Skip to content
← Ezekiel

Chapter 22 · Amharic

Ezekiel

1የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦

2አንተም፡የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ትፈርዳለኽን፧ደም፡በምታፈስ፟፡ከተማ፡ላይ፡ትፈርዳለኽን፧ርኵሰቷን፡ዅሉ፡ አስታውቃት።

3እንዲህም፡በል፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ጊዜሽ፡እንዲደርስ፡በመካከልሽ፡ደምን፡የምታፈሺ፟፡ እንድትረክሺም፡በራስሽ፡ላይ፡ጣዖታትን፡የምታደርጊ፡ከተማ፡ሆይ!

4ባፈሰስሽው፡ደም፡በድለሻል፥ባደረግሽውም፡ጣዖታት፡ረክሰሻል፤ቀንሽን፡አቀረብሽ፥ዘመንሽንም፡ አሳጠርሽ፤ስለዚህ፥ለአሕዛብ፡መሰደቢያ፥ለአገሮችም፡ዅሉ፡መሳለቂያ፡አደረግኹሽ።

5አንቺ፡ስምሽ፡የረከሰ፡ሽብርም፡የሞላብሽ፡ሆይ፥ወደ፡አንቺ፡የቀረቡና፡ከአንቺ፡የራቁ፡ይሣለቁብሻል።

6እንሆ፥የእስራኤል፡አለቃዎች፡እያንዳንዱ፡እንደ፡ችሎቱ፡ደም፡ያፈሱ፟፡ዘንድ፡ባንቺ፡ውስጥ፡ነበሩ።

7ባንቺ፡ውስጥ፡አባትንና፡እናትን፡አቃለሉ፤በመካከልሽ፡በመጻተኛው፡ላይ፡በደልን፡አደረጉ፤ባንቺ፡ውስጥ፡ ድኻ፡አደጉንና፡መበለቲቱን፡አስጨነቁ።

8ቅድሳቴንም፡ናቅሽ፡ሰንበታቴንም፡አረከ፟ሽ።

9ደምን፡ያፈሱ፟፡ዘንድ፥ቀማኛዎች፡ሰዎች፡ባንቺ፡ውስጥ፡ነበሩ፤ባንቺ፡ውስጥ፡በተራራዎች፡ላይ፡ በሉ፤በመካከልሽ፡ሴሰኝነትን፡አደረጉ።

10ባንቺ፡ውስጥ፡የአባቶቻቸውን፡ኀፍረተ፡ሥጋ፡ገለጡ፤ባንቺም፡ውስጥ፡አደፍ፡ያለባትን፡አዋረዱ።

11ሰውም፡በባልንጀራው፡ሚስት፡ርኵሰትን፡አደረገ፥አባትም፡የልጁን፡ሚስት፡አረከሰ፥ባንቺም፡ዘንድ፡ ወንድም፡የአባቱን፡ልጅ፡እኅቱን፡አሳፈረ።

12ባንቺ፡ውስጥ፡ደምን፡ያፈሱ፟፡ዘንድ፥ጕቦን፡ተቀበሉ፤አንቺም፡ዐራጣና፡ትርፍ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ወስደሻል፥ከባልንጀራዎችሽም፡በቅሚያ፡የሥሥትን፡ትርፍ፡አገኘሽ፥እኔንም፡ረሳሽኝ፥ይላል፡ጌታ፡ እግዚአብሔር።

13ስለዚህ፥እንሆ፥አንቺ፡ባደረግሽው፡ሥሥት፡በመካከልሽም፡በነበረው፡ደም፡ላይ፡እጄን፡አጨበጨብኹ።

14በእውኑ፡እኔ፡በማደርግብሽ፡ወራት፡ልብሽ፡ይታገሣልን፧ወይስ፡እጅሽ፡ትጸናለችን፧እኔ፡እግዚአብሔር፡ ተናግሬያለኹ፥አደርገውማለኹ።

15ወደ፡አሕዛብም፡እበትንሻለኹ፡ወደ፡አገሮችም፡እዘራሻለኹ፥ርኵሰትሽንም፡ከአንቺ፡ዘንድ፡አጠፋለኹ።

16በአሕዛብም፡ፊት፡አንቺ፡ትረክሻለሽ፡እኔም፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ታውቂያለሽ።

17የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦

18የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥የእስራኤል፡ቤት፡ለእኔ፡እንደ፡አተላ፡ኾኑብኝ፤እነርሱ፡ዅሉ፡በከውር፡ውስጥ፡ መዳብና፡ቈርቈሮ፡ብረትና፡ርሳስ፡ናቸው፤የብር፡አተላ፡ናቸው።

19ስለዚህ፥ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ዅላችኹ፡አተላ፡ ኾናችዃልና፥ስለዚህ፥እንሆ፥በኢየሩሳሌም፡ውስጥ፡እሰበስባችዃለኹ።

20እንዲያቀልጡት፡እሳት፡ያናፉበት፡ዘንድ፥ብርንና፡መዳብን፡ብረትንና፡ርሳስን፡ቈርቈሮንም፡በከውር፡ እንደሚሰበስቡ፥እንዲሁ፡በቍጣዬና፡በመዓቴ፡እሰበስባችዃለኹ፥በዚያም፡ውስጥ፡እጨምራችዃለኹ፡ አቀልጣችኹማለኹ።

21እሰበስባችኹማለኹ፡የመዓቴንም፡እሳት፡አና፟ፋ፟ባችዃለኹ፡በውስጡም፡ትቀልጣላችኹ።

22ብርም፡በከውር፡ውስጥ፡እንደሚቀልጥ፥እንዲሁ፡በውስጧ፡ትቀልጣላችኹ፤እኔም፡እግዚአብሔር፡ መዓቴን፡እንዳፈሰስኹባችኹ፡ታውቃላችኹ።

23የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦

24የሰው፡ልጅ፡ሆይ፦አንቺ፡ያልነጻሽ፡በቍጣም፡ቀን፡ያልዘነበብሽ፡ምድር፡ነሽ፡በላት።

25በውስጧ፡ያሉ፡ነቢያት፡እንደሚጮኽና፡እንደሚናጠቅ፡አንበሳ፡አንድ፡ኾነው፡ተማማሉ፤ነፍሶችን፡ በልተዋል፥ብልጥግናና፡ሀብትን፡ወስደዋል፥በውስጧም፡መበለቶችን፡አብዝተዋል።

26ካህናቷም፡ሕጌን፡በድለዋል፡ቅድሳቴንም፡አርክሰዋል፤ቅዱስ፡በኾነና፡ቅዱስ፡ባልኾነ፡መካከልም፡ አልለዩም፥በንጹሕና፡በርኩስ፡መካከል፡ያለውን፡ልዩነት፡አላስታወቁም፤ዐይናቸውንም፡ከሰንበታቴ፡ሰወሩ፡እኔም፡ በመካከላቸው፡ረከስኹ።

27በውስጧ፡ያሉ፡አለቃዎቿ፡የሥሥትን፡ትርፍ፡ለማግኘት፡ሲሉ፡ደምን፡ያፈሱ፟፡ዘንድ፥ነፍሶችንም፡ያጠፉ፡ ዘንድ፥እንደሚናጠቁ፡ተኵላዎች፡ናቸው።

28እግዚአብሔርም፡ሳይናገር፡ነቢያቷ፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፡እያሉ፡ከንቱን፡ራእይ፡በማየት፡ የሐሰትንም፡ሟርት፡ለእነርሱ፡በማሟረት፡ያለገለባ፡በጭቃ፡ይመርጓቸዋል።

29የምድርን፡ሕዝብ፡ግፍ፡አደረጉ፡ቅሚያም፡ሠሩ፤ድኻዎችንና፡ችግረኛዎችን፡አስጨነቁ፥መጻተኛውንም፡ በደሉ።

30ቅጥርን፡የሚጠግንን፥ምድሪቱንም፡እንዳላጠፋት፡በፈረሰበት፡በኩል፡በፊቴ፡የሚቆምላትን፡ሰው፡ በመካከላቸው፡ፈለግኹ፥ነገር፡ግን፥አላገኘኹም።

31ስለዚህ፥ቍጣዬን፡አፈሰስኹባቸው፥በመዓቴም፡እሳት፡አጠፋዃቸው፤መንገዳቸውንም፡በራሳቸው፡ላይ፡ መለስኹ፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source