Skip to content
← Ezekiel

Chapter 24 · Amharic

Ezekiel

1በዘጠነኛው፡ዓመት፡በዐሥረኛው፡ወር፡ከወሩም፡በዐሥረኛው፡ቀን፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡ እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦

2የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥የዚህን፡ቀን፥የዛሬን፡ቀን፡ስም፡ጻፍ፤በዚህ፡ቀን፡የባቢሎን፡ንጉሥ፡ወደ፡ ኢየሩሳሌም፡ቀረበ።

3ለዐመፀኛውም፡ቤት፡ምሳሌን፡ተናገር፡እንዲህም፡በላቸው፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ ይላል፦ጣድ፥ምንቸቲቱን፡ጣድ፥ውሃም፡ጨምርባት።

4ቍራጯንም፥መልካሙን፡ቍራጭ፡ዅሉ፥ጭኑንና፡ወርቹን፡በርሷ፡ውስጥ፡ሰብስብ፥የተመረጡትንም፡ ዐጥንቶች፡ሙላባት።

5ከመንጋው፡የተመረጠውን፡ውሰድ፥ዐጥንቶቹም፡እንዲበስሉ፡ዕንጨት፡በበታቿ፡ማግድ፤ዐጥንቶቹም፡ በውስጧ፡ይቀቀሉ።

6ስለዚህ፥ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ዝገቷ፡ላለባት፥ዝገቷም፡ከርሷ፡ላልወጣ፡ምንቸት፥ለደም፡ ከተማ፡ወዮላት! ቍራጭ፡ቍራጩን፡አውጣ፤ዕጣ፡አልወደቀባትም።

7ደሟ፡በውስጧ፡አለ።በተራቈተ፡ድንጋይ፡ላይ፡አደረገችው፡እንጂ፡በዐፈር፡ይከደን፡ዘንድ፥በመሬት፡ላይ፡ አላፈሰሰችውም፤

8መዓቴን፡አወጣ፡ዘንድ፥በቀሌንም፡እበቀል፡ዘንድ፥ደሟ፡እንዳይከደን፡በተራቈተ፡ድንጋይ፡ላይ፡ አደረግኹ።

9ስለዚህ፥ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ለደም፡ከተማ፡ወዮላት! እኔ፡ደግሞ፡ማገዶዋን፡ታላቅ፡ አደርገዋለኹ።

10ዕንጨቱን፡አብዛ፤እሳቱን፡አንድድ፤ሥጋውን፡ቀቅል፤መረቁን፡አጣፍጠው፤ዐጥንቶቹ፡ይቃጠሉ።

11ትሞቅም፡ዘንድ፥ናሷም፡ትግል፡ዘንድ፥ርኵሰቷም፡በውስጧ፡ይቀልጥ፡ዘንድ፥ዝገቷም፡ይጠፋ፡ ዘንድ፥ባዶዋን፡በፍም፡ላይ፡አድርጋት።

12በከንቱ፡ደከመች፤ኾኖም፡ዝገቷ፡በእሳት፡ስንኳ፡አልለቀቀም።

13በርኵሰትሽ፡ሴሰኝነት፡አለ፤አነጻኹሽ፥አልነጻሽምና፡መዓቴን፡በላይሽ፡እስክጨርስ፡ድረስ፡እንግዲህ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ከርኵሰትሽ፡አትነጺም።

14እኔ፡እግዚአብሔር፡ተናግሬያለኹ፤ይመጣል፥እኔም፡ አደርገዋለኹ፤አልመለስም፥አልራራም፥አልጸጸትም፤እንደ፡መንገድሽና፡እንደ፡ሥራሽ፡ይፈርዱብሻል፥ይላል፡ ጌታ፡እግዚአብሔር።

15የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦

16የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥እንሆ፥የዐይንኽን፡አምሮት፡በመቅሠፍት፡እወስድብኻለኹ፤አንተም፡ወይ፡አትበል፡ አታልቅስም፡እንባኽንም፡አታፍስ፟።

17በቀስታ፡ተክዝ፤ለሟቾችም፡አታልቅስ፥መጠምጠሚያኽን፡በራስኽ፡ላይ፡አድርግ፥ጫማኽንም፡በእግርኽ፡ አጥልቅ፥ከንፈሮችኽንም፡አትሸፍን፡የሰዎችንም፡እንጀራ፡አትብላ።

18እኔም፡በማለዳ፡ለሕዝቡ፡ተናገርኹ፥ወደ፡ማታም፡ሚስቴ፡ሞተች፤በነጋውም፡እንደ፡ታዘዝኹ፡ አደረግኹ።

19ሕዝቡም፦ይህ፡የምታደርገው፡ነገር፡ለእኛ፡ምን፡እንደ፡ኾነ፡አትነግረንምን፧አሉኝ።

20እኔም፡እንዲህ፡አልዃቸው፦የእግዚአብሔር፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦

21ለእስራኤል፡ቤት፡ተናገር፡እንዲህም፡በል፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥የኀይላችኹን፡ ትምክሕት፥የዐይናችኹን፡አምሮት፥የነፍሳችኹን፡ምኞት፡መቅደሴን፡አረክሳለኹ፤ያስቀራችዃቸውም፡ወንዶችና፡ ሴቶች፡ልጆቻችኹ፡በሰይፍ፡ይወድቃሉ።

22እኔም፡እንዳደረግኹ፡እናንተ፡ታደርጋላችኹ፤ከንፈራችኹን፡አትሸፍኑም፡የሰዎችንም፡እንጀራ፡አትበሉም።

23መጠምጠሚያችኹም፡በራሳችኹ፡ጫማችኹም፡በእግራችኹ፡ይኾናል፤ዋይ፡አትሉም፡ አታለቅሱምም፤በኀጢአታችኹም፡ትሰለስላላችኹ፥ርስ፡በርሳችኹም፡ታንጐራጕራላችኹ።

24ሕዝቅኤልም፡ምልክት፡ይኾናችዃል፤ርሱ፡እንዳደረገ፡ዅሉ፡እናንተ፡ታደርጋላችኹ፤ይህም፡በመጣ፡ጊዜ፡ እኔ፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ታውቃላችኹ።

25አንተም፡የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ኀይላቸውን፥የተመኩበትንም፡ደስታ፥የዐይናቸውን፡አምሮት፥የነፍሳቸውንም፡ ምኞት፥ወንዶችና፡ሴቶች፡ልጆቻቸውን፡በወሰድኹባቸው፡ቀን፥

26በዚያ፡ቀን፡ያመለጠው፡ይህን፡ነገር፡በዦሮኽ፡ያሰማ፡ዘንድ፥ወዳንተ፡ይመጣል።

27በዚያ፡ቀን፡አፍኽ፡ላመለጠው፡ይከፈታል፥አንተም፡ትናገራለኽ፡ከዚያ፡ወዲያም፡ዲዳ፡ አትኾንም፤ምልክትም፡ትኾናቸዋለኽ፥እኔም፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ያውቃሉ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source