1የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
2የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ትንቢት፡ተናገር፡እንዲህም፡በል፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ዋይ! በሉ፥ለቀኑ፡ወዮ! ቀኑ፡ቅርብ፡ነው፥
3የእግዚአብሔር፡ቀን፡ቅርብ፡ነው፥የደመና፡ቀን፥የአሕዛብ፡ጊዜ፡ይኾናል።
4ሰይፍ፡በግብጽ፡ላይ፡ይመጣል፥ሁከትም፡በኢትዮጵያ፡ይኾናል፤የተገደሉትም፡በግብጽ፡ውስጥ፡ ይወድቃሉ፥ብዛቷንም፡ይወስዳሉ፥መሠረቷም፡ይፈርሳል።
5ኢትዮጵያና፡ፉጥ፡ሉድም፡የተደባለቀም፡ሕዝብ፡ዅሉ፡ኩብም፡ቃል፡ኪዳንም፡የገባችው፡ምድር፡ልጆች፡ ከነርሱ፡ጋራ፡በሰይፍ፡ይወድቃሉ።
6እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ግብጽን፡የሚደግፉ፡ይወድቃሉ፥የኀይሏም፡ትዕቢት፡ይወርዳል፤ከሚግዶል፡ ዠምሮ፡እስከ፡ሴዌኔ፡ድረስ፡በርሷ፡ውስጥ፡በሰይፍ፡ይወድቃሉ፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
7ባድማም፡በኾኑ፡አገሮች፡መካከል፡ባድማ፡ይኾናሉ፥ከተማዎቿም፡በፈረሱ፡ከተማዎች፡መካከል፡ይኾናሉ።
8እሳትንም፡በግብጽ፡ባነደድኹ፡ጊዜ፥ረዳቶቿም፡ዅሉ፡በተሰበሩ፡ጊዜ፥እኔ፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ ያውቃሉ።
9በዚያ፡ቀን፡መልእክተኛዎች፡ተዘልለው፡የሚኖሩትን፡ኢትዮጵያውያንን፡ለማስፈራት፡ከፊቴ፡በመርከብ፡ ይወጣሉ፤እንደ፡ግብጽም፡ቀን፡ሁከት፡ይኾንባቸዋል፤እንሆ፥ይመጣልና።
10ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦የግብጽን፡ብዛት፡በባቢሎን፡ንጉሥ፡በናቡከደነጾር፡እጅ፡እሽራለኹ።
11ርሱና፡የአሕዛብ፡ጨካኞች፡ሕዝቡ፡ምድሪቱን፡ለማጥፋት፡ይመጣሉ፤ሰይፋቸውንም፡በግብጽ፡ላይ፡ ይመዛ፟ሉ፡ምድሪቱንም፡በተገደሉት፡ይሞላሉ።
12ወንዞችንም፡ምድረ፡በዳ፡አደርጋለኹ፡ምድሪቱንም፡በክፉ፡ሰዎች፡እጅ፡እሸጣለኹ፥ምድሪቱንና፡ መላ፟ዋንም፡በእንግዳዎች፡እጅ፡ባድማ፡አደርጋለኹ፤እኔ፡እግዚአብሔር፡ተናግሬያለኹ።
13ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ጣዖቶቹን፡አጠፋለኹ፡ምስሎችንም፡ከሜምፎስ፡ እሽራለኹ፤ከእንግዲህ፡ወዲያ፡በግብጽ፡ምድር፡አለቃ፡አይኾንም፥በግብጽም፡ምድር፡ላይ፡ፍርሀትን፡ አደርጋለኹ።
14ጳትሮስንም፡አፈርሳለኹ፥በጣኔዎስም፡እሳትን፡አነዳ፟ለኹ፥በኖእ፡ላይም፡ፍርድን፡አደርጋለኹ።
15በግብጽም፡ምሽግ፡በሲን፡ላይ፡መዓቴን፡አፈሳ፟ለኹ፥የኖእንም፡ብዛት፡አጠፋለኹ።
16በግብጽም፡እሳትን፡አነዳ፟ለኹ፥ሲንም፡ትጨነቃለች፡ኖእም፡ትሰበራለች፥በሜምፎስም፡በየቀኑ፡ጠላቶች፡ ይኾኑባታል።
17የሄልዮቱ፡ከተማና፡የቡባስቱም፡ጐልማሶች፡በሰይፍ፡ይወድቃሉ፡ሴቶችም፡ይማረካሉ።
18የግብጽን፡ቀንበር፡በዚያ፡በሰበርኹ፡ጊዜ፡በጣፍናስ፡ቀኑ፡ይጨልማል፡የኀይሏም፡ትዕቢት፡ ይጠፋባታል፤ደመናም፡ይጋርዳታል፥ሴቶች፡ልጆቿም፡ይማረካሉ።
19እንዲሁ፡በግብጽ፡ላይ፡ፍርድን፡አደርጋለኹ፤እኔም፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ያውቃሉ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
20እንዲህም፡ኾነ፤በዐሥራ፡አንደኛው፡ዓመት፡በመዠመሪያው፡ወር፡ከወሩም፡በሰባተኛው፡ቀን፡ የእግዚአብሔር፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
21የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥የግብጽን፡ንጉሥ፡የፈርዖንን፡ክንድ፡ሰብሬያለኹ፤እንሆም፥በጨርቅ፡በመጠቅለል፡ ይፈወስ፡ዘንድ፥ሰይፉንም፡ለመያዝ፡እንዲበረታ፡አልታሰረም።
22ስለዚህ፥ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥እኔ፡በግብጽ፡ንጉሥ፡በፈርዖን፡ላይ፡ ነኝ፥የጸናችውንና፡የተሰበረችውንም፡ክንዱን፡እሰብራለኹ፥ሰይፉንም፡ከእጁ፡አስረግፈዋለኹ።
23ግብጻውያንንም፡ወደ፡አሕዛብ፡እበትናለኹ፡ወደ፡አገሮችም፡እዘራቸዋለኹ።
24የባቢሎንንም፡ንጉሥ፡ክንድ፡አበረታለኹ፡ሰይፌንም፡በእጁ፡እሰጣለኹ፤የፈርዖንን፡ክንድ፡ግን፡ እሰብራለኹ፥ተወግቶም፡በሚሞተው፡እንጕርጕሮ፡በፊቱ፡ያንጐራጕራል።
25የባቢሎንንም፡ንጉሥ፡ክንድ፡አጸናለኹ፡የፈርዖንም፡ክንድ፡ይወድቃል፤ሰይፌንም፡በባቢሎን፡ንጉሥ፡እጅ፡ በሰጠኹ፡ጊዜ፡ርሱም፡በግብጽ፡ምድር፡ላይ፡በዘረጋው፡ጊዜ፥እኔ፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ያውቃሉ።
26ግብጻውያንንም፡ወደ፡አሕዛብ፡እበትናለኹ፡ወደ፡አገሮችም፡እዘራቸዋለኹ፤እኔም፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ ኾንኹ፡ያውቃሉ።