኾንን፧ይደርቅስ፡ ዘንድ፥ዐዲስ፡የበቀለውስ፡ቅጠሉ፡ይጠወልግ፡ዘንድ፡ሥሩን፡አይነቅለውምን፧ፍሬውንስ፡ አይለቅመውምን፧ሥሩም፡የተነቀለው፡በብርቱ፡ክንድና፡በብዙ፡ሕዝብ፡አይደለም።

10ተተክሎስ፥እንሆ፥ይከናወንለት፡ይኾንን፧የምሥራቅ፡ነፋስ፡ባገኘው፡ጊዜ፡ፈጽሞ፡ አይደርቅምን፧በተተከለበት፡መደብ፡ላይ፡ይደርቃል።

11የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦

12ለዐመፀኛ፡ቤት፦ይህ፡ትርጓሜ፡ምን፡እንደ፡ኾነ፡አታውቁምን፧በላቸው።እንዲህም፡ብለኽ፡ ንገራቸው፦እንሆ፥የባቢሎን፡ንጉሥ፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡መጣ፥ንጉሧንና፡መኳንንቷንም፡ማረከ፥ወደ፡ርሱም፡ ወደ፡ባቢሎን፡ወሰዳቸው።

13ከመንግሥትም፡ዘር፡ወስዶ፡ቃል፡ኪዳን፡ከርሱ፡ጋራ፡አደረገ፤አማለውም፥የምድሪቱንም፡ኀያላን፡ወሰደ፤

14ይኸውም፡ቃል፡ኪዳኑን፡በመጠበቅ፡እንድትጸና፡እንጂ፡መንግሥቱ፡እንድትዋረድና፡ከፍ፡እንዳትል፡ነው።

15ርሱ፡ግን፡በርሱ፡ላይ፡ሸፈተ፡ፈረሶችንና፡ብዙንም፡ሕዝብ፡ይሰጡት፡ዘንድ፡መልእክተኛዎችን፡ወደ፡ ግብጽ፡ላከ።በእውኑ፡ይከናወንለት፡ይኾንን፧ይህንስ፡ያደረገ፡ያመልጣልን፧ቃል፡ኪዳንንስ፡አፍርሶ፡ ያመልጣልን፧

16እኔ፡ሕያው፡ነኝና፡ያነገሠውና፡መሐላውን፡የናቀበቱ፥ቃል፡ኪዳኑንም፡ያፈረሰበቱ፡ንጉሥ፡በሚኖርበት፡ ስፍራ፡ከርሱ፡ጋራ፡በባቢሎን፡መካከል፡በርግጥ፡ይሞታል፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።

17ብዙዎችን፡ነፍሳት፡ለማስወገድ፡ዐፈርን፡በደለደሉ፡ምሽግም፡በሠሩ፡ጊዜ፥ፈርዖን፡ከብዙ፡ሰራዊቱና፡ ከታላቁ፡ጉባኤው፡ጋራ፡በሰልፍ፡አይረዳውም።

18ቃል፡ኪዳኑንም፡በማፍረስ፡መሐላውን፡ንቋል፤እንሆም፥እጁን፡ሰጠ፥ይህንም፡ዅሉ፡ አድርጓል፤ስለዚህ፥አያመልጥም።

19ስለዚህ፥ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እኔ፡ሕያው፡ነኝና፡የናቀውን፡መሐላዬን፡ያፈረሰውንም፡ ቃል፡ኪዳኔን፡በራሱ፡ላይ፡አመጣለኹ።

20መረቤንም፡በርሱ፡ላይ፡እዘረጋለኹ፡በወጥመድም፡ይያዛል፥ወደ፡ባቢሎንም፡አመጣዋለኹ፡በእኔም፡ላይ፡ ስላደረገው፡ዐመፅ፡በዚያ፡ከርሱ፡ጋራ፡እፋረዳለኹ።

21ጭፍራዎቹም፡ዅሉ፡በሰይፍ፡ይወድቃሉ፥የቀሩትም፡ዅሉ፡ወደ፡እየነፋሳቱ፡ይበተናሉ፤እኔም፡ እግዚአብሔር፡እንደ፡ተናገርኹ፡ታውቃላችኹ።

22ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ከረዥሙ፡ዝግባ፡ጫፍ፡ላይ፡ቀንበጥን፡ወስጄ፡ አኖረዋለኹ፤ከጫፎቹ፡አንዱን፡ቀንበጥ፡እቀነጥበዋለኹ፤በረዥምና፡በታላቅ፡ተራራም፡ላይ፡እተክለዋለኹ።

23ከፍ፡ባለው፡በእስራኤል፡ተራራ፡ላይ፡እተክለዋለኹ፥ቅርንጫፎችም፡ያወጣል፡ፍሬም፡ያፈራል፡የከበረም፡ ዝግባ፡ይኾናል፤በበታቹም፡ወፎች፡ዅሉ፡ያርፋሉ፥በቅርንጫፎቹም፡ጥላ፡በክንፍ፡የሚበር፟፡ዅሉ፡ይጠጋል።

24የዱር፡ዛፎች፡ዅሉ፡ረዥሙን፡ዛፍ፡ዝቅ፡ያደረግኹ፥ዐጪሩንም፡ዛፍ፡ከፍ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ያደረግኹ፥የለመለመውንም፡ዛፍ፡ያደረቅኹ፥የደረቀውንም፡ዛፍ፡ያለመለምኹ፡እኔ፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ ኾንኹ፡ያውቃሉ፤እኔ፡እግዚአብሔር፡ተናግሬያለኹ፡እኔም፡አድርጌያለኹ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source