Skip to content
← Ezekiel

Chapter 3 · Amharic

Ezekiel

1ርሱም፦የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ያገኘኸውን፡ብላ፤ይህን፡መጽሐፍ፡ብላ፥ኼደኽም፡ለእስራኤል፡ቤት፡ ተናገር፡አለኝ።

2አፌንም፡ከፈትኹ፡መጽሐፉንም፡አጐረሠኝ።

3ርሱም፦የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥አፍኽ፡ይብላ፥በምሰጥኽም፡በዚህ፡መጽሐፍ፡ሆድኽን፡ሙላ፡አለኝ።እኔም፡ በላኹት፥በአፌም፡ውስጥ፡እንደ፡ማር፡ጣፈጠ።

4እንዲህም፡አለኝ፦የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ተነሥተኽ፡ወደእስራኤል፡ቤት፡ኺድ፥ቃሌንም፡ተናገራቸው።

5ወደእስራኤል፡ቤት፡እንጂ፡ንግግራቸው፡ወደጠለቀው፡ቋንቋቸውም፡ወደማይታወቅ፡ሕዝብ፡አልተላክኽምና፤

6ንግግራቸው፡ወደጠለቀው፡ቋንቋቸውም፡ወደማይታወቅ፡ቃላቸውንም፡ታውቅ፡ዘንድ፡ወደማይቻልኽ፡ ሕዝብ፡አላ፟ኩ፟ኽም።ወደ፡እነዚያስ፡ልኬኽ፡ቢኾን፡ኖሮ፡በሰሙኽ፡ነበር።

7ነገር፡ግን፥የእስራኤል፡ቤት፡ዅሉ፡የጠነከረ፡ግንባርና፡የደነደነ፡ልብ፡አላቸውና፥እኔንም፡መስማት፡ እንቢ፡ብለዋልና፥የእስራኤል፡ቤት፡አንተን፡አይሰሙም።

8እንሆ፥ፊትኽን፡በፊታቸው፡ግንባርኽንም፡በግንባራቸው፡አጠንክሬያለኹ።

9ከቡላድ፡ድንጋይ፡ይልቅ፡እንዳለ፡አልማዝ፡ግንባርኽን፡አጠንክሬያለኹ፤እነርሱ፡ዐመፀኛ፡ቤት፡ቢኾኑ፡ አትፍራቸው፤ከፊታቸውም፡የተነሣ፡አትደንግጥ።

10ርሱም፦የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥የነገርኹኽን፡ቃሌን፡ዅሉ፡በልብኽ፡ተቀበል፡በዦሮኽም፡ስማ።

11ተነሥተኽም፡ወደተማረኩ፡ወደወገንኽ፡ልጆች፡ኺድ፤እነርሱም፡ቢሰሙ፡ወይም፡ባይሰሙ፦ጌታ፡ እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፡ብለኽ፡ንገራቸው፡አለኝ።

12መንፈስም፡አነሣኝ፥በዃላዬም፦የእግዚአብሔር፡ክብር፡ከቦታው፡ይባረክ፡የሚል፡የጽኑ፡ንውጥውጥታ፡ ድምፅ፡ሰማኹ።

13የአራቱም፡እንስሳ፡ክንፎች፡ርስ፡በርሳቸው፡ሲማቱ፥በአጠገባቸውም፡የመንኰራኵሮችን፡ ድምፅ፥የጽኑውንም፡ንውጥውጥታ፡ድምፅ፡ሰማኹ።

14መንፈስ፡አንሥቶ፡አስወገደኝ፥እኔም፡በምሬትና፡በመንፈሴ፡ሙቀት፡ኼድኹ፥የእግዚአብሔርም፡እጅ፡ በላዬ፡በርትታ፡ነበር።

15በቴልአቢብም፡ወዳሉ፡በኮቦርም፡ወንዝ፡አጠገብ፡ወደተቀመጡ፡ምርኮኛዎች፡መጣኹ፥በተቀመጡበትም፡ ቦታ፡ተቀመጥኹ፤በዚያም፡ሰባት፡ቀን፡በድንጋጤ፡በመካከላቸው፡ተቀመጥኹ።

16ከሰባቱም፡ቀን፡በዃላ፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦

17የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ለእስራኤል፡ቤት፡ጠባቂ፡አድርጌኻለኹ፤ስለዚህ፥የአፌን፡ቃል፡ስማ፥ከእኔም፡ዘንድ፡ አስጠንቅቃቸው።

18እኔ፡ኀጢአተኛውን፦በርግጥ፡ትሞታለኽ፡ባልኹት፡ጊዜ፥አንተም፡ባታስጠነቅቀው፡ነፍሱም፡እንድትድን፡ ከክፉ፡መንገዱ፡ይመለስ፡ዘንድ፡ለኀጢአተኛው፡አስጠንቅቀኽ፡ባትነግረው፥ያ፡ኀጢአተኛ፡በኀጢአት፡ ይሞታል፤ደሙን፡ግን፡ከእጅኽ፡እፈልጋለኹ።

19ነገር፡ግን፥አንተ፡ኀጢአተኛውን፡ብታስጠነቅቅ፡ርሱም፡ከኀጢአቱና፡ከክፉ፡መንገዱ፡ ባይመለስ፥በኀጢአቱ፡ይሞታል፥አንተ፡ግን፡ነፍስኽን፡አድነኻል።

20ደግሞ፡ጻድቁ፡ከጽድቁ፡ተመልሶ፡ኀጢአት፡በሠራ፡ጊዜ፡እኔ፡በፊቱም፡ዕንቅፋትን፡ሳደርግ፥ርሱ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ይሞታል፤አንተም፡አላስጠነቀቅኸውምና፡በኀጢአቱ፡ይሞታል፡ያደረጋትም፡ጽድቅ፡ነገር፡ አትታሰብለትም፤ደሙን፡ግን፡ከእጅኽ፡እፈልጋለኹ።

21ነገር፡ግን፥ኀጢአት፡እንዳይሠራ፡ጻድቁን፡ብታስጠነቅቅ፡ርሱም፡ኀጢአት፡ ባይሠራ፥ተጠንቅቋልና፥በርግጥ፡በሕይወት፡ይኖራል፤አንተም፡ነፍስኽን፡አድነኻል።

22በዚያም፡የእግዚአብሔር፡እጅ፡በእኔ፡ላይ፡ነበረች፥ርሱም፦ተነሥተኽ፡ወደ፡ቈላው፡ኺድ፡በዚያም፡ እናገርኻለኹ፡አለኝ።

23እኔም፡ተነሥቼ፡ወደ፡ቈላው፡ኼድኹ፤እንሆም፥በኮቦር፡ወንዝ፡እንዳየኹት፡ክብር፡ያለ፡የእግዚአብሔር፡ ክብር፡በዚያ፡ቆሞ፡ነበር፥በግንባሬም፡ተደፋኹ።

24መንፈስም፡ገባብኝ፡በእግሬም፡አቆመኝ፥ተናገረኝም፡እንዲህም፡አለኝ፦ኺድ፥ገብተኽ፡ቤትኽን፡ዝጋ።

25አንተም፥የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥እንሆ፥ገመድ፡ያደርጉብኻል፡ያስሩኽማል፥አንተም፡በመካከላቸው፡ አትወጣም፤

26እኔም፡ምላስኽን፡ከትናጋኽ፡ጋራ፡አጣብቃታለኹ፡አንተም፡ዲዳ፡ትኾናለኽ፥እነርሱም፡ዐመፀኛ፡ቤት፡ ናቸውና፥የሚዘልፍ፡ሰው፡አትኾንባቸውም።

27ነገር፡ግን፥በተናገርኹኽ፡ጊዜ፡አፍኽን፡እከፍታለኹ፥እነርሱም፡ዐመፀኛ፡ቤት፡ናቸውና፥አንተ፦ጌታ፡ እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦የሚሰማ፡ይስማ፥የማይሰማም፡አይስማ፡ትላቸዋለኽ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source