Skip to content
← Ezekiel

Chapter 31 · Amharic

Ezekiel

1እንዲህም፡ኾነ፤በዐሥራ፡አንደኛው፡ዓመት፡በሦስተኛው፡ወር፡ከወሩም፡በመዠመሪያው፡ቀን፡ የእግዚአብሔር፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦

2የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥የግብጽን፡ንጉሥ፡ፈርዖንንና፡የሕዝቡን፡ብዛት፡እንዲህ፡በላቸው፦በታላቅነትኽ፡ማንን፡ መስለኻል፧

3እንሆ፥አሶር፡ጫፉ፡እንደ፡ተዋበ፥ችፍግነቱ፡ጥላ፡እንደ፡ሰጠ፥ቁመቱም፡እንደ፡ረዘመ፥ራሱም፡ በደመናዎች፡መካከል፡እንደ፡ነበረ፡እንደ፡ሊባኖስ፡ዝግባ፡ነበረ።

4ውሃዎችም፡አበቀሉት፥ቀላይም፡አሳደገው፥ወንዞችም፡በተተከለበት፡ዙሪያ፡ይጐርፉ፡ነበር፥ፈሳሾቹንም፡ ወደ፡ምድረ፡በዳ፡ዛፍ፡ዅሉ፡ሰደደ።

5ስለዚህ፥ቁመቱ፡ከምድረ፡በዳ፡ዛፍ፡ዅሉ፡በላይ፡ከፍ፡ከፍ፡አለ፥ቅርንጫፎቹም፡በዙ፥ጫፎቹንም፡ ባበቀለ፡ጊዜ፡ከብዙ፡ውሃዎች፡የተነሣ፡ረዘሙ።

6የሰማይ፡ወፎች፡ዅሉ፡ጐዦዎቻቸውን፡በቅርንጫፎቹ፡ላይ፡አደረጉ፥የምድርም፡አራዊት፡ዅሉ፡ከጫፎቹ፡ በታች፡ተዋለዱ፥ከጥላውም፡በታች፡ታላላቆች፡አሕዛብ፡ዅሉ፡ይቀመጡ፡ነበር።

7ሥሩም፡በብዙ፡ውሃ፡አጠገብ፡ነበረና፡በታላቅነቱና፡በጫፎቹ፡ርዝመት፡የተዋበ፡ነበረ።

8በእግዚአብሔር፡ገነት፡የነበሩ፡ዝግባዎች፡አላጨለሙትም፥ጥዶችም፡ቅርጫፎቹን፡አስታ፡የሚባለውም፡ዛፍ፡ ጫፎቹን፡አይመሳሰሉትም፡ነበር፤የእግዚአብሔርም፡ገነት፡ዛፍ፡ዅሉ፡በውበቱ፡አይመሳሰለውም፡ነበር።

9በጫፎቹም፡ብዛት፡ውብ፡አደረግኹት፡በእግዚአብሔርም፡ገነት፡በዔዴን፡የነበሩ፡ዛፎች፡ዅሉ፡ቀኑበት።

10ስለዚህ፥ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ቁመትኽ፡ከፍ፡ከፍ፡ብሏልና፥ራሱንም፡በደመናዎች፡ መካከል፡አድርጓልና፥

11ልቡም፡በቁመቱ፡ኰርቷልና፥ከአሕዛብ፡በጨካኙ፡እጅ፡አሳልፌ፡እሰጠዋለኹ፥ርሱም፡እንደ፡ክፋቱ፡ መጠን፡ያደርግበታል፡እኔም፡አሳድደዋለኹ።

12የሌላ፡አገር፡ሰዎች፥የአሕዛብ፡ጨካኞች፡የኾኑ፥ቈርጠው፡ጣሉት፤በተራራዎችና፡በሸለቆዎች፡ዅሉ፡ ውስጥ፡ጫፎቹ፡ወደቁ፥ቅርንጫፎቹም፡በምድር፡ፈሳሾች፡ዅሉ፡ላይ፡ተሰባበሩ፥የምድርም፡አሕዛብ፡ዅሉ፡ ከጥላው፡ተመልሰው፡ተዉት። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

14ወደ፡ጕድጓድ፡በሚወርዱ፡በሰው፡ልጆች፡መካከል፡ዅላቸው፡ለታችኛው፡ምድር፡ለሞት፡ዐልፈው፡ ተሰጥተዋልና፥በውሃ፡አጠገብ፡ያሉ፡ዛፎች፡ዅሉ፡በቁመታቸው፡እንዳይረዝሙ፥ራሳቸውንም፡በደመናዎች፡ መካከል፡እንዳያደርጉ፥ውሃንም፡የሚጠጡ፡ኀያላናቸው፡ዅሉ፡በቁመታቸው፡እንዳይቆሙ፥በወደቀው፡ግንድ፡ ላይ፡የሰማይ፡ወፎች፡ዅሉ፡ይቀመጣሉ፡የምድርም፡አራዊት፡ዅሉ፡በቅርንጫፎቹ፡ላይ፡ይኾናሉ።

15ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ወደ፡ሲኦል፡በወረደበት፡ቀን፡ልቅሶ፡አስለቀስኹ፤ቀላዩንም፡ስለ፡ ርሱ፡ሸፈንኹት፡ፈሳሾቹንም፡ከለከልኹ፡ታላላቆችም፡ውሃዎች፡ተከለከሉ፤ሊባኖስንም፡ስለ፡ርሱ፡ አሳዘንኹት፥የዱርም፡ዛፎች፡ዅሉ፡ስለ፡ርሱ፡ዛሉ።

16ወደ፡ጕድጓድ፡ከሚወርዱ፡ጋራ፡ወደ፡ሲኦል፡በጣልኹት፡ጊዜ፥ከመውደቁ፡ድምፅ፡የተነሣ፥አሕዛብን፡ አንቀጠቀጥኹ፤ውሃም፡የሚጠጡ፡ዅሉ፥ምርጦችና፡መልካካሞች፡የሊባኖስ፡ዛፎች፥የዔዴን፡ዛፎች፡ዅሉ፡ በታችኛው፡ምድር፡ውስጥ፡ተጽናንተዋል።

17ክንዱም፡ወደነበሩት፡በአሕዛብም፡መካከል፡በጥላው፡ወደተቀመጡት፥በሰይፍ፡ወደተገደሉት፡ሰዎች፡ወደ፡ ሲኦል፡ከርሱ፡ጋራ፡ወረዱ።

18በክብርና፡በታላቅነት፡በዔዴን፡ዛፎች፡መካከል፡ማንን፡መስለኻል፧ነገር፡ግን፡ከዔዴን፡ዛፎች፡ጋራ፡ወደ፡ ታችኛው፡ምድር፡ያወርዱኻል፥በሰይፍም፡በተገደሉት፡ባልተገረዙት፡መካከል፡ትተኛለኽ።ይህም፡ፈርዖንና፡ የሕዝቡ፡ብዛት፡ዅሉ፡ነው፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source