1የእግዚአብሔር፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
2የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥የአንዲት፡እናት፡ልጆች፡የኾኑ፡ኹለት፡ሴቶች፡ነበሩ።
3በግብጽም፡አመነዘሩ፥በኰረዳነታቸው፡አመነዘሩ፤በዚያ፡ጡቶቻቸው፡ሟሸሹ፡በዚያም፡የድንግልናቸውን፡ ጡቶች፡ዳበሱ።
4ስማቸውም፡የታላቂቱ፡ኦሖላ፡የእኅቷም፡ኦሖሊባ፡ነበረ፥ለኔም፡ኾኑ፡ወንዶችና፡ሴቶች፡ልጆችንም፡ ወለዱ።ስማቸውም፡ኦሖላ፡ሰማርያ፡ናት፤ኦሖሊባ፡ደግሞ፡ኢየሩሳሌም፡ናት።
5ኦሖላም፡ገለሞተችብኝ፥ውሽማዎቿንም፡ጎረቤቶቿን፡አሶራውያንን፡በፍቅር፡ተከተለቻቸው።
6እነርሱም፡ሰማያዊ፡ሐር፡የለበሱ፡አለቃዎችና፡ሹማምቶች፥መልከ፡መልካሞች፡ጐበዛዝት፥በፈረስ፡ላይ፡ የሚቀመጡ፡ፈረሰኛዎች፡ነበሩ።
7ግልሙትናዋንም፡ከተመረጡ፡ከአሶር፡ሰዎች፡ዅሉ፡ጋራ፡አደረገች፥በፍቅር፡በተከተለቻቸውም፡ ጣዖቶቻቸው፡ዅሉ፡ረከሰች።
8በግብጽም፡የነበረውን፡ግልሙትናዋን፡አልተወችም፤በዚያ፡በኰረዳነቷ፡ጊዜ፡ከርሷ፡ጋራ፡ተኝተው፡ ነበር፥የድንግልናዋንም፡ጡቶች፡ዳብሰው፡ነበር፥ግልሙትናቸውንም፡አፍሰ፟ውባት፡ነበር።
9ስለዚህ፥በፍቅር፡በተከተለቻቸው፣በውሽማዎቿ፣በአሶራውያን፡እጅ፡አሳልፌ፡ሰጠዃት።
10እነርሱም፡ኅፍረተ፡ሥጋዋን፡ገለጡ፤ወንዶችና፡ሴቶች፡ልጆቿንም፡ማርከው፡ወሰዱ፥ርሷንም፡በሰይፍ፡ ገደሉ፤ፍርድንም፡ስላደረጉባት፡በሴቶች፡መካከል፡መተረቻ፡ኾነች።
11እኅቷም፡ኦሖሊባ፡ይህን፡አየች፤ኾኖም፡ከርሷ፡ይልቅ፡በፍቅር፡በመከተሏ፡ረከሰች፥ግልሙትናዋም፡ ከእኅቷ፡ግልሙትና፡ይልቅ፡በዛ።
12አለቃዎችንና፡ሹማምቶችን፡ጎረቤቶቿን፡ጌጠኛ፡ልብስ፡የለበሱትን፡በፈረሶች፡ላይ፡የሚቀመጡትን፡ ፈረሰኛዎች፥ዅሉም፡መልከ፡መልካሞችን፡ጐበዛዝት፡አሶራውያንን፡በፍቅር፡ተከተለቻቸው።
13የረከሰችም፡እንደ፡ኾነች፡አየኹ፥ኹለቱም፡አንድ፡መንገድ፡ኼደዋል።
14ግልሙትናዋንም፡አበዛች፤በቀይ፡ቀለምም፡የተሳለችውን፡የከለዳውያንን፡ሥዕል፥በናስ፡ላይ፡የተሳሉትን፡ ሰዎች፡አየች።
15በወገባቸው፡ዝናር፡የታጠቁ፡ራሳቸውንም፡በቀለማዊ፡መጠምጠሚያ፡የጠመጠሙ፡ነበሩ፤ዅሉም፡ ከተወለዱባት፡አገር፡የኾኑትን፡የከለዳውያንን፡ልጆች፡መስለው፡መሳፍንትን፡ይመስሉ፡ነበር።
16ባየቻቸውም፡ጊዜ፡በፍቅር፡ተከተለቻቸው፥ወደከላውዴዎን፡ምድር፡ወደ፡እነርሱ፡መልእክተኛዎችን፡ ላከች።
17የባቢሎንም፡ሰዎች፡ወደ፡ርሷ፡ፍቅር፡ወዳለበት፡መኝታ፡መጡ፡በግልሙትናቸውም፡አረከሷት፤ርሷም፡ ከነርሱ፡ጋራ፡ረከሰች፡ነፍሷም፡ከነርሱ፡ተለየች።
18ግልሙትናዋንም፡ገለጠች፡ኅፍረተ፡ሥጋዋንም፡አሳየች፤ነፍሴም፡ከእኅቷ፡እንደ፡ተለየች፡እንዲሁ፡ነፍሴ፡ ከርሷ፡ተለየች።
19ነገር፡ግን፥በግብጽ፡ምድር፡የገለሞተችበትን፡የኰረዳነቷን፡ዘመን፡ዐስባ፡ግልሙትናዋን፡አበዛች።
20ሥጋቸውም፡እንደ፡አህያዎች፡ሥጋ፡ዘራቸውም፡እንደ፡ፈረሶች፡ዘር፡የኾነውን፡እነዚያን፡ምልምሎች፡ በፍቅር፡ተከተለቻቸው።
21ስለኰረዳነትሽ፡ምክንያት፡ግብጻውያን፡ጡቶችሽን፡በዳበሱ፡ጊዜ፡የኰረዳነትሽን፡ሴሰኝነት፡ዐሰብሽ።
22ስለዚህ፥ኦሖሊባ፡ሆይ፥ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ነፍስሽ፡ከነርሱ፡የተለየች፡ውሽማዎችሽን፡ አስነሣብሻለኹ፥በዙሪያሽም፡ባንቺ፡ላይ፡አመጣቸዋለኹ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
23እነርሱም፡የባቢሎን፡ሰዎች፡ከለዳውያንም፡ዅሉ፥ፋቁድ፥ሱሔ፥ቆዓ፥ከነርሱም፡ጋራ፡አሶራውያን፡ ዅሉ፥መልከ፡መልካሞች፡ጐበዛዝት፥አለቃዎችና፡ሹማምቶች፡ዅሉ፥መሳፍንቶችና፡አማካሪዎች፡ ዅሉ፥በፈረስ፡ላይ፡የተቀመጡ፡ናቸው።
24በመሣሪያና፡በሠረገላ፡በመንኰራኵርም፡በአሕዛብም፡ጉባኤ፡ይመጡብሻል፤ጋሻና፡አላባሽ፡ጋሻ፡ራስ፡ ቍርም፡ይዘው፡በዙሪያሽ፡ይዘጋጁብሻል፤ፍርድንም፡እሰጣቸዋለኹ፥እንደ፡ፍርዳቸውም፡ይፈርዱብሻል።
25ቅንአቴንም፡ባንቺ፡ላይ፡አደርጋለኹ፡በመዓትም፡ያደርጉብሻል፤አፍንጫሽንና፡ዦሮሽንም፡ከአንቺ፡ ይቈርጣሉ፥ከአንቺም፡የቀረ፡በሰይፍ፡ይወድቃል፤ወንዶችና፡ሴቶች፡ልጆችሽንም፡ማርከው፡ ይወስዳሉ፥ከአንቺም፡የቀረውን፡እሳት፡ትበላቸዋለች።
26ልብስሽንም፡ይገፉ፟ሻል፥የክብርሽንም፡ጌጥ፡ይወስዳሉ።
27ሴሰኝነትሽንም፥ከግብጽ፡ምድር፡ያወጣሽውን፡ግልሙትናሽንም፡ከአንቺ፡አስቀራለኹ፤ዐይንሽንም፡ወደ፡ እነርሱ፡አታነሺም፡ግብጽንም፡ከዚያ፡ወዲያ፡አታስቢም።
28ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላልና፦እንሆ፥በጠላሻቸው፡እጅ፥ነፍስሽ፡በተለየቻቸው፡እጅ፡አሳልፌ፡ እሰጥሻለኹ፤
29እነርሱም፡በጥል፡ያደርጉብሻል፥የደከምሽበትንም፡ዅሉ፡ይወስዳሉ፥ዕራቍትሽንና፡ዕርቃንሽን፡አድርገውም፡ ይተዉሻል፤የግልሙትናሽም፡ነውር፥ሴሰኝነትሽና፡ግልሙትናሽም፡ዅሉ፡ይገለጣል።
30ከአሕዛብ፡ጋራ፡ስላመነዘርሽ፥በጣዖቶቻቸውም፡ስለ፡ረከሽ፥ይህን፡ያደርጉብሻል።
31በእኅትሽ፡መንገድ፡ኼደሻል፤ስለዚህ፥ጽዋዋን፡በእጅሽ፡እሰጥሻለኹ።
32ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦የጠለቀውንና፡የሰፋውን፡ብዙም፡የሚይዘውን፡የእኅትሽን፡ጽዋ፡ ትጠጪያለሽ፤መሳቂያና፡መሳለቂያም፡ትኾኛለሽ።
33በእኅትሽ፡በሰማርያ፡ጽዋ፥በድንጋጤና፡በጥፋት፡ጽዋ፥በስካርና፡በውርደት፡ትሞልያለሽ።
34ትጠጪዋለሽ፥ትጨልጪውማለሽ፤ገሉንም፡ታኝኪዋለሽ፥ጡትሽንም፡ትሸነትሪዋለሽ፤እኔ፡ ተናግሬያለኹና፥ይላል፡እግዚአብሔር።
35ስለዚህ፥ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ዘንግተሽኛልና፥ወደ፡ዃላሽም፡ጥለሽኛልና፥አንቺ፡ደግሞ፡ ሴሰኝነትሽንና፡ግልሙትናሽን፡ተሸከሚ።
36እግዚአብሔርም፡እንዲህ፡አለኝ፦የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥በኦሖላና፡በኦሖሊባ፡ትፈርዳለኽን፧ኀጢአታቸውንም፡ ታስታውቃቸዋለኽ፧
37አመንዝረዋልና፥ደምም፡በእጃቸው፡አለና፥ከጣዖቶቻቸውም፡ጋራ፡አመንዝረዋልና፥ለኔም፡የወለዷቸውን፡ ልጆቻቸውን፡መብል፡እንዲኾኑላቸው፡በእሳት፡አሳልፈዋቸዋልና።
38ይህን፡ደግሞ፡አድርገውብኛል፤በዚያ፡ቀን፡መቅደሴን፡አርክሰዋል፡ሰንበታቴንም፡ሽረዋል።
39ልጆቻቸውንም፡ለጣዖቶቻቸው፡በሠዉ፡ጊዜ፥በዚያው፡ቀን፡ያረክሱት፡ዘንድ፥ወደ፡መቅደሴ፡ ገቡ፤እንሆም፥በቤቴ፡ውስጥ፡እንደዚህ፡አደረጉ።
40ደግሞ፡መልእክተኛ፡ወደተላከባቸው፡ከሩቅም፡ወደሚመጡ፡ሰዎች፡ልካችዃል፤እንሆም፡መጡ፥አንቺም፡ ታጠብሽላቸው፡ዐይኖችሽንም፡ተኳልሽ፡ጌጥም፡አጌጥሽ፤
41በክብር፡ዐልጋ፡ላይ፡ተቀመጥሽ፥በፊት፡ለፊቷም፡ማእድ፡ተዘጋጅታ፡ነበር፥ዕጣኔንና፡ዘይቴንም፡ አኖርሽባት።
42የደስተኛዎችም፡ድምፅ፡በርሷ፡ዘንድ፡ነበረ፤ከብዙም፡ሰዎች፡ጉባኤ፡ጋራ፡ሰካራሞቹ፡ከምድረ፡በዳ፡ መጡ፤በእጃቸው፡አንባር፡በራሳቸውም፡የተዋበ፡አክሊል፡አደረጉ።
43እኔም፡በምንዝር፡ላረጀችው፦አኹን፡ከርሷ፡ጋራ፡ያመነዝራሉ፡ርሷም፡ከነርሱ፡ጋራ፡ታመነዝራለች፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org አልኹ።
44ወደ፡ጋለሞታም፡እንደሚገቡ፡ወደ፡ርሷ፡ገቡ፤እንዲሁ፡ይሰስኑ፡ዘንድ፥ወደ፡ኦሖላና፡ወደ፡ኦሖሊባ፡ ገቡ።
45ሴቶቹ፡አመንዝራዎች፡ናቸውና፥በእጃቸውም፡ደም፡አለና፡ጻጽቃን፡ሰዎች፡በአመንዝሮቹና፡በደም፡ አፍሳሾቹ፡ሴቶች፡ላይ፡በሚፈረደው፡ፍርድ፡ይፈርዱባቸዋል።
46ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ጉባኤን፡አመጣባቸዋለኹ፥ለመበተንና፡ለመበዝበዝም፡አሳልፌ፡ አሰጣቸዋለኹ።
47ጉባኤውም፡በድንጋይ፡ይወግሯቸዋል፡በሰይፋቸውም፡ይቈርጧቸዋል፥ወንዶችና፡ሴቶች፡ልጆቻቸውንም፡ ይገድላሉ፥ቤቶቻቸውንም፡በእሳት፡ያቃጥላሉ።
48ሴቶችም፡ዅሉ፡እንደ፡ሴሰኝነታችኹ፡እንዳይሠሩ፡ይማሩ፡ዘንድ፥ሴሰኝነትን፡ከምድር፡ላይ፡አጠፋለኹ።
49ሴሰኝነታችኹንም፡በላያችኹ፡ላይ፡ይመልሳሉ፥እናንተም፡የጣዖቶቻችኹን፡ኀጢአት፡ትሸከማላችኹ፤እኔም፡ ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ታውቃላችኹ።