1የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
2የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ፊትኽን፡ወደሴይር፡ተራራ፡አድርግ፥ትንቢትም፡ተናገርበት፥
3እንዲህም፡በለው፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦የሴይር፡ተራራ፡ሆይ፥እንሆ፥ባንተ፡ላይ፡ ነኝ፥እጄንም፡እዘረጋብኻለኹ፡ባድማና፡ውድማም፡አደርግኻለኹ።
4ከተማዎችኽንም፡አፈራርሳቸዋለኹ፥አንተም፡ባድማ፡ትኾናለኽ፥እኔም፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ ታውቃለኽ።
5የዘለዓለም፡ጥል፡ስለ፡አለኽ፡በመከራቸውም፡ጊዜ፡በዃለኛዪቱ፡የኀጢአታቸው፡ቀጠሮ፡ጊዜ፡የእስራኤልን፡ ልጆች፡በሰይፍ፡እጅ፡ጥለኻቸዋልና፥
6ስለዚህ፥እኔ፡ሕያው፡ነኝና፡ለደም፡አሳልፌ፡እሰጥኻለኹ፥ደምም፡ያሳድድኻል፥ይላል፡ጌታ፡ እግዚአብሔር፤ደምን፡ስላልጠላኽ፥ደም፡ያሳድድኻል።
7የሴይርንም፡ተራራ፡ውድማ፡አደርገዋለኹ፥የሚኼደውንና፡የሚመለሰውንም፡ከርሱ፡አጠፋለኹ።
8ተራራዎቹንም፡በተገደሉት፡ሰዎች፡እሞላለኹ፤በኰረብታዎችኽና፡በሸለቆዎችኽ፡በፈሳሾችኽም፡ዅሉ፡ላይ፡ በሰይፍ፡የተገደሉት፡ዅሉ፡ይወድቃሉ።
9ለዘለዓለምም፡ባድማ፡አደርግኻለኹ፡ከተማዎችኽም፡ሰው፡የማይኖርባቸው፡ይኾናሉ፥እኔም፡እግዚአብሔር፡ እንደ፡ኾንኹ፡ታውቃላችኹ።
10እግዚአብሔርም፡በዚያ፡ሳለ፥አንተ፦እነዚህ፡ኹለቱ፡ሕዝቦች፡እነዚህም፡ኹለቱ፡አገሮች፡ለእኔ፡ይኾናሉ፡ እኛም፡እንወርሳቸዋለን፡ብለኻልና፥ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
11ስለዚህ፥እኔ፡ሕያው፡ነኝና፥እንደ፡ቍጣኽ፡መጠን፡እነርሱንም፡ጠልተኽ፡እንዳደረግኸው፥እንደ፡ ቅንአትኽ፡መጠን፡እኔ፡እሠራለኹ፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር፤በፈረድኩብኽም፡ጊዜ፡በእነርሱ፡ዘንድ፡ የታወቅኹ፡እኾናለኹ።
12አንተም፦ፈርሰዋል፡መብልም፡ኾነው፡ለእኛ፡ተሰጥተዋል፡ብለኽ፡በእስራኤል፡ተራራዎች፡ላይ፡ የተናገርኸውን፡ስድብ፡ዅሉ፡እኔ፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ሰማኹት፡ታውቃለኽ።
13በአፋችኹም፡ተመካችኹብኝ፥ቃላችኹንም፡አበዛችኹብኝ፤እኔም፡ሰምቼዋለኹ።
14ጌታ፡እግዚአብሔርም፡እንዲህ፡ይላል፦ምድር፡ዅሉ፡ደስ፡ሲላት፡አንተን፡ባድማ፡አደርግኻለኹ።
15የእስራኤል፡ቤት፡ርስት፡ባድማ፡ስለ፡ኾነ፡በላዩ፡ደስ፡እንዳለኽ፥እንዲሁ፡አደርግብኻለኹ፤የሴይር፡ ተራራ፡ሆይ፥አንተና፡ኤዶምያስ፡ዅሉ፡ዅለንተናውም፡ባድማ፡ትኾናላችኹ፤እኔም፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ ኾንኹ፡ያውቃሉ።