Skip to content
← Ezekiel

Chapter 5 · Amharic

Ezekiel

1አንተም፥የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥የተሳለን፡ጐራዴ፡ውሰድ፥እንደ፡ጢም፡መላጫ፡ወዳንተ፡ ትወስደዋለኽ፥ራስኽንና፡ጢምኽንም፡ትላጭበታለኽ፤ሚዛንንም፡ውሰድ፡ጠጕሩንም፡ትከፋፍላለኽ።

2የመከበብም፡ወራት፡በተፈጸመ፡ጊዜ፡በከተማዪቱ፡መካከል፡ሢሶውን፡በእሳት፡ታቃጥላለኽ፤ሢሶውንም፡ ወስደኽ፡ዙሪያውን፡በጐራዴ፡ትመታለኽ፥ሢሶውንም፡ወደ፡ነፋስ፡ትበትናለኽ፡እኔም፡በዃላቸው፡ጐራዴ፡ እመዛ፟ለኹ።

3ከዚያም፡በጥቂቱ፡ውሰድ፥በመጐናጸፊያኽም፡ጫፍ፡ቋጥራቸው።

4ከነርሱም፡ደግሞ፡ወስደኽ፡በእሳት፡ውስጥ፡ትጥላለኽ፡በእሳትም፡ታቃጥላቸዋለኽ፤ከዚያም፡በእስራኤል፡ ቤት፡ዅሉ፡ላይ፡እሳት፡ትወጣለች።

5ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ይህች፡ኢየሩሳሌም፡ናት፤በአሕዛብም፡መካከል፡ አድርጌያታለኹ፥አገሮችም፡በዙሪያዋ፡አሉ።

6ርሷም፡ከአሕዛብ፡ይልቅ፡ፍርዴን፡በኀጢአት፡ለወጠች፡በዙሪያዋም፡ካሉ፡አገሮች፡ዅሉ፡ይልቅ፡ትእዛዜን፡ ተላለፈች፤ፍርዴን፡ጥለዋልና፥በትእዛዜም፡አልኼዱምና።

7ስለዚህ፥ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦በዙሪያችኹ፡ላሉት፡አሕዛብ፡ሰበብ፡ ኾናችዃልና፥በትእዛዜም፡አልኼዳችኹምና፥ፍርዴንም፡አልጠበቃችኹምና፥በዙሪያችኹም፡እንዳሉ፡እንደ፡ አሕዛብ፡ፍርድ፡እንኳ፡አላደረጋችኹምና፡

8ስለዚህ፥ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥እኔ፡ራሴ፡ባንቺ፡ላይ፡ነኝ፥አሕዛብም፡ እያዩ፥ፍርድን፡በመካከልሽ፡አደርጋለኹ።

9ስለ፡ርኵሰትሽም፡ዅሉ፡ያልሠራኹትን፥ርሱንም፡የሚመስል፡ደግሞ፡የማልሠራውን፥ነገር፡እሠራብሻለኹ።

10ስለዚህ፥በመካከልሽ፡አባቶች፡ልጆቻቸውን፡ይበላሉ፥ልጆችም፡አባቶቻቸውን፡ይበላሉ፤ፍርድንም፡ አደርግብሻለኹ፥ከአንቺም፡የቀረውን፡ዅሉ፡ወደ፡ነፋሳት፡ዅሉ፡እበትናለኹ።

11ስለዚህ፥እኔ፡ሕያው፡ነኝና፡በእድፍሽና፡በርኵሰትሽ፡መቅደሴን፡ስላረከ፟ሽ፥ስለዚህ፡በእውነት፡እኔ፡ አሳንስሻለኹ፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር፤ዐይኔም፡አይራራም፡እኔም፡አላዝንም።

12ከአንቺም፡ሢሶው፡በቸነፈር፡ይሞታል፥በመካከልሽም፡በራብ፡ያልቃል፤ሢሶውም፡በዙሪያሽ፡በሰይፍ፡ ይወድቃል፤ሢሶውንም፡ወደ፡ነፋሳት፡ዅሉ፡እበትናለኹ፡በዃላቸውም፡ሰይፍ፡እመዛ፟ለኹ።

13ቍጣዬም፡ይፈጸማል፡መዓቴንም፡እጨርሳለኹ፡እጽናናማለኹ፥መዓቴንም፡በፈጸምኹባቸው፡ጊዜ፡እኔ፡ እግዚአብሔር፡በቅንአቴ፡እንደ፡ተናገርኹ፡ያውቃሉ።

14በዙሪያሽም፡ባሉ፡በአሕዛብ፡መካከል፡በሚያልፉም፡ዅሉ፡ፊት፡ባድማና፡መሰደቢያ፡አደርግሻለኹ።

15በቍጣና፡በመዓት፥በመዓትም፡ዘለፋ፡ፍርድን፡ባደረግኹብሽ፡ጊዜ፡በዙሪያሽ፡ላሉ፡አሕዛብ፡መሰደቢያና፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org መተረቻ፥ተግሣጽና፡መደነቂያ፡ይኾናል፤እኔ፡እግዚአብሔር፡ይህን፡ተናግሬያለኹ።

16ለማጥፋትም፡የኾነውን፥አጠፋችኹም፡ዘንድ፡የምሰደ፟ውን፡የራብ፡ፍላጻ፡በላያችኹ፡በሰደድኹ፡ ጊዜ፥ራብን፡እጨምርባችዃለኹ፥የእንጀራችኹንም፡በትር፡እሰብራለኹ።

17ራብንና፡ክፉዎችን፡አራዊት፡እሰድ፟ባችዃለኹ፥ልጆቻችኹንም፡ያጠፋሉ፤ቸነፈርና፡ደምም፡ባንቺ፡ዘንድ፡ ያልፋሉ፤ሰይፍንም፡አመጣብሻለኹ።እኔ፡እግዚአብሔር፡ይህን፡ተናግሬያለኹ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source