Skip to content
← Ezekiel

Chapter 42 · Amharic

Ezekiel

1በውጭም፡አደባባይ፡በሰሜኑ፡መንገድ፡አወጣኝ፥በልዩውም፡ስፍራ፡አንጻርና፡በሰሜን፡በኩል፡ባለው፡ግቢ፡ ፊት፡ለፊት፡ወዳለው፡ዕቃ፡ቤት፡አገባኝ።

2መቶ፡ክንድ፡በኾነው፡ርዝመት፡ፊት፡በሰሜን፡በኩል፡መዝጊያ፡ነበረ፡ወርዱም፡ዐምሳ፡ክንድ፡ነበረ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

3በውስጠኛውም፡አደባባይ፡በኻያው፡ክንድ፡አንጻር፡በውጭውም፡አደባባይ፡በወለሉ፡አንጻር፡በሦስት፡ደርብ፡ በትይዩ፡የተሠራ፡መተላለፊያ፡ነበረ።

4በዕቃ፡ቤቶቹም፡ፊት፡በስተውስጥ፡ወርዱ፡ዐሥር፡ክንድ፡ርዝመቱ፡መቶ፡ክንድ፡የኾነ፡መንገድ፡ ነበረ፤መዝጊያዎቻቸውም፡ወደ፡ሰሜን፡ይመለከቱ፡ነበር።

5መተላለፊያውም፡አሳጥሯቸዋልና፥ላይኛዎቹ፡ዕቃ፡ቤቶች፡ከመካከለኛዎቹና፡ከታችኛዎቹ፡ይልቅ፡ዐጫጪር፡ ነበሩ።

6በሦስትም፡ደርብ፡ተሠርተው፡ነበርና፥በአደባባዩም፡እንዳሉት፡አዕማድ፥አዕማድ፡አልነበሩላቸውምና፡ ስለዚህ፡ላይኛዎቹ፡ከመካከለኛዎቹና፡ከታችኛዎቹ፡ይልቅ፡ጠባብ፡ነበሩ።

7በውጭ፡በዕቃ፡ቤቶቹ፡አጠገብ፡ያለው፥ወደ፡ውጭው፡አደባባይ፡የሚመለከተው፡ቅጥር፥በዕቃ፡ቤቶች፡ ትይዩ፡የኾነ፥ርዝመቱ፡ዐምሳ፡ክንድ፡ነበረ።

8በመቅደሱ፡ፊት፡የነበሩት፡ዕቃ፡ቤቶች፡ርዝመታቸው፡መቶ፡ክንድ፡ሲኾን፡በውጭው፡አደባባይ፡በኩል፡ የነበሩት፡ዕቃ፡ቤቶች፡ርዝመታቸው፡ዐምሳ፡ክንድ፡ነበረና።

9ከነዚህም፡ዕቃ፡ቤቶች፡በታች፡በስተምሥራቅ፡በኩል፥ሰው፡ከውጭው፡አደባባይ፡የሚገባበት፡መግቢያ፡ ነበረ።ይህም፡በቅጥሩ፡ራስ፡አጠገብ፡ነበረ።

10በደቡብም፡በኩል፡በልዩው፡ስፍራና፡በግቢው፡አንጻር፡ዕቃ፡ቤቶች፡ነበሩ።

11በስተፊታቸውም፡የነበረ፡መንገድ፡በሰሜን፡በኩል፡እንደ፡ነበረው፡እንደ፡ዕቃ፡ቤቶቹ፡መንገድ፡ምስያ፡ ነበረ።ርዝመታቸውም፡ወርዳቸውም፡መውጫቸውም፡ሥርዐታቸውም፡መዝጊያዎቻቸውም፡በዚያው፡ልክ፡ነበረ።

12በደቡብም፡በኩል፡ካሉት፡ዕቃ፡ቤቶች፡በታች፡በምሥራቅ፡በኩል፡በቅጥሩ፡ራስ፡አጠገብ፡መግቢያ፡ነበረ።

13እንዲህም፡አለኝ፦በልዩ፡ስፍራ፡አንጻር፡በሰሜንና፡በደቡብ፡በኩል፡ያሉ፡ዕቃ፡ቤቶች፥እነርሱ፡ወደ፡ እግዚአብሔር፡የሚቀርቡ፡ካህናት፡ከዅሉ፡ይልቅ፡የተቀደሰውን፡ምግብ፡የሚበሉባቸው፡ቤቶች፡ ናቸው።ስፍራው፡ቅዱስ፡ነውና፥በዚያ፡የተቀደሰውን፡ነገር፡የእኽሉን፡ቍርባን፡የኀጢአቱንና፡የበደሉን፡ መሥዋዕት፡ያኖራሉ።

14ካህናቱም፡በገቡ፡ጊዜ፡ከመቅደሱ፡በውጭው፡አደባባይ፡አይወጡም፤የሚያገለግሉበትን፡ልብሳቸውን፡ግን፡ ቅዱስ፡ነውና፥በዚያ፡ያኖሩታል፥ሌላም፡ልብስ፡ለብሰው፡ወደ፡ሕዝብ፡ይወጣሉ።

15ውስጠኛውንም፡ቤት፡ለክቶ፡በፈጸመ፡ጊዜ፡ወደ፡ምሥራቅ፡በሚመለከት፡በር፡መንገድ፡አወጣኝ፡ ርሱንም፡በዙሪያው፡ለካው።

16የምሥራቁን፡ወገን፡በመለኪያ፡ዘንግ፡ዐምስት፡መቶ፡ክንድ፡አድርጎ፡ለካ።

17ዞረም፥የሰሜኑንም፡ወገን፡በመለኪያ፡ዘንግ፡ዐምስት፡መቶ፡ክንድ፡አድርጎ፡ለካ።

18ዞረም፥የደቡቡንም፡ወገን፡በመለኪያ፡ዘንግ፡ዐምስት፡መቶ፡ክንድ፡አድርጎ፡ለካ።

19ዞረም፥የምዕራቡንም፡ወገን፡በመለኪያ፡ዘንግ፡ዐምስት፡መቶ፡ክንድ፡አድርጎ፡ለካ።

20በአራቱ፡ወገን፡ለካው።የተቀደሰውንና፡ያልተቀደሰውን፡ይለይ፡ዘንድ፥ርዝመቱ፡ዐምስት፡መቶ፡ክንድ፡ ወርዱም፡ዐምስት፡መቶ፡ክንድ፡የኾነ፡ቅጥር፡በዙሪያው፡ነበረ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source