Skip to content
← Ezekiel

Chapter 37 · Amharic

Ezekiel

1የእግዚአብሔርም፡እጅ፡በላዬ፡ነበረ፡እግዚአብሔርም፡በመንፈሱ፡አወጣኝ፡ዐጥንቶችም፡በሞሉባት፡ሸለቆ፡ መካከል፡አኖረኝ።

2በእነርሱም፡አንጻር፡በዙሪያቸው፡አሳለፈኝ፤እንሆም፥በሸለቆው፡ፊት፡እጅግ፡ብዙ፡ነበሩ፥እንሆም፥እጅግ፡ ደርቀው፡ነበር።

3ርሱም፦የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥እነዚህ፡ዐጥንቶች፡በሕይወት፡ይኖራሉን፧አለኝ።እኔም፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡ ሆይ፥አንተ፡ታውቃለኽ፡አልኹ።

4ርሱም፡እንዲህ፡አለኝ፦በእነዚህ፡ዐጥንቶች፡ላይ፡ትንቢት፡ተናገር፡እንዲህም፡በላቸው፦እናንተ፡ የደረቃችኹ፡ዐጥንቶች፡ሆይ፥የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ሰሙ።

5ጌታ፡እግዚአብሔር፡ለእነዚህ፡ዐጥንቶች፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥ትንፋሽን፡አገባባችዃለኹ፡በሕይወትም፡ ትኖራላችኹ።

6ዥማትም፡እሰጣችዃለኹ፡ሥጋንም፡አወጣባችዃለኹ፡በእናንተም፡ላይ፡ቍርበትን፡እዘረጋለኹ፡ትንፋሽንም፡ አገባባችዃለኹ፡በሕይወትም፡ትኖራላችኹ፤እኔም፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ታውቃላችኹ።

7እንዳዘዘኝም፡ትንቢት፡ተናገርኹ፤ስናገርም፡ድምፅ፡ኾነ፥እንሆም፥መናወጥ፡ኾነ፥ዐጥንቶችም፡ዐጥንት፡ ከዐጥንት፡ጋራ፡ተቀራረቡ።

8እኔም፡አየኹ፥እንሆም፥ዥማት፡ነበረባቸው፡ሥጋም፡ወጣ፡ቍርበትም፡በላያቸው፡ተዘረጋ፥ትንፋሽ፡ግን፡ አልነበረባቸውም።

9ርሱም፦የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ትንቢት፡ተናገር፥ለነፋስ፡ትንቢት፡ተናገር፥ለነፋስም፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡ እንዲህ፡ይላል፦ነፋስ፡ሆይ፥ከአራቱ፡ነፋሳት፡ዘንድ፡ና፥እነዚህም፡የተገደሉት፡በሕይወት፡ይኖሩ፡ዘንድ፡ እፍ፡በልባቸው፡በል፡አለኝ።

10እንዳዘዘኝም፡ትንቢት፡ተናገርኹ፥ትንፋሽም፡ገባባቸው፡ሕያዋንም፡ኾኑ፥እጅግም፡ታላቅ፡ሰራዊት፡ኾነው፡ በእግራቸው፡ቆሙ።

11ርሱም፡እንዲህ፡አለኝ፦የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥እነዚህ፡ዐጥንቶች፡የእስራኤል፡ቤት፡ዅሉ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ናቸው፤እንሆ፦ዐጥንቶቻችን፡ደርቀዋል፡ተስፋችንም፡ጠፍቷል፡ፈጽመንም፡ተቈርጠናል፡ብለዋል።

12ስለዚህ፥ትንቢት፡ተናገር፥እንዲህም፡በላቸው፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ሕዝቤ፡ ሆይ፥እንሆ፥መቃብራችኹን፡እከፍታለኹ፡ከመቃብራችኹም፡አወጣችዃለኹ፥ወደእስራኤልም፡ምድር፡ አገባችዃለኹ።

13ሕዝቤ፡ሆይ፥መቃብራችኹን፡በከፈትኹ፡ጊዜ፡ከመቃብራችኹም፡ባወጣዃችኹ፡ጊዜ፥እኔ፡እግዚአብሔር፡ እንደ፡ኾንኹ፡ታውቃላችኹ።

14መንፈሴንም፡በውስጣችኹ፡አሳድራለኹ፥እናንተም፡በሕይወት፡ትኖራላችኹ፥በገዛ፡ምድራችኹም፡ አኖራችዃለኹ፤እኔም፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ተናገርኹ፡እንዳደረግኹም፡ታውቃላችኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር።

15የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦

16አንተ፥የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥አንድ፡በትር፡ውሰድና፦ለይሁዳና፡ለባልንጀራዎቹ፣ለእስራኤል፡ልጆች፡ብለኽ፡ በላዩ፡ጻፍ፤ሌላም፡በትር፡ውሰድና፦የኤፍሬም፡በትር፡ለዮሴፍና፡ለባልንጀራዎቹ፣ለእስራኤል፡ቤት፡ዅሉ፡ ብለኽ፡በላዩ፡ጻፍ።

17አንድ፡በትርም፡እንዲኾኑ፡አንዱን፡ከኹለተኛው፡ጋራ፡ለአንተ፡አጋጥም፥በእጅኽም፡ውስጥ፡አንድ፡ ይኹኑ።

18የሕዝብኽም፡ልጆች፦ይህ፡የምታደርገው፡ነገር፡ምን፡ማለት፡እንደ፡ኾነ፡አትነግረንምን፧ብለው፡ በተናገሩኽ፡ጊዜ፥

19አንተ፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥በኤፍሬም፡እጅ፡ያለውን፡የዮሴፍን፡በትር፡ ባልንጀራዎቹንም፡የእስራኤልን፡ነገዶች፡እወስዳለኹ፥ከርሱም፡ከይሁዳ፡በትር፡ጋራ፡አጋጥማቸዋለኹ፡አንድ፡ በትርም፡አደርጋቸዋለኹ፥በእጄም፡ውስጥ፡አንድ፡ይኾናሉ፡በላቸው።

20የምትጽፍባቸውም፡በትሮች፡በዐይናቸው፡ፊት፡በእጅኽ፡ውስጥ፡ይኾናሉ።

21አንተም፡እንዲህ፡ትላቸዋለኽ፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥የእስራኤልን፡ልጆች፡ ከኼዱባቸው፡ከአሕዛብ፡መካከል፡እወስዳለኹ፡ከስፍራም፡ዅሉ፡እሰበስባቸዋለኹ፡ወደገዛ፡ምድራቸውም፡ አመጣቸዋለኹ፤

22በምድርም፡ላይ፡በእስራኤል፡ተራራዎች፡ላይ፡አንድ፡ሕዝብ፡አደርጋቸዋለኹ፥አንድ፡ንጉሥም፡ በኹላቸው፡ላይ፡ይነግሣል፤ከዚያ፡ወዲያ፡ኹለት፡ሕዝብ፡አይኾኑም፥ከዚያ፡ወዲያም፡ኹለት፡መንግሥቶች፡ ኾነው፡አይለዩም።

23ከዚያ፡ወዲያም፡በጣዖቶቻቸውና፡በርኵሰታቸው፡በመተላለፋቸውም፡ዅሉ፡አይረክሱም፥ኀጢአትም፡ ከሠሩባት፡ዐመፅ፡ዅሉ፡አድናቸዋለኹ፡አነጻቸውማለኹ፤ሕዝብም፡ይኾኑኛል፡እኔም፡አምላክ፡እኾናቸዋለኹ።

24ባሪያዬም፡ዳዊት፡ንጉሥ፡ይኾናቸዋል፤ለዅሉም፡አንድ፡እረኛ፡ይኾንላቸዋል፤በፍርዴም፡ይኼዳሉ፡ ትእዛዜንም፡ይጠብቃሉ፡ያደርጓትማል።

25አባቶቻችኹም፡በኖሩበት፡ለባሪያዬ፡ለያዕቆብ፡በሰጠዃት፡ምድር፡ይኖራሉ፤እነርሱና፡ልጆቻቸው፡የልጅ፡ ልጆቻቸውም፡ለዘለዓለም፡ይኖሩባታል፤ባሪያዬም፡ዳዊት፡ለዘለዓለም፡አለቃ፡ይኾናቸዋል።

26የሰላምም፡ቃል፡ኪዳን፡ከነርሱ፡ጋራ፡አደርጋለኹ፥የዘለዓለምም፡ቃል፡ኪዳን፡ይኾንላቸዋል፤እኔም፡ እባርካቸዋለኹ፡አበዛቸውማለኹ፡መቅደሴንም፡ለዘለዓለም፡በመካከላቸው፡አኖራለኹ።

27ማደሪያዬም፡በላያቸው፡ላይ፡ይኾናል፤እኔም፡አምላክ፡እኾናቸዋለኹ፡እነርሱም፡ሕዝብ፡ይኾኑኛል።

28መቅደሴም፡ለዘለዓለም፡በመካከላቸው፡በኾነ፡ጊዜ፥እኔ፡እስራኤልን፡የምቀድሰው፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ ኾንኹ፡አሕዛብ፡ያውቃሉ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source