Skip to content
← Ezekiel

Chapter 39 · Amharic

Ezekiel

1አንተም፥የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥በጎግ፡ላይ፡ትንቢትን፡ተናገር፡እንዲህም፡በል፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ ይላል፦የሞሳሕና፡የቶቤል፡ዋነኛ፡አለቃ፡ጎግ፡ሆይ፥እንሆ፥እኔ፡ባንተ፡ላይ፡ነኝ፤

2እመልስኻለኹ፥እነዳኽማለኹ፥ከሰሜንም፡ዳርቻ፡እጐትትኻለኹ፥ወደእስራኤልም፡ተራራዎች፡አመጣኻለኹ።

3ከግራ፡እጅኽም፡ቀስትኽን፡አስጥልኻለኹ፥ከቀኝ፡እጅኽም፡ፍላጻዎችኽን፡አስረግፍኻለኹ።

4አንተና፡ጭፍራዎችኽ፡ዅሉ፡ከአንተም፡ጋራ፡ያሉ፡ሕዝብ፡በእስራኤል፡ተራራዎች፡ላይ፡ ትወድቃላችኹ፤ለሚናጠቁ፡ወፎች፡ዅሉና፡ለምድር፡አራዊትም፡መብል፡አድርጌ፡እሰጥኻለኹ።

5አንተ፡በምድር፡ፊት፡ላይ፡ትወድቃለኽ፤እኔ፡ተናግሬያለኹና፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።

6በማጎግም፡ላይ፡ሳይፈሩም፡በደሴቶች፡በሚቀመጡ፡ላይ፡እሳትን፡እሰዳ፟ለኹ፤እኔም፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ ኾንኹ፡ያውቃሉ።

7ቅዱሱም፡ስሜ፡በሕዝቤ፡በእስራኤል፡መካከል፡ይታወቅ፡ዘንድ፡አደርጋለኹ፥ቅዱሱንም፡ስሜን፡ከእንግዲህ፡ ወዲህ፡አላስረክስም፤አሕዛብም፡እግዚአብሔር፥የእስራኤል፡ቅዱስ፥እኔ፡እንደ፡ኾንኹ፡ያውቃሉ።

8እንሆ፥ይመጣል፡ይኾንማል፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር፤ያልኹት፡ቀን፡ይህ፡ነው።

9በእስራኤልም፡ከተማዎች፡የሚኖሩ፡ይወጣሉ፥የጦር፡መሣሪያዎችንም፡በእሳት፡ያቃጥላሉ፤አላባሽ፡ጋሻንና፡ ጋሻን፥ቀስትንና፡ፍላጻዎችን፥ጐመድንና፡ጦርንም፡ያቃጥላሉ፤ሰባት፡ዓመት፡በእሳት፡ያቃጥሏቸዋል።

10በጦር፡መሣሪያው፡እሳትን፡ያነዳ፟ሉ፡እንጂ፡ዕንጨትን፡ከምድረ፡በዳ፡አይወስዱም፡ከዱርም፡ አይቈርጡም፤የገፈፏቸውንም፡ይገፋ፟ሉ፡የበዘበዟቸውንም፡ይበዘብዛሉ፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።

11በዚያም፡ቀን፡በእስራኤል፡ዘንድ፡በባሕር፡ምሥራቅ፡የሚያልፉበትን፡ሸለቆ፡የመቃብርን፡ስፍራ፡ለጎግ፡ እሰጣለኹ፥የሚያልፉትንም፡ይከለክላል፤በዚያም፡ጎግንና፡ብዛቱን፡ዅሉ፡ይቀብራሉ፤የሸለቆውንም፡ስም፡ ሐሞንጎግ፡ብለው፡ይጠሩታል።

12ምድሩንም፡ያጸዱ፡ዘንድ፥የእስራኤል፡ቤት፡ሰዎች፡ሰባት፡ወር፡ይቀብሯቸዋል፥

13የምድርም፡ሕዝብ፡ዅሉ፡ይቀብሯቸዋል፥በተመሰገንኹበትም፡ቀን፡ለክብር፡ይኾንላችዃል፥ይላል፡ጌታ፡ እግዚአብሔር።

14ምድርንም፡ለማጽዳት፡በምድሩ፡ላይ፡ወድቀው፡የቀሩትን፡የሚቀብሩ፥ዘወትር፡በምድሩ፡ላይ፡የሚዞሩትን፡ ሰዎች፡ይቀጥራሉ፤ከሰባት፡ወርም፡በዃላ፡ይመረምራሉ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

15በምድርም፡የሚዞሩት፡ያልፋሉ፤የሰውንም፡ዐጥንት፡ቢያዩ፥ቀባሪዎች፡በሐሞን፡ጎግ፡ሸለቆ፡እስኪቀብሩት፡ ድረስ፡ምልክት፡ያኖሩበታል።

16ደግሞም፡የከተማዪቱ፡ስም፡ሐሞና፡ይባላል።እንዲሁ፡ምድሪቱን፡ያጸዳሉ።

17አንተም፥የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ለወፎች፡ዅሉና፡ለምድር፡አራዊት፡ ዅሉ፡እንዲህ፡በላቸው፦ኑ፥ተከማቹ፥ሥጋንም፡ትበሉ፡ዘንድ፥ደምንም፡ትጠጡ፡ዘንድ፥በእስራኤል፡ ተራራዎች፡ላይ፡ወደማርድላችኹ፡መሥዋዕት፥ርሱም፡ታላቅ፡መሥዋዕት፥ከየስፍራው፡ዅሉ፡ተሰብሰቡ።

18የኀያላኑን፡ሥጋ፡ትበላላችኹ፡የምድርንም፡አለቃዎች፥የአውራ፡በጎችንና፡የጠቦቶችን፥የፍየሎችንና፡ የወይፈኖችን፥የባሳንን፡ፍሪዳዎች፡ዅሉ፥ደም፡ትጠጣላችኹ።

19እኔም፡ከማርድላችኹ፡መሥዋዕት፡እስክትጠግቡ፡ድረስ፡ጮማ፡ትበላላችኹ፡እስክትሰክሩም፡ድረስ፡ደም፡ ትጠጣላችኹ።

20በሰደቃዬም፡ከፈረሶችና፡ከፈረሰኛዎች፥ከኀያላንና፡ከሰልፈኛዎች፡ዅሉ፡ትጠግባላችኹ፥ይላል፡ጌታ፡ እግዚአብሔር።

21ክብሬንም፡በአሕዛብ፡መካከል፡አኖራለኹ፡አሕዛብም፡ዅሉ፡ያደርግኹትን፡ፍርዴን፥በላያቸውም፡ ያኖርዃትን፡እጄን፡ያያሉ።

22ከእንግዲህም፡ወዲያ፡የእስራኤል፡ቤት፡እኔ፡እግዚአብሔር፡አምላካቸው፡እንደ፡ኾንኹ፡ያውቃሉ።

23አሕዛብም፡የእስራኤል፡ቤት፡በኀጢአታቸው፡ምክንያት፡እንደ፡ተማረኩ፡ያውቃሉ፤ስለ፡በደሉኝ፡እኔም፡ ፊቴን፡ከነርሱ፡ስለ፡ሸሸግኹ፥በጠላቶቻቸው፡እጅ፡አሳልፌ፡ሰጠዃቸው፥እነርሱም፡ዅሉ፡በሰይፍ፡ወደቁ።

24እንደ፡ርኵሰታቸውም፡እንደ፡መተላለፋቸውም፡መጠን፡አደረግኹባቸው፡ፊቴንም፡ከነርሱ፡ሸሸግኹ።

25ስለዚህ፥ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦አኹን፡የያዕቆብን፡ምርኮ፡እመልሳለኹ፡ለእስራኤልም፡ ቤት፡ዅሉ፡እራራለኹ፥ስለ፡ቅዱስ፡ስሜም፡እቀናለኹ።

27ማንም፡ሳያስፈራቸው፡በምድራቸው፡ተዘልለው፡በተቀመጡ፡ጊዜ፡ከአሕዛብም፡ዘንድ፡በመለስዃቸው፡ ጊዜ፡ከጠላቶቻቸውም፡ምድር፡በሰበሰብዃቸው፡ጊዜ፡በብዙ፡አሕዛብም፡ፊት፡በተቀደስኹባቸው፡ ጊዜ፥ዕፍረታቸውንና፡የበደሉኝን፡በደላቸውን፡ዅሉ፡ይሸከማሉ።

28እኔም፡ወደ፡አሕዛብ፡አስማርኬያቸዋለኹና፥ወደገዛ፡ምድራቸውም፡ሰብስቤያቸዋለኹና፡እኔ፡እግዚአብሔር፡ አምላካቸው፡እንደ፡ኾንኹ፡ያውቃሉ፤በዚያም፡ከነርሱ፡አንድ፡ሰው፡ከእንግዲህ፡ወዲያ፡አልተውም፥

29ፊቴንም፡ከነርሱ፡ከእንግዲህ፡ወዲህ፡አልሸሽግም፤መንፈሴን፡በእስራኤል፡ቤት፡ላይ፡ አፍስሻለኹና፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source