Skip to content
← Ezekiel

Chapter 2 · Amharic

Ezekiel

1ርሱም፦የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥በእግርኽ፡ቁም፡እኔም፡እናገርኻለኹ፡አለኝ።

2በተናገረኝም፡ጊዜ፡መንፈስ፡ገባብኝ፡በእግሬም፡አቆመኝ፥የሚናገረኝንም፡ሰማኹ።

3ርሱም፡እንዲህ፡አለኝ፦የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥በእኔ፡ላይ፡ወደዐመፁ፡ወደ፡ዐመፀኛዎች፡ሰዎች፡ ወደእስራኤል፡ልጆች፡እልክኻለኹ።እነርሱና፡አባቶቻቸው፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡ዐመፁብኝ።

4እነርሱ፡ፊታቸው፡የተጨማተረ፡ልባቸውም፡የደነደነ፡ልጆች፡ናቸው።እኔ፡ወደ፡እነርሱ፡ እልክኻለኹ፤አንተም፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፡በላቸው።

5እነርሱም፡ዐመፀኛ፡ቤት፡ናቸውና፥ቢሰሙ፡ወይም፡ባይሰሙ፡ነቢይ፡በመካከላቸው፡እንዳለ፡ያውቃሉ።

6አንተ፥የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ኵርንችትና፡ሾኽ፡ከአንተ፡ጋራ፡ቢኖሩም፥አንተም፡በጊንጦች፡መካከል፡ ብትቀመጥም፥አትፍራቸው፥ቃላቸውንም፡አትፍራ፤አንተ፡ቃላቸውን፡አትፍራ፥ከፊታቸውም፡የተነሣ፡ አትደንግጥ፤እነርሱ፡ዐመፀኛ፡ቤት፡ናቸውና።

7እነርሱ፡ዐመፀኛ፡ቤት፡ናቸውና፥ቢሰሙ፡ወይም፡ባይሰሙ፡ቃሌን፡ትነግራቸዋለኽ።

8አንተ፡ግን፥የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥የምነግርኽን፡ስማ፤እንደዚያ፡እንደ፡ዐመፀኛው፡ቤት፡ዐመፀኛ፡ አትኹን፤አፍኽን፡ክፈት፡የምሰጥኽንም፡ብላ።

9ባየኹም፡ጊዜ፥እንሆ፥እጅ፡ወደ፡እኔ፡ተዘርግታ፡ነበር፤እንሆም፥የመጽሐፍ፡ጥቅል፟፡ነበረባት። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

10በፊቴም፡ዘረጋው፥በውስጥና፡በውጭም፡ተጽፎበት፡ነበር፤ልቅሶና፡ሐዘን፡ዋይታም፡ተጽፎበት፡ነበር።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source