1የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
2የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥የጢሮስን፡ገዢ፡እንዲህ፡በለው፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ልብኽ፡ ኰርቷል፡አንተም፦እኔ፡አምላክ፡ነኝ፥በእግዚአብሔር፡ወንበር፡በባሕር፡መካከል፡ተቀምጫለኹ፡ ብለኻል፤ነገር፡ግን፥ልብኽን፡እንደእግዚአብሔር፡ልብ፡ብታደርግም፡አንተ፡ሰው፡ነኽ፡እንጂ፡አምላክ፡ አይደለኽም።
3እንሆ፥ከዳንኤል፡ይልቅ፡ጥበበኛ፡ነኽ፥ምስጢርም፡ዅሉ፡ከአንተ፡የተሸሸገ፡አይደለም።
4በጥበብኽና፡በማስተዋልኽ፡ብልጥግናን፡ለራስኽ፡አግኝተኻል፡ወርቅና፡ብርም፡በግምጃ፡ቤትኽ፡ውስጥ፡ ሰብስበኻል።
5በታላቅ፡ጥበብኽና፡በንግድኽ፡ብልጥግናኽን፡አብዝተኻል፡በብልጥግናኽም፡ልብኽ፡ኰርቷል።
6ስለዚህ፥ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ልብኽን፡እንደእግዚአብሔር፡ልብ፡አድርገኻልና፥
7ስለዚህ፥እንሆ፥የሌላ፡አገር፡ሰዎችን፥የአሕዛብን፡ጨካኞች፥አመጣብኻለኹ፤ሰይፋቸውንም፡በጥበብኽ፡ ውበት፡ላይ፡ይመዛ፟ሉ፡ክብርኽንም፡ያረክሳሉ።
8ወደ፡ጕድጓድ፡ያወርዱኻል፤ተገድለው፡እንደ፡ሞቱ፡በባሕር፡ውስጥ፡ትሞታለኽ።
9በእውኑ፡በገዳይኽ፡ፊት፦እኔ፡አምላክ፡ነኝ፡ትላለኽን፧ነገር፡ግን፡በገዳይኽ፡እጅ፡ሰው፡ነኽ፡እንጂ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org አምላክ፡አይደለኽም።
10በእንግዳዎች፡እጅ፡ያልተገረዙትን፡ሰዎች፡ሞት፡ትሞታለኽ፤እኔ፡ተናግሬያለኹና፥ይላል፡እግዚአብሔር።
11የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
12የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥በጢሮስ፡ንጉሥ፡ላይ፡ሙሾ፡አሞሽተኽ፡እንዲህ፡በለው፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡ እንዲህ፡ይላል፦ጥበብን፡የተሞላኽ፡ውበትኽም፡የተፈጸመ፡መደምደሚያ፡አንተ፡ነኽ።
13በእግዚአብሔር፡ገነት፡በዔዴን፡ነበርኽ፤የከበረ፡ዕንቍስ፡ ዅሉ፥ሰርድዮን፥ቶጳዝዮን፥አልማዝ፥ቢረሌ፥መረግድ፥ኢያስጲድ፥ሰንፔር፥በሉር፥የሚያብረቀርቅ፡ ዕንቍ፥ወርቅ፥ልብስኽ፡ነበረ፤የከበሮኽና፡የእንቢልታኽ፡ሥራ፡ባንተ፡ዘንድ፡ነበረ፤በተፈጠርኽበት፡ቀን፡ ተዘጋጅተው፡ነበር።
14አንተ፡ልትጋርድ፡የተቀባኽ፡ኪሩብ፡ነበርኽ፡በተቀደሰው፡በእግዚአብሔር፡ተራራ፡ላይ፡አኖርኹኽ፤በእሳት፡ ድንጋዮች፡መካከል፡ተመላለስኽ።
15ከተፈጠርኽበት፡ቀን፡ዠምረኽ፡በደል፡እስኪገኝብኽ፡ድረስ፡በመንገድኽ፡ፍጹም፡ነበርኽ።
16በንግድኽ፡ብዛት፡ግፍ፡በውስጥኽ፡ተሞላ፡ኀጢአትንም፡ሠራኽ፤ስለዚህ፥እንደ፡ርኩስ፡ነገር፡ ከእግዚአብሔር፡ተራራ፡ጣልኹኽ፤የምትጋርድ፡ኪሩብ፡ሆይ፥ከእሳት፡ድንጋዮች፡መካከል፡አጠፋኹኽ።
17በውበትኽ፡ምክንያት፡ልብኽ፡ኰርቷል፤ከክብርኽ፡የተነሣ፡ጥበብኽን፡አረከስኽ፤በምድር፡ላይ፡ ጣልኹኽ፤ያዩኽም፡ዘንድ፥በነገሥታት፡ፊት፡ሰጠኹኽ።
18በበደልኽ፡ብዛት፡በንግድኽም፡ኀጢአት፡መቅደስኽን፡አረከስኽ፤ስለዚህ፥እሳትን፡ከውስጥኽ፡አውጥቻለኹ፡ ርሷም፡በልታኻለች፥በሚያዩኽም፡ዅሉ፡ፊት፡በምድር፡ላይ፡ዐመድ፡አድርጌኻለኹ።
19በአሕዛብም፡ውስጥ፡የሚያውቁኽ፡ዅሉ፡ይደነቁብኻል፤አንተም፡ለድንጋጤ፡ኾነኻል፥እስከ፡ዘለዓለምም፡ አትገኝም።
20የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
21የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ፊትኽን፡ወደ፡ሲዶና፡አቅንተኽ፡ትንቢት፡ተናገርባት፥እንዲህም፡በል።
22ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ሲዶና፡ሆይ፥እንሆ፥ባንቺ፡ላይ፡ነኝ፥በውስጥሽም፡ እከብራለኹ፤ፍርድንም፡ባደረግኹባት፡ጊዜ፡በተቀደስኹባትም፡ጊዜ፡እኔ፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ ያውቃሉ።
23ቸነፈርንም፡በርሷ፡ላይ፥ደምንም፡በጐዳናዋ፡እሰዳ፟ለኹ፤ከዙሪያዋ፡በላይዋ፡ባለ፡ሰይፍ፡የተወጉ፡ በመካከሏ፡ይወድቃሉ፤እኔም፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ያውቃሉ።
24ከእንግዲህም፡ወዲያ፡ለእስራኤል፡ቤት፡የሚወጋ፡ሾኽ፥በዙሪያቸውም፡ካሉ፡ከናቋቸው፡ዅሉ፡ የሚያቈስል፡ኵርንችት፡አይኾንም፤እኔም፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ያውቃሉ።
25ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦የእስራኤልን፡ቤት፡ከተበተኑባቸው፡አሕዛብ፡ዘንድ፡በሰበሰብኹ፡ ጊዜ፥በአሕዛብም፡ፊት፡በተቀደስኹባቸው፡ጊዜ፥ለባሪያዬ፡ለያዕቆብ፡በሰጠዃት፡ምድራቸው፡ይቀመጣሉ።
26ተዘልለውም፡ይቀመጡባታል፤ቤቶችንም፡ይሠራሉ፡ወይኑንም፡ይተክላሉ፡በዙሪያቸውም፡ባሉ፡በሚንቋቸው፡ ዅሉ፡ላይ፡ፍርድን፡ባደረግኹ፡ጊዜ፡ተዘልለው፡ይቀመጣሉ፤እኔም፡እግዚአብሔር፡አምላካቸው፡እንደ፡ኾንኹ፡ ያውቃሉ።