Skip to content
← Ezekiel

Chapter 20 · Amharic

Ezekiel

1እንዲህም፡ኾነ፤በሰባተኛው፡ዓመት፡በዐምስተኛው፡ወር፡ከወሩም፡በዐሥረኛው፡ቀን፡እግዚአብሔርን፡ ይጠይቁ፡ዘንድ፡ከእስራኤል፡ሽማግሌዎች፡ዐያሌ፡ሰዎች፡መጡ፥በፊቴም፡ተቀመጡ።

2የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦

3የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ለእስራኤል፡ሽማግሌዎች፡ተናገር፥እንዲህም፡በላቸው፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ ይላል፦እኔን፡ትጠይቁ፡ዘንድ፡መጥታችዃልን፧እኔ፡ሕያው፡ነኝና፡በእናንተ፡ዘንድ፡አልጠየቅም፥ይላል፡ጌታ፡ እግዚአብሔር።

4ትፈርድባቸዋለኽን፧የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥በእውኑ፡ትፈርድባቸዋለኽን፧የአባቶቻቸውን፡ርኵሰት፡ አስታውቃቸው።

5እንዲህም፡በላቸው፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እስራኤልን፡በመረጥኹበት፡ለያዕቆብም፡ቤት፡ ዘር፡በማልኹበት፡ቀን፡በግብጽም፡ምድር፡በተገለጥኹላቸውና፦እኔ፡እግዚአብሔር፡አምላካችኹ፡ነኝ፡ብዬ፡ በማልኹላቸው፡ጊዜ፥

6በዚያ፡ቀን፡ከግብጽ፡ምድር፡ወዳዘጋጀኹላቸው፥ወተትና፡ማር፡ወደምታፈሰ፟ው፥የምድርም፡ዅሉ፡ጌጥ፡ ወደምትኾን፡ምድር፡አወጣቸው፡ዘንድ፡ማልኹላቸው፤

7እኔም፦ከእናንተ፡እያንዳንዱ፡የዐይኑን፡ርኵሰት፡ይጣል፥በግብጽም፡ጣዖታት፡አትርከሱ፤እኔ፡ እግዚአብሔር፡አምላካችኹ፡ነኝ፡አልዃቸው።

8እነርሱ፡ግን፡ዐመፁብኝ፡ይሰሙኝም፡ዘንድ፡አልወደዱም፥ዅሉም፡እያንዳንዱ፡የዐይኑን፡ርኵሰት፡ አልጣለም፡የግብጽንም፡ጣዖታት፡አልተወም፤በዚህም፡ጊዜ፦በግብጽ፡ምድር፡መካከል፡ቍጣዬን፡ እፈጽምባቸው፡ዘንድ፡መዓቴን፡አፈስ፟ባቸዋለኹ፡አልኹ።

9ነገር፡ግን፥በመካከላቸው፡ባሉ፡ከግብጽም፡ምድር፡አወጣቸው፡ዘንድ፡በፊታቸው፡በተገለጥኹላቸው፡ በአሕዛብ፡ፊት፡ስሜ፡እንዳይረክስ፡ብዬ፡ስለ፡ስሜ፡ሠራኹ።

10ከግብጽም፡ምድር፡አወጣዃቸው፡ወደ፡ምድረ፡በዳም፡አመጣዃቸው።

11ሰው፡ቢያደርገው፡ኖሮ፡በሕይወት፡የሚኖርበትን፡ሥርዐቴንም፡ሰጠዃቸው፥ፍርዴንም፡አስታወቅዃቸው።

12የምቀድሳቸውም፡እኔ፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ያውቁ፡ዘንድ፥በእኔና፡በእነርሱ፡መካከል፡ምልክት፡ ይኾኑ፡ዘንድ፡ሰንበታቴን፡ሰጠዃቸው።

13ነገር፡ግን፥የእስራኤል፡ቤት፡በምድረ፡በዳ፡ዐመፁብኝ፤ሰው፡ቢያደርገው፡ኖሮ፡በሕይወት፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org የሚኖርበትንም፡ፍርዴን፡ጣሱ፥በትእዛዜም፡አልኼዱም፥ሰንበታቴንም፡ፈጽመው፡አረከሱ።በዚህም፡ ጊዜ፦አጠፋቸው፡ዘንድ፡ቍጣዬን፡በምድረ፡በዳ፡አፈስ፟ባቸዋለኹ፡አልኹ።

14ነገር፡ግን፥በፊታቸው፡ባወጣዃቸው፡በአሕዛብ፡ፊት፡ስሜ፡እንዳይረክስ፡ብዬ፡ስለ፡ስሜ፡ሠራኹ።

15ወተትና፡ማርም፡ወደምታፈሰ፟ው፡የምድር፡ዅሉ፡ጌጥ፡ወደምትኾን፡ወደሰጠዃቸው፡ምድር፡ አላመጣቸውም፡ብዬ፡በምድረ፡በዳ፡ማልኹባቸው።

16ልባቸው፡ጣዖቶቻቸውን፡ተከትሏልና፤ፍርዴንም፡ጥሰዋልና፥በሥርዐቴም፡አልኼዱምና፥ሰንበታቴንም፡ አርክሰዋልና።

17ነገር፡ግን፥ዐይኔ፡ራራችላቸው፡እኔም፡አላጠፋዃቸውም፥በምድረ፡በዳም፡ፈጽሜ፡አልፈጀዃቸውም።

18ለልጆቻቸውም፡በምድረ፡በዳ፡እንዲህ፡አልዃቸው፦በአባቶቻችኹ፡ሥርዐት፡አትኺዱ፥ወጋቸውንም፡ አትጠብቁ፥በጣዖቶቻቸውም፡አትርከሱ።

19እኔ፡እግዚአብሔር፡አምላካችኹ፡ነኝ፤በትእዛዜ፡ኺዱ፡ፍርዴንም፡ጠብቁ፡አድርጓትም።

20ሰንበታቴንም፡ቀድሱ፤እኔም፡እግዚአብሔር፡አምላካችኹ፡እንደ፡ኾንኹ፡ታውቁ፡ዘንድ፡በእኔና፡በእናንተ፡ መካከል፡ምልክት፡ይኾናሉ።

21ልጆች፡ግን፡ዐመፁብኝ፥ሰው፡ቢያደርገው፡ኖሮ፡በሕይወት፡የሚኖርባትን፡ፍርዴን፡ጠብቀው፡ አላደረጓትም፡በሥርዐቴም፡አልኼዱም፥ሰንበታቴንም፡አረከሱ፤በዚህም፡ጊዜ፦መዓቴን፡አፈስ፟ባቸዋለኹ፡ ቍጣዬንም፡በምድረ፡በዳ፡እፈጽምባቸዋለኹ፡አልኹ።

22ነገር፡ግን፥እጄን፡መለስኹ፥በፊታቸውም፡ባወጣዃቸው፡በአሕዛብ፡ፊት፡ስሜ፡እንዳይረክስ፡ብዬ፡ስለ፡ ስሜ፡ሠራኹ።

23ደግሞም፡ወደ፡አሕዛብ፡እበትናቸው፡ዘንድ፥በአገሮችም፡እበትናቸው፡ዘንድ፡በምድረ፡በዳ፡ ማልኹባቸው፤ፍርዴን፡አላደረጉምና፤

24ሥርዐቴንም፡ጥሰዋልና፤ሰንበታቴንም፡አርክሰዋልና፤ዐይናቸውም፡የአባቶቻቸውን፡ጣዖታቶች፡ተከትለዋልና።

25ደግሞም፡መልካም፡ያልኾነውን፡ሥርዐት፡በሕይወት፡የማይኖሩበትንም፡ፍርድ፡ሰጠዃቸው።

26እኔም፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡እንዲያውቁ፡አጠፋቸው፡ዘንድ፥ማሕፀን፡የሚከፍተውን፡ዅሉ፡ በእሳት፡ባሳለፉ፡ጊዜ፥በመባቸው፡አረከስዃቸው።

27ስለዚህ፥የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ለእስራኤል፡ቤት፡ተናገር፡እንዲህም፡በላቸው፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ ይላል፦በዚህም፡ደግሞ፡አባቶቻችኹ፡ባደረጉት፡ዐመፅ፡አስቈጡኝ።

28እሰጣቸውም፡ዘንድ፡ወደማልኹላቸው፡ምድር፡ባገባዃቸው፡ጊዜ፥ከፍ፡ያለውን፡ኰረብታ፡ዅሉ፡ ቅጠልማውንም፡ዛፍ፡ዅሉ፡አዩ፥በዚያም፡መሥዋዕታቸውን፡ሠዉ፡በዚያም፡የሚያስቈጣኝን፡ቍርባናቸውን፡ አቀረቡ፡በዚያም፡ደግሞ፡ጣፋጩን፡ሽታቸውን፡አደረጉ፡በዚያም፡የመጠጥ፡ቍርባናቸውን፡አፈሰሱ።

29እኔም፦እናንተ፡ወደ፡ርሱ፡የምትኼዱበት፡ከፍታ፡ምንድር፡ነው፧አልዃቸው።እስከ፡ዛሬም፡ድረስ፡ ስሙ፡ባማ፡ተብሎ፡ተጠርቷል።

30ስለዚህ፥ለእስራኤል፡ቤት፡እንዲህ፡በላቸው፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንደ፡አባቶቻችኹ፡ ልማድ፡ትረክሳላችኹን፧ርኵሰታቸውንም፡ተከትላችኹ፡ታመነዝራላችኹን፧

31ቍርባናችኹን፡ባቀረባችኹ፡ጊዜ፥ልጆቻችኹንም፡በእሳት፡ባሳለፋችኹ፡ጊዜ፥እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡ በጣዖቶቻችኹ፡ትረክሳላችኹን፡የእስራኤል፡ቤት፡ሆይ፥ከናንተስ፡ዘንድ፡እጠየቃለኹን፧እኔ፡ሕያው፡ነኝና፡ ከእናንተ፡ዘንድ፡አልጠየቅም፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር፤

32ለእናንተም፦እንደ፡አሕዛብና፡እንደምድር፡ወገኖች፡እንኾናለን፥ዕንጨትና፡ድንጋይም፡እናመልካለን፡ የሚል፡ከልባችኹ፡የወጣ፡ዐሳብ፡አይፈጸምላችኹም። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

33እኔ፡ሕያው፡ነኝና፡በበረታች፡እጅና፡በተዘረጋች፡ክንድ፡በፈሰሰችም፡መዓት፡እነግሥባችዃለኹ፥ይላል፡ ጌታ፡እግዚአብሔር።

34ከአሕዛብም፡ዘንድ፡አወጣችዃለኹ፡ከተበተናችኹባትም፡አገር፡ዅሉ፡በበረታች፡እጅና፡በተዘረጋች፡ክንድ፡ በፈሰሰችም፡መዓት፡እሰበስባችዃለኹ።

35ወደአሕዛብም፡ምድረ፡በዳ፡አመጣችዃለኹ፡በዚያም፡ፊት፡ለፊት፡ከእናንተ፡ጋራ፡እፋረዳለኹ።

36በግብጽ፡ምድረ፡በዳ፡ከአባቶቻችኹ፡ጋራ፡እንደ፡ተፋረድኹ፡እንዲሁ፡ከእናንተ፡ጋራ፡ እፋረዳለኹ፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።

37ከበትርም፡በታች፡አሳልፋችዃለኹ፡ወደቃል፡ኪዳንም፡እስራት፡አገባችዃለኹ፤

38ከእናንተም፡ዘንድ፡ዐመፀኛዎችንና፡የበደሉኝን፡እለያለኹ፤ከኖሩባትም፡ምድር፡ አወጣቸዋለኹ፥ወደእስራኤል፡ምድር፡ግን፡አይገቡም፤እኔም፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ታውቃላችኹ።

39ጌታ፡እግዚአብሔርም፡እንዲህ፡ይላል፦እናንተ፡የእስራኤል፡ቤት፡ሆይ፥ኺዱ፥ከዚህም፡በዃላ፡ ትሰሙኝ፡ዘንድ፡ባትወዱ፡ዅላችኹ፡ጣዖቶቻችኹን፡አምልኩ።ነገር፡ግን፥ከእንግዲህ፡ወዲህ፡በቍርባናችኹና፡ በጣዖቶቻችኹ፡ቅዱሱን፡ስሜን፡አታረክሱም።

40በቅዱሱ፡ተራራዬ፥ከፍ፡ባለው፡በእስራኤል፡ተራራ፡ላይ፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር፥በዚያ፡የእስራኤል፡ ቤት፡ዅሉ፡ዅላቸው፡በምድሩ፡ላይ፡ያመልኩኛል፤በዚያም፡እቀበላቸዋለኹ፥በዚያም፡ቍርባናችኹን፡ በኵራታችኹንም፡የቀደሳችኹትንም፡ነገር፡ዅሉ፡እፈልጋለኹ።

41ከአሕዛብም፡ዘንድ፡ባወጣዃችኹ፡ጊዜ፡ከተበተናችኹባትም፡አገር፡ዅሉ፡በሰበሰብዃችኹ፡ጊዜ፡እንደ፡ ጣፋጭ፡ሽታ፡እቀበላችዃለኹ፥በአሕዛብም፡ፊት፡እቀደስባችዃለኹ።

42ለአባቶቻችኹም፡እሰጣት፡ዘንድ፡ወደማልኹላቸው፡ምድር፡ወደእስራኤል፡አገር፡ባገባዃችኹ፡ጊዜ፥እኔ፡ እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ታውቃላችኹ።

43በዚያም፡የረከሳችኹባትን፡መንገዳችኹንና፡ሥራችኹን፡ዅሉ፡ታስባላችኹ፤ስለ፡ሠራችኹትም፡ክፋታችኹ፡ ዅሉ፡ራሳችኹን፡ትጸየፋላችኹ።

44የእስራኤል፡ቤት፡ሆይ፥እንደ፡ክፉ፡መንገዳችኹና፡እንደ፡ርኩስ፡ሥራችኹ፡ሳይኾን፡ስለ፡ስሜ፡ስል፡ በሠራኹላችኹ፡ጊዜ፥እኔ፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ታውቃላችኹ፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።

45የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦

46የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ፊትኽን፡ወደ፡ደቡብ፡አቅና፡ወደ፡ደቡብም፡ተናገር፡በደቡብም፡ባለው፡ዱር፡ላይ፡ ትንቢት፡ተናገር፤

47ለደቡብም፡ዱር፦የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ስማ፤ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥ባንተ፡ ውስጥ፡እሳት፡አነዳ፟ለኹ፤በውስጥኽም፡ያለውን፡የለመለመውንና፡የደረቀውን፡ዛፍ፡ዅሉ፡ይበላል፤የሚቃጠል፡ ነበልባል፡አይጠፋም፤ከደቡብም፡ዠምሮ፡እስከ፡ሰሜን፡ድረስ፡ፊት፡ዅሉ፡ይቃጠልበታል።

48እኔም፡እግዚአብሔር፡እንዳነደድኹት፡ሥጋ፡ለባሽ፡ዅሉ፡ያያል፥ርሱም፡አይጠፋም፡በለው።

49እኔም፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡ሆይ፥ወዮ! እነርሱ፡ስለ፡እኔ፦ይህ፡ምሳሌን፡የሚመስል፡ አይደለምን፧ብለዋል፡አልኹ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source