Skip to content
← Ezekiel

Chapter 26 · Amharic

Ezekiel

1እንዲህም፡ኾነ፤በዐሥራ፡አንደኛው፡ዓመት፡ከወሩ፡በመዠመሪያው፡ቀን፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡ እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦

2የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ጢሮስ፡በኢየሩሳሌም፡ላይ፦ዕሠይ፥የአሕዛብ፡በር፡የነበረች፡ተሰብራለች፡ወደ፡እኔም፡ ተመልሳለች፤ርሷ፡ፈርሳለችና፡እኔ፡እሞላለኹ፡ብላለችና፡

3ስለዚህ፥ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ጢሮስ፡ሆይ፥እንሆ፥ባንቺ፡ላይ፡ነኝ፥ባሕርም፡ሞገዷን፡ እንደምታወጣ፡እንዲሁ፡ብዙ፡አሕዛብን፡አወጣብሻለኹ።

4የጢሮስንም፡ቅጥሮች፡ያጠፋሉ፡ግንቦቿንም፡ያፈርሳሉ፤ትቢያዋንም፡ከርሷ፡እፍቃለኹ፥የተራቈተ፡ ድንጋይም፡አደርጋታለኹ።

5በባሕር፡ውስጥ፡የመረብ፡ማስጫ፡ትኾናለች፤እኔ፡ተናግሬያለኹና፥ይላል፡እግዚአብሔር፤ለአሕዛብም፡ ብዝበዛ፡ትኾናለች።

6በሜዳ፡ያሉትም፡ሴቶች፡ልጆቿ፡በሰይፍ፡ይገደላሉ፤እኔም፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ያውቃሉ።

7ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላልና፦እንሆ፥ከሰሜን፡የነገሥታት፡ንጉሥ፡የባቢሎንን፡ንጉሥ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ናቡከደነጾርን፡ከፈረሶችና፡ከሠረገላዎች፡ከፈረሰኛዎችም፡ከጉባኤና፡ከብዙ፡ሕዝብ፡ጋራ፡በጢሮስ፡ላይ፡ አመጣለኹ።

8በሜዳ፡ያሉትን፡ሴቶች፡ልጆችሽን፡በሰይፍ፡ይገድላቸዋል፥ዐምባም፡ይሠራብሻል፡ዐፈርንም፡ ይደለድልብሻል፡ጋሻም፡ያነሣብሻል።

9ማፍረሻውን፡በቅጥርሽ፡ላይ፡ያደርጋል፥ግንቦችሽንም፡በምሣር፡ያፈርሳል።

10ከፈረሶቹም፡ብዛት፡የተነሣ፡ትቢያቸው፡ይከድንሻል፤ሰዎችም፡በተናደች፡ቅጥር፡ወደ፡ከተማ፡እንደሚገቡ፡ ርሱ፡በበሮችሽ፡ሲገባ፥ከፈረሰኛዎችና፡ከመንኰራኵሮች፡ከሠረገላዎችም፡ድምፅ፡የተነሣ፡ቅጥርሽ፡ትናወጣለች።

11በፈረሶቹ፡ኰቴ፡ጐዳናዎችሽን፡ዅሉ፡ይረመርማል፥ሕዝብሽንም፡በሰይፍ፡ይገድላል፥የብርታትሽም፡ ሐውልት፡ወደ፡ምድር፡ይወድቃል።

12ብልጥግናሽንም፡ይማርካሉ፥ሸቀጥሽንም፡ይበዘብዛሉ፤ቅጥርሽንም፡ያፈርሳሉ፥ተድላ፡የምታደርጊባቸውን፡ ቤቶችሽን፡ያጠፋሉ፤ድንጋይሽንና፡ዕንጨትሽን፡መሬትሽንም፡በባሕር፡ውስጥ፡ይጥላሉ።

13የዘፋኞችሽንም፡ብዛት፡ዝም፡አሠኛለኹ፤የመሰንቆሽም፡ድምፅ፡ከዚያ፡ወዲያ፡አይሰማም።

14የተራቈተ፡ድንጋይ፡አደርግሻለኹ፡የመረብም፡ማስጫ፡ትኾኛለሽ፤ከእንግዲህ፡ወዲህ፡አትሠሪም፤እኔ፡ እግዚአብሔር፡ተናግሬያለኹና፥ይላል፡እግዚአብሔር።

15ጌታ፡እግዚአብሔር፡ጢሮስን፡እንዲህ፡ይላታል፦የተወጉት፡ባንቋረሩ፡ጊዜ፥በውስጥሽ፡እልቂት፡በኾነ፡ ጊዜ፥ከውድቀትሽ፡ድምፅ፡የተነሣ፡ደሴቶች፡ይነዋወጡ፡የለምን፧

16የባሕርም፡አለቃዎች፡ዅሉ፡ከዙፋኖቻቸው፡ይወርዳሉ፤መጐናጸፊያቸውን፡ያወጣሉ፡ወርቀ፡ዘቦ፡ ልብሳቸውንም፡ያወልቃሉ፤መንቀጥቀጥን፡ለብሰው፡በመሬት፡ላይ፡ይቀመጣሉ፥ዅልጊዜም፡ይንቀጠቀጣሉ፡ ባንቺም፡ይደነቃሉ።

17ባንቺም፡ላይ፡ሙሾ፡ያሞሻሉ፥እንዲህም፡ይሉሻል፦በባሕር፡የተቀመጥሽ፡በባሕርም፡ውስጥ፡ የጸናሽ፥ከሚቀመጡብሽም፡ጋራ፡በዙሪያሽ፡የሚኖሩትን፡ዅሉ፡ያስፈራሽ፥የከበርሽ፡ከተማ፡ሆይ፥እንዴት፡ ጠፋሽ!

18አኹን፡በውድቀትሽ፡ቀን፡ደሴቶች፡ይንቀጠቀጣሉ፥በባሕርም፡ውስጥ፡ያሉ፡ደሴቶች፡ከመጥፋትሽ፡የተነሣ፡ ይደነግጣሉ።

19ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላልና፦ሰው፡እንደሌለባቸው፡ከተማዎች፡ባድማ፡ከተማ፡ባደረግኹሽ፡ ጊዜ፥ቀላዩንም፡ባወጣኹብሽ፡ጊዜ፡ብዙ፡ውሃዎችም፡በከደኑሽ፡ጊዜ፥

20የቀድሞ፡ሕዝብ፡ወዳሉበት፡ወደ፡ጕድጓድ፡ከሚወርዱት፡ጋራ፡አወርድሻለኹ፤የሚኖርብሽም፡እንዳይገኝ፡ ወደ፡ጕድጓድ፡ከሚወርዱ፡ጋራ፡ቀድሞ፡በፈረሰችው፡ስፍራ፥በታችኛዪቱ፡ምድር፡አኖርሻለኹ፤ጌጥሽንም፡ በሕያዋን፡ምድር፡አላኖርም።

21ለድንጋጤ፡አደርግሻለኹ፡እንግዲህም፡አትኖሪም፤ትፈለጊያለሽ፡ለዘለዓለምም፡አትገኚም፥ይላል፡ጌታ፡ እግዚአብሔር።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source