Skip to content
← Ezekiel

Chapter 4 · Amharic

Ezekiel

1አንተም፥የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ጡብን፡ወስደኽ፡በፊትኽ፡አኑራት፥የኢየሩሳሌምንም፡ከተማ፡ሥዕል፡ሣልባት፡ ክበባት፥

2ምሽግም፡ሥራባት፥ዐፈርም፡ደልድልባት፥ሰፈርም፡አቁምባት፥በዙሪያዋም፡የሚያፈርስ፡ግንድ፡አድርግባት።

3የብረት፡ምጣድም፡ወስደኽ፡በአንተና፡በከተማዪቱ፡መካከል፡ለብረት፡ቅጥር፡አድርገው፥ፊትኽንም፡ወደ፡ ርሷ፡አቅና፥የተከበበችም፡ትኾናለች፡አንተም፡ትከባ፟ታለኽ።ይህም፡ለእስራኤል፡ቤት፡ምልክት፡ይኾናል።

4አንተም፡በግራ፡ጐድንኽ፡ተኛ፡የእስራኤልንም፡ቤት፡ኀጢአት፡አኑርባት፤በምትተኛበትም፡ቀን፡ቍጥር፡ ኀጢአታቸውን፡ትሸከማለኽ።

5እኔም፡የኀጢአታቸውን፡ዓመታት፡ለአንተ፡የቀን፡ቍጥር፡እንዲኾንልኽ፡ሦስት፡መቶ፡ዘጠና፡ቀን፡ ሰጥቼኻለኹ፤የእስራኤልንም፡ቤት፡ኀጢአት፡ትሸከማለኽ።

6እነዚህንም፡በፈጸምኽ፡ጊዜ፡በቀኝ፡ጐድንኽ፡ትተኛለኽ፥የይሁዳንም፡ቤት፡ኀጢአት፡ትሸከማለኽ፤አንድን፡ ዓመት፡አንድ፡ቀን፡አድርጌ፡አርባ፡ቀን፡ሰጥቼኻለኹ።

7ክንድኽን፡ዕራቍቱን፡አድርገኽ፡ፊትኽን፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡ክቡ፡ታቀናለኽ፥ትንቢትም፡ትናገርባታለኽ።

8እንሆም፥ገመድ፡አደርግብኻለኹ፥የምትከበብበትንም፡ወራት፡እስክትፈጽም፡ድረስ፡ከጐድን፡ጐድንኽ፡ አትገላበጥም።

9አንተም፡ስንዴንና፡ገብስን፥ባቄላንና፡ምስርን፥ጤፍንና፡ዐጃን፡ወዳንተ፡ውሰድ፥ባንድ፡ዕቃም፡ውስጥ፡ አድርገኽ፡እንጀራ፡ጋግር፤በጐድንኽ፡እንደ፡ተኛኽበት፡ቀን፡ቍጥር፡ሦስት፡መቶ፡ዘጠና፡ቀን፡ትበላዋለኽ።

10የምትበላውም፡በሚዛን፡በየቀኑ፡ኻያ፡ኻያ፡ሰቅል፡ይኹን፥በየጊዜው፡ትበላዋለኽ።

11ውሃውንም፡በልክ፡የኢን፡መስፈሪያ፡ከስድስት፡እጅ፡አንድን፡እጅ፡ትጠጣለኽ፥በየጊዜው፡ትጠጣዋለኽ።

12እንደ፡ገብስ፡ዕንጐቻም፡አድርገኽ፡ትበላዋለኽ፥ከሰውም፡በሚወጣ፡ፋንድያ፡በፊታቸው፡ትጋግረዋለኽ።

13እግዚአብሔርም፦እንዲሁ፡የእስራኤል፡ልጆች፡እነርሱን፡በምበትንባቸው፡በአሕዛብ፡መካከል፡ርኩስ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org እንጀራቸውን፡ይበላሉ፡አለ።

14እኔም፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡ሆይ፥ወዮ! እንሆ፥ሰውነቴ፡አልረከሰችም፤ከታናሽነቴ፡ዠምሮ፡እስከ፡ዛሬ፡ ድረስ፡ጥንብና፡አውሬ፡የሰበረውን፡ከቶ፡አልበላኹም፥ርኩስም፡ሥጋ፡በአፌ፡ውስጥ፡አልገባም፡አልኹ።

15ርሱም፦እንሆ፥በሰው፡ፋንድያ፡ፋንታ፡ኵበት፡ሰጥቼኻለኹ፡በርሱም፡እንጀራኽን፡ትጋግራለኽ፡አለኝ።

16ደግሞም፡እንዲህ፡አለኝ፦የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥የኢየሩሳሌምን፡እንጀራ፡በትር፡እሰብራለኹ፥እየፈሩም፡ እንጀራን፡በሚዛን፡ይበላሉ፥እየደነገጡም፡ውሃን፡በልክ፡ይጠጣሉ፤

17ይህም፡እንጀራንና፡ውሃን፡እንዲያጡ፥ርስ፡በርሳቸውም፡እንዲደነቁ፥በኀጢአታቸውም፡እንዲሰለስሉ፡ነው።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source