1አንተም፡በእስራኤል፡አለቃዎች፡ላይ፡ይህን፡ሙሾ፡አሙሽ፥እንዲህም፡በል፦
2እናትኽ፡ምን፡ነበረች፧አንበሳ፡ነበረች፤በአንበሳዎች፡መካከል፡ተጋደመች፤በደቦል፡አንበሳዎች፡መካከል፡ ግልገሎቿን፡አሳደገች።
3ከግልገሎቿም፡አንዱን፡አወጣች፥ርሱም፡ደቦል፡አንበሳ፡ኾነ፤ንጥቂያንም፡ተማረ፥ሰዎችንም፡በላ።
4አሕዛብም፡ወሬውን፡ሰሙ፥ርሱም፡በጕድጓዳቸው፡ተያዘ፥በሰንሰለትም፡አድርገው፡ወደግብጽ፡ምድር፡ ወሰዱት።
5ርሷም፡እንደ፡ደከመችና፡ተስፋዋ፡እንደ፡ጠፋ፡ባየች፡ጊዜ፥ከግልገሎቿ፡ሌላን፡ወስዳ፡ደቦል፡አንበሳ፡ አደረገችው።
6ርሱም፡በአንበሳዎች፡መካከል፡ተመላለሰ፥ደቦል፡አንበሳም፡ኾነ፤ንጥቂያም፡ተማረ፥ሰዎችንም፡በላ።
7ግንቦቻቸውንም፡ዐወቀ፥ከተማዎቻቸውንም፡አፈረሰ፤ከግሣቱም፡ድምፅ፡የተነሣ፡ምድሪቱና፡ሞላዋ፡ጠፋች።
8አሕዛብም፡በዙሪያው፡ከየአገሩ፡ዅሉ፡ተሰበሰቡበት፤መረባቸውንም፡በርሱ፡ላይ፡ዘረጉ፥በጕድጓዳቸውም፡ ተያዘ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
9በሰንሰለትም፡አድርገው፡በቀፎ፡ውስጥ፡አኖሩት፥ወደባቢሎንም፡ንጉሥ፡አመጡት፤ድምፁም፡በእስራኤል፡ ተራራዎች፡ላይ፡ከዚያ፡ወዲያ፡እንዳይሰማ፡ወደ፡ዐምባ፡አገቡት።
10እናትኽ፡በመልክኽ፡በውሃ፡አጠገብ፡እንደ፡ተተከለች፡እንደ፡ወይን፡ግንድ፡ነበረች፤ከውሃም፡ብዛት፡ የተነሣ፡የምታፈራና፡የምትሰፋ፡ኾነች።
11ለርሷም፡ብርቱዎች፡በትሮች፡ነበሯት፤እነርሱም፡ለነገሥታት፡በትሮች፡ነበሩ።ቁመታቸውም፡በዛፎች፡ ቅርንጫፎች፡መካከል፡ረዘመ፥በጫፎቻቸውም፡ብዛትና፡በርዝመታቸው፡ታዩ።
12ነገር፡ግን፥በመዓት፡ተነቀለች፥ወደ፡መሬትም፡ተጣለች፥የምሥራቅም፡ነፋስ፡ፍሬዋን፡ አደረቀ፤ብርቱዎች፡በትሮቿም፡ተሰበሩና፡ደረቁ፥እሳትም፡በላቻቸው።
13አኹንም፡በምድረ፡በዳ፥በደረቅና፡በተጠማች፡መሬት፡ተተከለች።
14ከጫፎቿም፡በትሮች፡እሳት፡ወጣች፥ፍሬዋንም፡በላች፤የነገሥታትም፡በትር፡ይኾን፡ዘንድ፥የበረታ፡ በትር፡የለባትም።ይህ፡ሙሾ፡ነው፥ለልቅሶም፡ይኾናል።