1የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
2ስለ፡እስራኤል፡ምድር፦አባቶች፡ጨርቋ፡የወይን፡ፍሬ፡በሉ፥የልጆችም፡ጥርሶች፡ጠረሱ፡ብላችኹ፡ የምትመስሉት፡ምሳሌ፡ምንድር፡ነው፧
3እኔ፡ሕያው፡ነኝና፡እንግዲህ፡ወዲህ፡ይህን፡ምሳሌ፡በእስራኤል፡ዘንድ፡አትመስሉትም፥ይላል፡ጌታ፡ እግዚአብሔር።
4እንሆ፥ነፍሳት፡ዅሉ፡የእኔ፡ናቸው፤የአባት፡ነፍስ፡የእኔ፡እንደ፡ኾነች፡ደግሞ፡የልጅ፡ነፍስ፡የእኔ፡ ናት፤ኀጢአት፡የምትሠራ፡ነፍስ፡ርሷ፡ትሞታለች።
5ሰውም፡ጻድቅ፡ቢኾን፡ፍርድንና፡ቅን፡ነገርን፡ቢያደርግ፥
6በተራራም፡ላይ፡ባይበላ፡ዐይኖቹንም፡ወደእስራኤል፡ቤት፡ጣዖታት፡ባያነሣ፡የባልንጀራውንም፡ሚስት፡ ባያረክስ፡አደፍም፡ወዳለባት፡ሴት፡ባይቀርብ፤
7ሰውንም፡ባያስጨንቅ፡ለባለዕዳም፡መያዣውን፡ቢመልስ፡ፈጽሞም፡ባይቀማ፡ከእንጀራውም፡ለተራበ፡ቢሰጥ፡ የተራቈተውንም፡በልብስ፡ቢያለብስ፤
8በዐራጣ፡ባያበድር፥ትርፎቻም፡ባይወስድ፥እጁንም፡ከኀጢአት፡ቢመልስ፥በሰውና፡በሰው፡መካከልም፡ የእውነትን፡ፍርድ፡ቢፈርድ፤
9በትእዛዜም፡ቢኼድ፥እውነትንም፡ለማድረግ፡ፍርዴን፡ቢጠብቅ፥ርሱ፡ጻድቅ፡ነው፥ፈጽሞ፡በሕይወት፡ ይኖራል፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
10ርሱም፡ቀማኛና፡ደም፡አፍሳሽ፡ልጅ፡ከዚህም፡ዅሉ፡አንዳቸውን፡የሚያደርገውን፡ቢወልድ፥
11ርሱም፡ጻድቅ፡አባቱ፡የሠራውን፡ዅሉ፡ባይሠራ፡በተራራም፡ላይ፡ቢበላ፡የባልንጀራውንም፡ሚስት፡ ቢያረክስ፥
12ድኻውንና፡ችግረኛውንም፡ቢያስጨንቅ፡ቢቀማም፡መያዣውንም፡ባይመልስ፡ዐይኖቹንም፡ወደ፡ጣዖታት፡ ቢያነሣ፡ርኩስን፡ነገር፡ቢያደርግ፥
13በዐራጣ፡ቢያበድር፥ትርፎቻም፡ቢወስድ፥በእውኑ፡ርሱ፡በሕይወት፡ይኖራልን፧በሕይወት፡ አይኖርም፤ይህን፡ርኵሰት፡ዅሉ፡አድርጓልና፥ፈጽሞ፡ይሞታል፤ደሙ፡በላዩ፡ላይ፡ይኾናል።
14እንሆም፥ልጅ፡ቢወልድ፥ርሱም፡አባቱ፡የሠራውን፡ኀጢአት፡አይቶ፡ቢፈራ፡እንዲህም፡ባይሠራ፥
15በተራራ፡ላይ፡ባይበላ፡ዐይኖቹንም፡ወደእስራኤል፡ቤት፡ጣዖታት፡ባያነሣ፡የባልንጀራውንም፡ሚስት፡ ባያረክስ፥
16ሰውንም፡ባያስጨንቅ፡መያዣውን፡ባይወስድ፡ባይቀማም፡ከእንጀራውም፡ለተራበ፡ቢሰጥ፡ለተራቈተውም፡ ልብስን፡ቢያለብስ፥
17እጁንም፡ድኻን፡ከመበደል፡ቢመልስ፡ዐራጣን፡ትርፎቻንም፡ባይወስድ፡ፍርዴንም፡ቢያደርግ፡በትእዛዜም፡ ቢኼድ፥ርሱ፡ፈጽሞ፡በሕይወት፡ይኖራል፡እንጂ፡በአባቱ፡ኀጢአት፡አይሞትም።
18አባቱ፡ግን፡ፈጽሞ፡በድሏልና፥ወንድሙንም፡ቀምቷልና፥በሕዝቡም፡መካከል፡ክፉን፡ነገር፡ አድርጓልና፥እንሆ፥ርሱ፡በበደሉ፡ይሞታል።
19እናንተ፡ግን፦ልጅ፡የአባቱን፡ኀጢአት፡ስለ፡ምን፡አይሸከምም፧ትላላችኹ።ልጅ፡ፍርድንና፡ቅን፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ነገርን፡ባደረገ፡ትእዛዜንም፡ዅሉ፡በጠበቀና፡ባደረገ፡ጊዜ፡ፈጽሞ፡በሕይወት፡ይኖራል።
20ኀጢአትን፡የምትሠራ፡ነፍስ፡ርሷ፡ትሞታለች፤ልጅ፡የአባቱን፡ኀጢአት፡አይሸከምም፥አባትም፡የልጁን፡ ኀጢአት፡አይሸከምም፤የጻድቁ፡ጽድቅ፡በራሱ፡ላይ፡ይኾናል፥የኀጢአተኛውም፡ኀጢአት፡በራሱ፡ላይ፡ይኾናል።
21ኀጢአተኛውም፡ካደረጋት፡ኀጢአት፡ዅሉ፡ቢመለስ፡ትእዛዜንም፡ዅሉ፡ቢጠብቅ፡ፍርድንና፡ቅን፡ ነገርንም፡ቢያደርግ፡ፈጽሞ፡በሕይወት፡ይኖራል፡እንጂ፡አይሞትም።
22የበደለው፡በደል፡ዅሉ፡አይታሰብበትም፤በሠራው፡ጽድቅ፡በሕይወት፡ይኖራል።
23በእውኑ፡ኀጢአተኛ፡ይሞት፡ዘንድ፡እፈቅዳለኹን፧ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር፤ከመንገዱስ፡ይመለስና፡ በሕይወት፡ይኖር፡ዘንድ፡አይደለምን፧
24ጻድቁ፡ግን፡ከጽድቁ፡ቢመለስ፡ኀጢአትንም፡ቢሠራ፡ኀጢአተኛውም፡እንደሚያደርገው፡ርኵሰት፡ዅሉ፡ ቢያደርግ፥በሕይወት፡ይኖራልን፧የሠራት፡ጽድቅ፡ዅሉ፡አትታሰብለትም፤ባደረገው፡ዐመፅና፡በሠራት፡ ኀጢአት፡በዚያች፡ይሞታል።
25እናንተ፡ግን፦የጌታ፡መንገድ፡የቀናች፡አይደለችም፡ትላላችኹ።የእስራኤል፡ቤት፡ሆይ፥እንግዲህ፡ ስሙ፤በእውኑ፡መንገዴ፡የቀናች፡አይደለችምን፧ይልቅስ፡የእናንተ፡መንገድ፡ያልቀናች፡አይደለችምን፧
26ጻድቁ፡ከጽድቁ፡ቢመለስ፥ኀጢአትንም፡በሠራ፡ጊዜ፥በዚያም፡ቢሞት፥ርሱ፡ባደረገው፡በደል፡ይሞታል።
27ኀጢአተኛውም፡ከሠራው፡ኀጢአት፡ቢመለስ፡ፍርድንና፡ቅን፡ነገርንም፡ቢያደርግ፡ነፍሱን፡ይጠብቃል።
28ዐስቦ፡ከሠራው፡በደል፡ዅሉ፡ተመልሷልና፥ፈጽሞ፡በሕይወት፡ይኖራል፡እንጂ፡አይሞትም።
29ነገር፡ግን፥የእስራኤል፡ቤት፦የጌታ፡መንገድ፡የቀናች፡አይደለችም፡ይላል።የእስራኤል፡ቤት፡ ሆይ፥በእውኑ፡መንገዴ፡የቀናች፡አይደለችምን፧ይልቅስ፡የእናንተ፡መንገድ፡ያልቀናች፡አይደለችምን፧
30የእስራኤል፡ቤት፡ሆይ፥ስለዚህ፡እንደ፡መንገዱ፡በየሰዉ፡ዅሉ፡እፈርድባችዃለኹ፥ይላል፡ጌታ፡ እግዚአብሔር፤ንስሓ፡ግቡ፡ኀጢአትም፡ዕንቅፋት፡እንዳይኾንባችኹ፡ከኀጢአታችኹ፡ዅሉ፡ተመለሱ።
31የበደላችኹትን፡በደል፡ዅሉ፡ከእናንተ፡ጣሉ፡ዐዲስ፡ልብና፡ዐዲስ፡መንፈስም፡ለእናንተ፡ አድርጉ፤የእስራኤል፡ቤት፡ሆይ፥ስለ፡ምን፡ትሞታላችኹ፧
32የሟቹን፡ሞት፡አልፈቅድምና፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር፤ስለዚህ፥ተመለሱና፡በሕይወት፡ኑሩ።