Skip to content
← Ezekiel

Chapter 41 · Amharic

Ezekiel

1ወደ፡መቅደሱም፡አገባኝ፥የግንቡንም፡አዕማድ፡ወርድ፡በዚህ፡ወገን፡ስድስት፡ክንድ፡በዚያም፡ወገን፡ ስድስት፡ክንድ፡አድርጎ፡ለካ።

2የመግቢያውም፡ወርድ፡ዐሥር፡ክንድ፡ነበረ፥የመግቢያውም፡መቃኖች፡በዚህ፡ወገን፡ዐምስት፡ክንድ፡ በዚያም፡ወገን፡ዐምስት፡ክንድ፡ነበሩ፤ርዝመቱንም፡አርባ፡ክንድ፡ወርዱንም፡ኻያ፡ክንድ፡አድርጎ፡ለካ።

3ወደ፡ውስጥም፡ገባ፥የመግቢያውንም፡የግንብ፡አዕማድ፡ወርድ፡ኹለት፡ክንድ፡አድርጎ፡ ለካ፤የመግቢያውም፡ወርድ፡ስድስት፡ክንድ፡ነበረ፥የመግቢያውም፡ግንብ፡ወርድ፡በዚህ፡ወገን፡ሰባት፡ክንድ፡ በዚያም፡ወገን፡ሰባት፡ክንድ፡ነበረ።

4በመቅደሱም፡ፊት፡ርዝመቱን፡ኻያ፡ክንድ፡ወርዱንም፡ኻያ፡ክንድ፡አድርጎ፡ለካና፦ይህ፡ቅድስተ፡ ቅዱሳን፡ነው፡አለኝ።

5የመቅደሱንም፡ግንብ፡ስድስት፡ክንድ፡አድርጎ፥በመቅደሱም፡ዙሪያ፡ዅሉ፡ያሉትን፡የጓዳዎቹን፡ዅሉ፡ ወርድ፡አራት፡ክንድ፡አድርጎ፡ለካ።

6ጓዳዎቹም፡አንዱ፡ከአንዱ፡በላይ፡በሦስት፡ደርብ፡ነበሩ፥በያንዳንዱም፡ደርብ፡ሠላሳ፡ጓዳዎች፡ ነበሩ።በመቅደሱም፡ግንብ፡ዙሪያ፡ደገፋዎች፡ይኾኑ፡ዘንድ፥አረፍቶች፡ነበሩ፥በመቅደሱም፡ግንብ፡ውስጥ፡ ደገፋዎች፡አልነበሩም።

7በቤቱም፡ዙሪያ፡ባለ፡ግንብ፡ውስጥ፡በነበሩት፡አረፍቶች፡ምክንያት፡ላይኛዎቹ፡ጓዳዎች፡ከታችኛዎቹ፡ ጓዳዎች፡ይበልጡ፡ነበር፤ከታችኛውም፡ደርብ፡ወደ፡መካከለኛው፡ከመካከለኛውም፡ደርብ፡ወደ፡ላይኛው፡ የሚወጣበት፡ደረጃ፡ነበረ።

8ለመቅደሱም፡ከፍ፡ያለ፡ወለል፡በዙሪያው፡እንዳለው፡አየኹ፤የጓዳዎቹም፡መሠረት፡ቁመቱ፡ሙሉ፡ዘንግ፡ የሚያኽል፡ስድስት፡ትልቅ፡ክንድ፡ነበረ።

9የጓዳዎቹም፡የውጭው፡ግንብ፡ውፍረት፡ዐምስት፡ክንድ፡ነበረ፤በመቅደሱም፡ጓዳዎች፡አጠገብ፡የቀረ፡ አንድ፡ባዶ፡ስፍራ፡ነበረ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

11በዚህም፡በባዶው፡ስፍራ፡አንዱ፡በሰሜን፡በኩል፡አንዱም፡በደቡብ፡በኩል፡የጓዳዎች፡መግቢያ፡ነበረ፡ የባዶውም፡ስፍራ፡ወርድ፡በዙሪያ፡ዐምስት፡ክንድ፡ነበረ።በመቅደሱም፡ዙሪያ፡ወርዱ፡ኻያ፡ክንድ፡የኾነ፡ልዩ፡ ስፍራ፡ነበረ።

12በምዕራብም፡በኩል፡በልዩ፡ስፍራ፡አንጻር፡የነበረ፡ግቢ፡ስፋቱ፡ሰባ፡ክንድ፡ነበረ።በግቢውም፡ዙሪያ፡ የነበረ፡ግንብ፡ውፍረቱ፡ዐምስት፡ክንድ፡ርዝመቱም፡ዘጠና፡ክንድ፡ነበረ።

13የመቅደሱንም፡ርዝመት፡መቶ፡ክንድ፥የልዩውን፡ስፍራና፡ግቢውን፡ከግንቡ፡ጋራ፡አንድ፡መቶ፡ክንድ፡ አድርጎ፡ለካ።

14ደግሞም፡በምሥራቅ፡በኩል፡የነበረውን፡የመቅደሱንና፡የልዩውን፡ስፍራ፡ወርድ፡አንድ፡መቶ፡ክንድ፡ አድርጎ፡ለካ።

15ወደ፡ዃላውም፡ባለው፡በልዩ፡ስፍራ፡አንጻር፡የነበረውን፡የግቢውን፡ርዝመት፡በዚህና፡በዚያም፡ከነበሩት፡ ከግንቦቹ፡ጋራ፡አንድ፡መቶ፡ክንድ፡አድርጎ፡ለካ።

16መድረኮቹ፥መቅደሱና፡በስተውስጥ፡ያለው፡ክፍል፡ደጀ፡ሰላሙም፡በዕንጨት፡ተለብጠው፡ ነበር፥በሦስቱም፡ዙሪያ፡የዐይነ፡ርግብ፡መስኮቶች፡ነበሩ።መቅደሱም፡በመድረኩ፡አንጻር፡ከመሬት፡ዠምሮ፡ እስከ፡መስኮቶቹ፡ድረስ፡በዕንጨት፡ተለብጦ፡ነበር፤መስኮቶቹም፡የዐይነ፡ርግብ፡ነበሩ፤

17በደጁም፡ላይ፡እስከ፡ውስጠኛው፡ክፍል፡ድረስ፥በውጭም፡ግንቡ፡ዅሉ፡ውስጡም፡ውጭውም፡ተለብጦ፡ ነበር።

18ኪሩቤልና፡የዘንባባው፡ዛፎች፡ተቀርጸውበት፡ነበር፤የዘንባባውም፡ዛፍ፡ከኪሩብና፡ከኪሩብ፡መካከል፡ ነበረ፤ለያንዳንዱም፡ኪሩብ፡ኹለት፡ፊት፡ነበረው።

19ባንድ፡ወገን፡ወዳለው፡የዘንባባ፡ዛፍ፡የሰው፡ፊት፡ይመለከት፡ነበር፥በሌላውም፡ወገን፡ወዳለው፡ የዘንባባ፡ዛፍ፡የአንበሳ፡ፊት፡ይመለከት፡ነበር፤በቤቱ፡ዅሉ፡ዙሪያ፡እንደዚህ፡ተደርጎ፡ነበር።

20ከመሬት፡አንሥቶ፡እስከደጁ፡ራስ፡ድረስ፡ኪሩቤልና፡የዘንባባ፡ዛፎች፡ተቀርጸው፡ነበር።የመቅደሱ፡ግንብ፡ እንደዚህ፡ነበረ።

21የመቅደሱ፡መቃኖችም፡አራት፡ማእዘን፡ነበሩ፥የመቅደሱ፡ፊትም፡መልኩ፡እንደ፡ሌላው፡መልክ፡ነበረ።

22መሠዊያውም፡ቁመቱ፡ሦስት፡ክንድ፡ርዝመቱ፡ኹለት፡ክንድ፡ወርዱም፡ኹለት፡ክንድ፡ኾኖ፡ከዕንጨት፡ ተሠርቶ፡ነበር፤ማእዘኖቹም፡እግሩም፡አገዳዎቹም፡ከዕንጨት፡ተሠርተው፡ነበር፤ርሱም፦በእግዚአብሔር፡ፊት፡ ያለችው፡ገበታ፡ይህች፡ናት፡አለኝ።

23ለመቅደሱና፡ለተቀደሰው፡ስፍራ፡ኹለት፡መዝጊያዎች፡ነበሯቸው።

24ለያንዳንዱ፡መዝጊያም፡ኹለት፡ተዘዋዋሪ፡ሳንቃዎች፡ነበሩት፤ለአንዱ፡መዝጊያ፡ኹለት፡ለሌላውም፡ መዝጊያ፡ኹለት፡ሳንቃዎች፡ነበሩት።

25በግንቡም፡ላይ፡በተቀረጹት፡ዐይነት፡በእነዚህ፡በመቅደሱ፡መዝጊያዎች፡ላይ፡ኪሩቤልና፡የዘንባባ፡ዛፎች፡ ተቀርጸው፡ነበር፤በስተውጭም፡ባለው፡በደጀ፡ሰላሙ፡ፊት፡የዕንጨት፡መድረክ፡ነበረ።

26በደጀ፡ሰላሙም፡በኹለቱ፡ወገን፡በዚህና፡በዚያ፡የዐይነ፡ርግብ፡መስኮቶችና፡የተቀረጹ፡የዘንባባ፡ዛፎች፡ ነበሩበት፤የመቅደሱም፡ጓዳዎችና፡የዕንጨቱ፡መድረክ፡እንዲሁ፡ነበሩ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source