Skip to content
← Ezekiel

Chapter 21 · Amharic

Ezekiel

1የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦

2የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ፊትኽን፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡አቅና፡ወደ፡መቅደሶችም፡ተናገር፡በእስራኤልም፡ምድር፡ ላይ፡ትንቢት፡ተናገር። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

3ለእስራኤልም፡ምድር፡እንዲህ፡በል፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥ባንተ፡ላይ፡ነኝ፥ሰይፌንም፡ ከሰገባው፡እመዘ፟ዋለኹ፥ጻድቁንና፡ክፉውንም፡ከአንተ፡ዘንድ፡አጠፋለኹ።

4እኔም፡ጻድቁንና፡ክፉውን፡ከአንተ፡ዘንድ፡ስለማጠፋ፥ስለዚህ፡ሰይፌ፡ከደቡብ፡ዠምሮ፡እስከ፡ሰሜን፡ ድረስ፡ባለ፡በሥጋ፡ለባሽ፡ዅሉ፡ላይ፡ከሰገባው፡ይመዘዛል።

5ሥጋ፡ለባሹም፡ዅሉ፡እኔ፡እግዚአብሔር፡ሰይፌን፡ከሰገባው፡እንደ፡መዘዝኹ፡ያውቃል፥ርሱም፡ደግሞ፡ አይመለስም።

6ስለዚህም፥አንተ፡የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥አልቅስ፤ወገብኽን፡በማጕበጥ፡በፊታቸው፡ምርር፡ብለኽ፡አልቅስ።

7እነርሱም፦ስለ፡ምን፡ታለቅሳለኽ፧ቢሉኽ፥አንተ፡እንዲህ፡በላቸው፦ወሬ፡ስለሚመጣ፡ነው፤ልብም፡ ዅሉ፡ይቀልጣል፥እጆችም፡ዅሉ፡ይዝላሉ፥ነፍስም፡ዅሉ፡ትደክማለች፥ጕልበትም፡እንደ፡ውሃ፡ ይፈሳ፟ል፤እንሆ፥ይመጣል፡ይፈጸምማል፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።

8የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦

9የሰው፡ልጅ፡ሆይ፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፡ብለኽ፡ትንቢት፡ተናገር፤ሰይፍ፡ሰይፍ፡የተሳለ፡ የተሰነገለም፡ነው፡በል።

10ይገድል፡ዘንድ፡ተስሏል፡ያብረቀርቅም፡ዘንድ፡ተሰንግሏል፤እኛስ፡ደስ፡ይለናልን፧የልጄን፡በትር፡እንደ፡ ዛፍ፡ዅሉ፡ንቆታል።

11በእጁም፡እንዲያዝ፡ለመሰንገል፡ተሰጠ፤ሰይፍ፡በገዳይ፡እጅ፡እንዲሰጥ፡ተሳለና፡ተሰነገለ።

12የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥በሕዝቤ፡ላይ፡ነውና፥በእስራኤል፡አለቃዎች፡ዅሉ፡ላይ፡ነውና፥ጩኽ፡ዋይም፡ በል፤እነርሱ፡ከሕዝቤ፡ጋራ፡ለሰይፍ፡ተሰጥተዋል፤ስለዚህ፥ጭንኽን፡ጽፋ።

13ፈተና፡ደርሷል፤የተናቀ፡በትርስ፡ደግሞ፡ባይኖር፡ምንድር፡ነው፧ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።

14ስለዚህ፥አንተ፡የሰው፡ልጅ፥ትንቢት፡ተናገር፥እጅኽን፡አጨብጭብ፤የተገደሉ፡ሰዎች፡ሰይፍ፡ሦስት፡ ጊዜ፡ይደጋግም፡የሚከባ፟ቸው፡የተገደለ፡የታላቅ፡ሰው፡ሰይፍ፡ነው።

15ልባቸው፡እንዲቀልጥ፡መሰናክላቸውም፡እንዲበዛ፡የሚገድለውን፡ሰይፍ፡በበሮቻቸው፡ዅሉ፡ላይ፡ አድርጌያለኹ፤ወዮ! ያብረቀርቅ፡ዘንድ፡ተሰንግሏል፡ይገድልም፡ዘንድ፡ተስሏል።

16ተዘጋጅተኽ፡ፊትኽ፡ወደወደደው፡ወደ፡ቀኝ፡ወይም፡ወደ፡ግራ፡ኺድ።

17እኔ፡ደግሞ፡በእጄ፡አጨበጭባለኹ፡መዓቴንም፡እጨርሳለኹ፤እኔ፡እግዚአብሔር፡ተናግሬያለኹ።

18የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦

19አንተም፡የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥የባቢሎን፡ንጉሥ፡ሰይፍ፡ይመጣ፡ዘንድ፡ኹለት፡መንገዶችን፡ አድርግ፤ኹለቱም፡ከአንዲት፡ምድር፡ይውጡ፤ምልክትም፡አድርግ፥በከተማዪቱ፡መንገድ፡ራስ፡ላይ፡ አድርገው።

20ሰይፍ፡ወደዐሞን፡ልጆች፡አገር፡ወደ፡ረባት፡ወደ፡ይሁዳም፡ወደተመሸገች፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡ይመጣ፡ ዘንድ፡መንገድን፡አድርግ።

21የባቢሎን፡ንጉሥ፡ሟርቱን፡ያሟርት፡ዘንድ፡በመንታ፡መንገድ፡ላይ፡በኹለቱ፡መንገዶች፡ራስ፡ላይ፡ቆሞ፡ ነበር፤ፍላጻዎችን፡ወዘወዘ፥ከተራፊምም፡ጠየቀ፥ጕበትም፡ተመለከተ።

22የቅጥሩን፡ማፍረሻ፡ያደርግ፡ዘንድ፥አፍንም፡በጩኸት፡ይከፍት፡ዘንድ፥በውካታም፡ድምፅን፡ከፍ፡ ያደርግ፡ዘንድ፥የቅጥሩን፡ማፍረሻ፡በበሮች፡ላይ፡ያደርግ፡ዘንድ፥ዐፈርን፡ይደለድል፡ዘንድ፥ምሽግም፡ይሠራ፡ ዘንድ፡የኢየሩሳሌም፡ዕጣ፡በቀኝ፡እጁ፡ውስጥ፡ነበረ።

23መሐላውንም፡በማሉ፡በዐይናቸው፡ዘንድ፡የሐሰት፡ሟርት፡ይመስላል፥ነገር፡ግን፥እነርሱ፡ይያዙ፡ዘንድ፡ ርሱ፡ኀጢአትን፡ያሳስባል። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

24ስለዚህ፥ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ኀጢአታችኹን፡ስላሰባችኹ፥መተላለፋችኹም፡ስለ፡ ተገለጠ፥ኀጢአታችኹም፡በሥራችኹ፡ዅሉ፡ስለ፡ታየ፥እናንተም፡ስለ፡ታሰባችኹ፥በእጅ፡ትያዛላችኹ።

25አንተም፡ቀንኽ፡የደረሰብኽ፥የኀጢአትኽ፡ቀጠሮ፡ጊዜ፡የደረሰብኽ፥ርኩስ፡ኀጢአተኛ፡የእስራኤል፡አለቃ፡ ሆይ፥

26ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦መጠምጠሚያውን፡አውልቅ፥ዘውዱንም፡አርቅ፤ይህ፡እንዲህ፡ አይኾንም፤የተዋረደውን፡ከፍ፡አድርግ፥ከፍ፡ያለውንም፡አዋርድ።

27ባድማ፥ባድማ፥ባድማ፡አደርጋታለኹ፤ፍርድ፡ያለው፡እስኪመጣ፡ድረስ፡ይህች፡ደግሞ፡ አትኾንም፥ለርሱም፡እሰጣታለኹ።

29አንተም፡የሰው፡ልጅ፡ሆይ፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡ስለዐሞን፡ልጆችና፡ስለ፡ስድባቸው፡እንዲህ፡ ይላል፡ብለኽ፡ትንቢት፡ተናገር፤ቀናቸው፡በደረሰ፥የኀጢአታቸው፡ቀጠሮ፡ጊዜ፡በደረሰ፥በተገደሉት፡ ኀጢአተኛዎች፡ዐንገት፡ላይ፡ያኖሩኽ፡ዘንድ፡ከንቱን፡ራእይ፡ነገር፡ሲያዩልኽ፡በሐሰትም፡ሟርት፡ ሲናገሩልኽ፦ሰይፍ፥ሰይፍ፡ተመዟ፟ል፥ይገድልም፡ዘንድ፡ያብረቀርቅም፡ዘንድ፡ተሰንግሏል፡በል።

30ወደ፡ሰገባውም፡መልሰው፦በተፈጠርኽበት፡ስፍራ፡በተወለድኽባትም፡ምድር፡እፈርድብኻለኹ።

31ቍጣዬንም፡አፈስ፟ብኻለኹ፥በመዓቴም፡እሳት፡አናፋብኻለኹ፥ማጥፋትንም፡ለሚያውቁ፡ለጨካኞች፡ሰዎች፡ እጅ፡አሳልፌ፡እሰጥኻለኹ።

32ለእሳት፡ማገዶ፡ትኾናለኽ፥ደምኽም፡በምድር፡መካከል፡ይኾናል፥ደግሞም፡አትታሰብም፤እኔ፡ እግዚአብሔር፡ተናግሬያለኹና።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source