Skip to content
← Ezekiel

Chapter 25 · Amharic

Ezekiel

1የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦

2የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ፊትኽን፡ወደዐሞን፡ልጆች፡አቅንተኽ፡ትንቢት፡ተናገርባቸው።

3ለዐሞንም፡ልጆች፡እንዲህ፡በል፦የጌታን፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ስሙ፤ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ ይላል፦መቅደሴ፡በረከሰ፡ጊዜ፡የእስራኤልም፡ምድር፡ባድማ፡በኾነች፡ጊዜ፡የይሁዳም፡ቤት፡በተማረኩ፡ጊዜ፡ ስለ፡እነርሱ፡ዕሠይ፡ብለኻልና፥

4ስለዚህ፥እንሆ፥ርስት፡አድርጌ፡ለምሥራቅ፡ልጆች፡አሳልፌ፡አሰጥኻለኹ፥እነርሱም፡ባንተ፡ውስጥ፡ ይሰፍራሉ፥ማደሪያዎቻቸውንም፡ባንተ፡ዘንድ፡ይሠራሉ፤ፍሬኽን፡ይበላሉ፥ወተትኽንም፡ይጠጣሉ፤

5የዐሞንን፡ከተማ፡ለግመሎች፡ማሰማሪያ፥የዐሞንንም፡ልጆች፡ለመንጋ፡መመሰጊያ፡አደርጋለኹ፤እኔም፡ እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ታውቃላችኹ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

6ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላልና፦በእጅኽ፡አጨብጭበኻልና፥በእግርኽም፡ አሸብሽበኻልና፥በእስራኤልም፡ምድር፡ላይ፡በነፍስኽ፡ንቀት፡ዅሉ፡ደስ፡ብሎኻልና፥

7ስለዚህ፥እንሆ፥እጄን፡ዘርግቼብኻለኹ፥ለአሕዛብም፡አስበዘብዝኻለኹ፥ከአሕዛብም፡ለይቼ፡ እቈርጥኻለኹ፥ከአገሮችም፡አጠፋኻለኹ፡እፈጅኽማለኹ፤እኔም፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ታውቃለኽ።

8ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ሞዐብና፡ሴይር፦እንሆ፥የይሁዳ፡ቤት፡እንደ፡አሕዛብ፡ዅሉ፡ነው፡ ብለዋልና፥

9ስለዚህ፥እንሆ፥የሞዐብን፡ጫንቃ፡ከከተማዎቹ፥በዳርቻው፡ካሉት፡የምድሩ፡ትምክሕት፡ከኾኑት፡ ከተማዎቹ፥ከቤትየሺሞት፥ከበዓልሜዎን፥

10ከቂርያታይም፥ከዐሞን፡ልጆች፡ጋራ፡ለምሥራቅ፡ልጆች፡እከፍታለኹ።የዐሞን፡ልጆች፡በአሕዛብ፡መካከል፡ ከእንግዲህ፡ወዲህ፡እንዳይታሰቡ፡ርስት፡አድርጌ፡እሰጣቸዋለኹ።

11በሞዐብም፡ላይ፡ፍርድን፡አደርጋለኹ፤እኔም፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ያውቃሉ።

12ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ኤዶምያስ፡በይሁዳ፡ቤት፡ላይ፡በቀል፡አድርጓልና፥ቂም፡ ይዟልና፥ብድራትንም፡አስከፍሏልና፥

13ስለዚህ፥ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እጄን፡በኤዶምያስ፡ላይ፡እዘረጋለኹ፡ከርሷም፡ዘንድ፡ ሰውንና፡እንስሳን፡አጠፋለኹ፥ከቴማንም፡ዠምሮ፡ባድማ፡አደርጋታለኹ፥እስከ፡ድዳንም፡ድረስ፡በሰይፍ፡ ይወድቃሉ።

14በሕዝቤ፡በእስራኤል፡እጅ፡ኤዶምያስን፡እበቀላለኹ፤እንደ፡ቍጣዬና፡እንደ፡መዓቴም፡መጠን፡ በኤዶምያስ፡ያደርጋሉ፤በቀሌንም፡ያውቃሉ፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።

15ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ፍልስጥኤማውያን፡በቀልን፡አድርገዋልና፥በዘወትርም፡ጠላትነት፡ ያጠፉ፡ዘንድ፥በነፍሳቸው፡ንቀት፡ተበቅለዋልና፥

16ስለዚህ፥ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥እጄን፡በፍልስጥኤማውያን፡ላይ፡ እዘረጋለኹ፥ከሊታውያንንም፡እቈርጣለኹ፥የባሕሩንም፡ዳር፡ቅሬታ፡አጠፋለኹ።

17በመዓት፡መቅሠፍትም፡ታላቅ፡በቀል፡አደርግባቸዋለኹ፤በቀሌንም፡በላያቸው፡ባደረግኹ፡ጊዜ፥እኔ፡ እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ያውቃሉ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source