1በዐሥረኛው፡ዓመት፡በዐሥረኛው፡ወር፡ከወሩም፡በዐሥራ፡ኹለተኛው፡ቀን፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡ወደ፡ እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
2የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ፊትኽን፡በግብጽ፡ንጉሥ፡በፈርዖን፡ላይ፡አድርግ፥በርሱና፡በግብጽ፡ዅሉ፡ላይም፡ ትንቢት፡ተናገር፥
3እንዲህም፡በል፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦በወንዞች፡መካከል፡የምትተኛና፦ወንዙ፡የእኔ፡ ነው፥ለራሴም፡ሠርቼዋለኹ፡የምትል፡ታላቅ፡ዐዞ፥የግብጽ፡ንጉሥ፡ፈርዖን፡ሆይ፥እንሆ፥ባንተ፡ላይ፡ነኝ።
4በመንጋጋኽ፡መቃጥን፡አገባብኻለኹ፥የወንዞችኽንም፡ዓሣዎች፡ወደ፡ቅርፊትኽ፡ አጣብቃለኹ፤ከወንዞችኽም፡መካከል፡አወጣኻለኹ፥የወንዞችኽም፡ዓሣዎች፡ዅሉ፡ወደ፡ቅርፊትኽ፡ይጣበቃሉ።
5አንተንና፡የወንዞችኽን፡ዓሣዎች፡ዅሉ፡ወደ፡ምድረ፡በዳ፡እጥላለኹ፥በምድርም፡ፊት፡ላይ፡ትወድቃለኽ፡ እንጂ፡አትከማችም፡አትሰበሰብም፡መብልም፡አድርጌ፡ለምድር፡አራዊትና፡ለሰማይ፡ወፎች፡ሰጥቼኻለኹ።
6በግብጽም፡የሚኖሩ፡ዅሉ፡ለእስራኤል፡ቤት፡የሸንበቆ፡በትር፡ኾነዋልና፥እኔ፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ ያውቃሉ።
7በእጅ፡በያዙኽ፡ጊዜ፡ተሰበርኽ፡ጫንቃቸውንም፡ዅሉ፡አቈሰልኽ፤በተደገፉብኽም፡ጊዜ፡ተሰበርኽ፡ ወገባቸውንም፡ዅሉ፡አንቀጠቀጥኽ።
8ስለዚህ፥ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥ሰይፍ፡አመጣብኻለኹ፥ሰውንና፡እንስሳንም፡ከአንተ፡ ዘንድ፡አጠፋለኹ።
9የግብጽም፡ምድር፡ባድማና፡ውድማ፡ትኾናለች፥እኔም፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ ያውቃሉ፤አንተ፦ወንዙ፡የእኔ፡ነው፥የሠራኹትም፡እኔ፡ነኝ፡ብለኻልና።
10ስለዚህ፥እንሆ፥በአንተና፡በወንዞችኽ፡ላይ፡ነኝ፥የግብጽንም፡ምድር፡ከሚግዶል፡ዠምሮ፡እስከ፡ሴዌኔና፡ እስከኢትዮጵያ፡ዳርቻ፡ድረስ፡ውድማና፡ባድማ፡አደርጋታለኹ።
11የሰው፡እግር፡አያልፍባትም፡የእንስሳም፡ኰቴ፡አያልፍባትም፥እስከ፡አርባ፡ዓመትም፡ድረስ፡ማንም፡ አይኖርባትም።
12ባድማም፡በኾኑ፡ምድሮች፡መካከል፡የግብጽን፡ምድር፡ባድማ፡አደርጋታለኹ፥በፈረሱትም፡ከተማዎች፡ መካከል፡ከተማዎቿ፡አርባ፡ዓመት፡ፈርሰው፡ይቀመጣሉ፤ግብጻውያንንም፡ወደ፡አሕዛብ፡እበትናቸዋለኹ፡ በአገሮችም፡እዘራቸዋለኹ።
13ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ከአርባ፡ዓመት፡በዃላ፡ግብጻውያንን፡ከተበተኑባቸው፡አሕዛብ፡ ዘንድ፡እሰበስባለኹ፤
14የግብጽንም፡ምርኮ፡እመልሳለኹ፥ወደተወለዱባትም፡ምድር፡ወደ፡ጳትሮስ፡እመልሳቸዋለኹ፤በዚያም፡ የተዋረደች፡መንግሥት፡ይኾናሉ።
15ከሌላዎች፡መንግሥታት፡ዅሉ፡ይልቅ፡የተዋረደች፡ትኾናለች፤ከእንግዲህ፡ወዲያ፡በአሕዛብ፡ላይ፡ከፍ፡ አትልም፤በአሕዛብም፡ላይ፡እንዳይገዙ፡አሳንሳቸዋለኹ።
16የእስራኤል፡ቤት፡እነርሱን፡በተከተሉ፡ጊዜ፡ርሷ፡በደልን፡ታሳስባለች፥ከእንግዲህም፡ወዲያ፡መታመኛ፡ አትኾንላቸውም፤እኔም፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ያውቃሉ።
17እንዲህም፡ኾነ፤በኻያ፡ሰባተኛው፡ዓመት፡በመዠመሪያው፡ወር፡ከወሩም፡በመዠመሪያው፡ቀን፡ የእግዚአብሔር፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
18የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥የባቢሎን፡ንጉሥ፡ናቡከደነጾር፡ሰራዊቱን፡በጢሮስ፡ላይ፡ጽኑ፡አገልግሎት፡ አስገለገለ፤ራስ፡ዅሉ፡የተላጨ፡ጫንቃም፡ዅሉ፡የተላጠ፡ኾኗል፤ነገር፡ግን፥በላይዋ፡ስላገለገለው፡ አገልግሎት፡ርሱና፡ሰራዊቱ፡ደመ፡ወዝ፡ከጢሮስ፡አልተቀበሉም።
19ስለዚህ፥ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥የግብጽን፡ምድር፡ለባቢሎን፡ንጉሥ፡ለናቡከደነጾር፡ እሰጠዋለኹ፥ብዛቷንም፡ይወስዳል፡ምርኮዋንም፡ይማርካል፡ብዝበዛዋንም፡ይበዘብዛል፤ይህም፡ለሰራዊቱ፡ደመ፡ ወዝ፡ይኾናል። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
20ስለ፡እኔ፡ሠርተዋልና፥ስላገልግሎቱ፡ደመ፡ወዝ፡የግብጽን፡ምድር፡ሰጥቼዋለኹ፥ይላል፡ጌታ፡ እግዚአብሔር።
21በዚያ፡ቀን፡ለእስራኤል፡ቤት፡ቀንድን፡አበቅላለኹ፥በመካከላቸውም፡ለአንተ፡የተከፈተ፡አፍን፡ እሰጣለኹ፤እኔም፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ያውቃሉ።