Skip to content
← Ezekiel

Chapter 40 · Amharic

Ezekiel

1በተማረክን፡በኻያ፡ዐምስተኛው፡ዓመት፡በዓመቱ፡መዠመሪያ፡ከወሩ፡በዐሥረኛው፡ቀን፥ከተማዪቱ፡ ከተመታች፡በዃላ፡በዐሥራ፡አራተኛው፡ዓመት፥በዚያው፡ቀን፡የእግዚአብሔር፡እጅ፡በእኔ፡ላይ፡ነበረ፡ርሱም፡ ወደዚያ፡ወሰደኝ።

2በእግዚአብሔር፡ራእይ፡ወደእስራኤል፡ምድር፡አመጣኝ፡እጅግም፡በረዘመ፡ተራራ፡ላይ፡አኖረኝ፥በዚያም፡ ላይ፡በደቡብ፡ወገን፡እንደ፡ከተማ፡ኾኖ፡የተሠራ፡ነገር፡ነበረ።

3ወደዚያም፡አመጣኝ፥እንሆም፥መልኩ፡እንደ፡ናስ፡መልክ፡የመሰለ፡አንድ፡ሰው፡በዚያ፡ነበረ፥በእጁም፡ የተልባ፡እግር፡ገመድና፡የመለኪያ፡ዘንግ፡ነበረ፤ርሱም፡በበሩ፡አጠገብ፡ቆሞ፡ነበር።

4ሰውዬውም፦የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ይህን፡አሳይኽ፡ዘንድ፡አንተ፡ወደዚህ፡ተመርተኻልና፥በዐይንኽ፡ እይ፥በዦሮኽም፡ስማ፥በማሳይኽም፡ዅሉ፡ላይ፡ልብኽን፡አድርግ፤የምታየውንም፡ዅሉ፡ለእስራኤል፡ቤት፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ንገር፡አለኝ።

5እንሆም፥በቤቱ፡ውጭ፡በዙሪያው፡ቅጥር፡ነበረ፥በሰውዬውም፡እጅ፡የክንዱ፡ልክ፡አንድ፡ክንድ፡ከጋት፡ የኾነ፡ስድስት፡ክንድ፡ያለበት፡የመለኪያ፡ዘንግ፡ነበረ፤የቅጥሩንም፡ስፋት፡አንድ፡ዘንግ፡ቁመቱንም፡አንድ፡ ዘንግ፡አድርጎ፡ለካ።

6ወደ፡ምሥራቅ፡ወደሚመለከተውም፡በር፡መጣ፡በደረጃዎቹም፡ላይ፡ወጣ፥በበሩ፡በኩል፡ያለውንም፡ የመድረኩን፡ወለል፡ወርዱን፡አንድ፡ዘንግ፡አድርጎ፡ለካ።

7የዘበኛውም፡ጓዳ፡ዅሉ፡ርዝመቱ፡አንድ፡ዘንግ፥ወርዱም፡አንድ፡ዘንግ፡ነበረ፤በዘበኛውም፡ጓዳዎች፡ መካከል፡ዐምስት፡ክንድ፡ነበረ፤በበሩም፡ደጀ፡ሰላም፡በስተውስጥ፡በኩል፡የሚገኝ፡የበሩ፡የመድረክ፡ወለል፡ አንድ፡ዘንግ፡ነበረ።

8በስተውስጥም፡ያለውን፡የበሩን፡ደጀ፡ሰላም፡አንድ፡ዘንግ፡አድርጎ፡ለካ።

9የበሩንም፡ደጀ፡ሰላም፡ስምንት፡ክንድ፥የግንቡንም፡አዕማድ፡ወርድ፡ኹለት፡ክንድ፡አድርጎ፡ለካ፤የበሩም፡ ደጀ፡ሰላም፡በስተውስጥ፡ነበረ።

10የምሥራቁም፡በር፡የዘበኛ፡ጓዳዎች፡በዚህ፡በኩል፡ሦስት፡በዚያም፡በኩል፡ሦስት፡ነበሩ፥ለሦስቱም፡አንድ፡ ልክ፡ነበረ፤የግንቡም፡አዕማድ፡ወርድ፡በዚህ፡በኩልና፡በዚያ፡በኩል፡አንድ፡ልክ፡ነበረ።

11የበሩንም፡መግቢያ፡ወርድ፡ዐሥር፡ክንድ፡የበሩንም፡ርዝመት፡ዐሥራ፡ሦስት፡ክንድ፡አድርጎ፡ለካ።

12በዘበኛ፡ጓዳዎችም፡ፊት፡በዚህ፡በኩል፡አንድ፡ክንድ፡በዚያም፡በኩል፡አንድ፡ክንድ፡የኾነ፡ዳርቻ፡ ነበረ፤የዘበኛ፡ጓዳዎቹም፡በዚህ፡በኩል፡ስድስት፡ክንድ፡በዚያም፡በኩል፡ስድስት፡ክንድ፡ነበሩ።

13ከአንዱም፡የዘበኛ፡ጓዳ፡ደርብ፡ዠምሮ፡እስከ፡ሌላው፡ደርብ፡ድረስ፡የበሩን፡ወርድ፡ኻያ፡ዐምስት፡ ክንድ፡አድርጎ፡ለካ፤መዝጊያውና፡መዝጊያውም፡ትይዩ፡ነበረ።

14ደጀ፡ሰላሙንም፡ኻያ፡ክንድ፡አድርጎ፡ለካ፤በበሩም፡ደጀ፡ሰላም፡ዙሪያ፡አደባባይ፡ነበረ።

15ከበሩም፡መግቢያ፡ፊት፡ዠምሮ፡እስከ፡ውስጠኛው፡የበሩ፡ደጀ፡ሰላም፡መጨረሻ፡ድረስ፡ዐምሳ፡ክንድ፡ ነበረ።

16በዘበኛ፡ጓዳዎቹም፡በበሩ፡ውስጥ፡በዙሪያው፡በነበሩትም፡በግንቡ፡አዕማድ፡የዐይነ፡ርግብ፡መስኮቶች፡ ነበሩባቸው፤ደግሞም፡በደጀ፡ሰላሙ፡ውስጥ፡በዙሪያው፡መስኮቶች፡ነበሩ፤በግንቡም፡አዕማድ፡ዅሉ፡ላይ፡ የዘንባባ፡ዛፍ፡ተቀርጾባቸው፡ነበር።

17ወደውጭውም፡አደባባይ፡አመጣኝ፥እንሆም፥በአደባባዩ፡ዙሪያ፡የተሠሩ፡ዕቃ፡ቤቶችና፡ወለል፡ ነበሩ፤በወለሉም፡ላይ፡ሠላሳ፡ዕቃ፡ቤቶች፡ነበሩ።

18ወለሉም፡በበሮች፡አጠገብ፡ነበረ፡ይህም፡ታችኛው፡ወለል፡እንደ፡በሮቹ፡ርዝመት፡መጠን፡ነበረ።

19ከታችኛውም፡በር፡ፊት፡ዠምሮ፡እስከ፡ውስጠኛው፡አደባባይ፡ፊት፡ድረስ፡ወርዱን፡አንድ፡መቶ፡ክንድ፡ አድርጎ፡ለካ።

20ወደ፡ሰሜንም፡መራኝ፥እንሆም፥በውጭው፡አደባባይ፡ያለ፡ወደ፡ሰሜን፡የሚመለከት፡በር፡ ነበረ፤ርዝመቱንና፡ወርዱንም፡ለካ፥

21የዘበኛ፡ጓዳዎቹም፡በዚህ፡በኩል፡ሦስት፡በዚያም፡በኩል፡ሦስት፡ነበሩ፤የግንቡ፡አዕማድና፡ መዛነቢያዎቹም፡እንደ፡ፊተኛው፡በር፡ልክ፡ነበሩ፤ርዝመቱ፡ዐምሳ፡ክንድ፡ወርዱም፡ኻያ፡ዐምስት፡ክንድ፡ ነበረ።

22መስኮቶቹም፡መዛነቢያዎቹም፡የዘንባባ፡ዛፎቹም፡ወደ፡ምሥራቅ፡እንደሚመለከተው፡በር፡ልክ፡ ነበሩ።ወደ፡ርሱም፡የሚያደርሱ፡ሰባት፡ደረጃዎች፡ነበሩ፡መዛነቢያዎቹም፡በፊቱ፡ነበሩ።

23በውስጠኛውም፡አደባባይ፡በሰሜኑና፡በምሥራቁ፡በኩል፡በሌላው፡በር፡አንጻር፡በር፡ነበረ፤ከበርም፡ወደ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org በር፡አንድ፡መቶ፡ክንድ፡አድርጎ፡ለካ።

24ወደ፡ደቡብም፡መራኝ፥እንሆም፥ወደ፡ደቡብ፡የሚመለከት፡በር፡ነበረ፤የግንቡን፡አዕማድና፡ መዛነቢያዎቹንም፡እንደዚያው፡መጠን፡አድርጎ፡ለካ።

25በርሱና፡በመዛነቢያዎቹም፡ዙሪያ፡እንደ፡እነዚያ፡መስኮቶች፡የሚመስሉ፡መስኮቶች፡ነበሩ፤ርዝመቱ፡ ዐምሳ፡ክንድ፡ወርዱም፡ኻያ፡ዐምስት፡ክንድ፡ነበረ።

26ወደ፡ርሱም፡የሚያደርሱ፡ሰባት፡ደረጃዎች፡ነበሩ፥መዛነቢያዎቹም፡በፊቱ፡ነበሩ፤በግንቡም፡አዕማድ፡ ላይ፡አንዱ፡በዚህ፡አንዱም፡በዚያ፡ወገን፡ኾኖ፡የዘንባባ፡ዛፍ፡ተቀርጾባቸው፡ነበር።

27በውስጠኛውም፡አደባባይ፡በደቡብ፡በኩል፡በር፡ነበረ፤ከበር፡እስከ፡በር፡ድረስ፡በደቡብ፡በኩል፡መቶ፡ ክንድ፡አድርጎ፡ለካ።

28በደቡብም፡በር፡በኩል፡ወደ፡ውስጠኛው፡አደባባይ፡አገባኝ፤እንደዚያውም፡መጠን፡አድርጎ፡የደቡብን፡ በር፡ለካ፤

29እንደዚያውም፡መጠን፡አድርጎ፡የዘበኛ፡ጓዳዎቹንና፡የግንቡን፡አዕማድ፡መዛነቢያዎቹንም፡ለካ፤በርሱና፡ በመዛነቢያዎቹም፡ዙሪያ፡መስኮቶች፡ነበሩ፤ርዝመቱ፡ዐምሳ፡ክንድ፡ወርዱም፡ኻያ፡ዐምስት፡ክንድ፡ነበረ።

30በዙሪያውም፡ደጀ፡ሰላሞች፡ነበሩ፤ርዝመታቸውም፡ኻያ፡ዐምስት፡ክንድ፡ወርዳቸውም፡ዐምስት፡ክንድ፡ ነበረ።

31መዛነቢያዎቹም፡ወደ፡ውጭው፡አደባባይ፡ይመለከቱ፡ነበር፤በግንቡም፡አዕማድ፡ላይ፡የዘንባባ፡ዛፍ፡ ተቀርጾ፡ነበር፤ወደ፡ርሱም፡የሚያደርሱ፡ስምንት፡ደረጃዎች፡ነበሩ።

32በውስጠኛውም፡አደባባይ፡በምሥራቅ፡በኩል፡አገባኝ፥እንደዚያውም፡መጠን፡በሩን፡ለካ፤

33እንደዚያውም፡መጠን፡የዘበኛ፡ጓዳዎቹንና፡የግንቡን፡አዕማድ፡መዛነቢያዎቹንም፡ለካ፤በርሱና፡ በመዛነቢያዎቹም፡ዙሪያ፡መስኮቶች፡ነበሩ፥ርዝመቱም፡ዐምሳ፡ክንድ፡ወርዱም፡ኻያ፡ዐምስት፡ክንድ፡ነበረ።

34መዛነቢያዎቹም፡በስተውጭ፡ወዳለው፡አደባባይ፡ይመለከቱ፡ነበር፤በግንቡም፡አዕማድ፡ላይ፡በዚህና፡ በዚያ፡ወገን፡የዘንባባ፡ዛፍ፡ተቀርጾ፡ነበር፤ወደ፡ርሱም፡የሚያደርሱ፡ስምንት፡ደረጃዎች፡ነበሩት።

35በሰሜንም፡ወዳለው፡በር፡አመጣኝ፥እንደዚያውም፡መጠን፡ለካው፤

36የዘበኛ፡ጓዳዎቹንና፡የግንቡን፡አዕማድ፡መዛነቢያዎቹንም፡ለካ፤በዙሪያውም፡መስኮቶች፡ ነበሩበት፥ርዝመቱም፡ዐምሳ፡ክንድ፡ወርዱም፡ኻያ፡ዐምስት፡ክንድ፡ነበረ።

37የግንቡም፡አዕማድ፡ወደ፡ውጭው፡አደባባይ፡ይመለከቱ፡ነበር፤በግንቡም፡አዕማድ፡ላይ፡በዚህና፡በዚያ፡ ወገን፡የዘንባባ፡ዛፍ፡ተቀርጾ፡ነበር፤ወደ፡ርሱም፡የሚያደርሱ፡ስምንት፡ደረጃዎች፡ነበሩት።

38በበሮቹም፡በግንብ፡አዕማድ፡አጠገብ፡ዕቃ፡ቤቱና፡መዝጊያው፡ነበሩ፤በዚያም፡የሚቃጠለውን፡ መሥዋዕት፡ያጥቡ፡ነበር።

39የሚቃጠለውንም፡መሥዋዕት፡የኀጢአቱንና፡የበደሉንም፡መሥዋዕት፡ያርዱባቸው፡ዘንድ፥በበሩ፡ደጀ፡ ሰላም፡በዚህ፡ወገን፡ኹለት፡ገበታዎች፥በዚያም፡ወገን፡ኹለት፡ገበታዎች፡ነበሩ።

40በሰሜን፡በኩል፡ባለው፡በር፡በስተውጭው፥በመወጣጫው፡ደረጃዎች፡አጠገብ፥ባንድ፡ወገን፡ኹለት፡ ገበታዎች፡ነበሩ፥በሌላውም፡ወገን፡በበሩ፡ደጀ፡ሰላም፡በኩል፡ኹለት፡ገበታዎች፡ነበሩ።

41በበሩ፡አጠገብ፡በዚህ፡ወገን፡አራት፡ገበታዎች፡በዚያም፡ወገን፡አራት፡ገበታዎች፡ነበሩ፤መሥዋዕት፡ የሚያርዱባቸው፡ገበታዎች፡ስምንት፡ነበሩ።

42ስለሚቃጠለውም፡መሥዋዕት፡ርዝመታቸው፡ክንድ፡ተኩል፡ወርዳቸውም፡ክንድ፡ተኩል፡ቁመታቸውም፡ አንድ፡ክንድ፡የኾኑ፥የሚቃጠለውን፡መሥዋዕትና፡ሌላ፡መሥዋዕቱን፡የሚያርዱበትን፡ዕቃ፡ያኖሩባቸው፡ ዘንድ፥ከተጠረበ፡ድንጋይ፡የተሠሩ፡አራት፡ገበታዎች፡ነበሩ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

43በዙሪያውም፡አንድ፡ጋት፡የኾነ፡ክፈፍ፡ወደ፡ውስጥ፡ተቀልብሶ፡ነበር፤በገበታዎቹም፡ላይ፡የቍርባኑ፡ ሥጋ፡ነበረባቸው።

44ወደ፡ውስጠኛውም፡አደባባይ፡አገባኝ፥እንሆም፥ኹለት፡ቤቶች፡ነበሩ፤አንዱ፡ወደ፡ሰሜን፡በሚመለከት፡ በር፡አጠገብ፡ነበረ፥መግቢያውም፡ወደ፡ደቡብ፡ይመለከት፡ነበር፤ሌላውም፡ወደ፡ደቡብ፡በሚመለከተው፡ በር፡አጠገብ፡ነበረ፥መግቢያውም፡ወደ፡ሰሜን፡ይመለከት፡ነበር።

45ሰውዬውም፦ይህ፡ወደ፡ደቡብ፡የሚመለከት፡ቤት፡ለማገልገል፡ለሚተጉ፡ካህናት፡ነው።

46ወደ፡ሰሜንም፡የሚመለከተው፡ቤት፡መሠዊያውን፡ለማገልገል፡ለሚተጉ፡ካህናት፡ነው፤እነዚህ፡ከሌዊ፡ ልጆች፡መካከል፡ያገለግሉት፡ዘንድ፥ወደ፡እግዚአብሔር፡የሚቀርቡ፡የሳዶቅ፡ልጆች፡ናቸው፡አለኝ።

47አደባባዩንም፡በአራት፡ማእዘኑ፡ርዝመቱን፡መቶ፡ክንድ፡ወርዱንም፡መቶ፡ክንድ፡አድርጎ፡ ለካ፤መሠዊያውም፡በቤቱ፡ፊት፡ነበረ።

48ወደቤቱም፡ደጀ፡ሰላም፡አመጣኝ፥የደጀ፡ሰላሙንም፡የግንብ፡አዕማድ፡ወርድ፡በዚህ፡ወገን፡ዐምስት፡ ክንድ፡በዚያም፡ወገን፡ዐምስት፡ክንድ፡አድርጎ፡ለካ፤የበሩም፡ወርድ፡ዐሥራ፡አራት፡ክንድ፡ነበረ፥በበሩም፡ በዚህ፡ወገንና፡በዚያ፡ወገን፡የነበሩት፡ግንቦች፡ሦስት፡ሦስት፡ክንድ፡ነበሩ።

49የደጀ፡ሰላሙም፡ርዝመት፡ኻያ፡ክንድ፡ወርዱም፡ዐሥራ፡ኹለት፡ክንድ፡ነበረ፥ወደ፡ርሱም፡ የሚያደርሱ፡ዐሥር፡ደረጃዎች፡ነበሩ፤አንድ፡በዚህ፡ወገን፡አንድም፡በዚያ፡ወገን፡ኾነው፡በመቃኖቹ፡አጠገብ፡ የግንብ፡አዕማድ፡ነበሩ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source