Skip to content
← Ezekiel

Chapter 43 · Amharic

Ezekiel

1ወደ፡ምሥራቅም፡ወደሚመለከተው፡በር፡አመጣኝ።

2እንሆም፥የእስራኤል፡አምላክ፡ክብር፡ከምሥራቅ፡መንገድ፡መጣ፤ድምፁም፡እንደ፡ብዙ፡ውሃዎች፡ይተም፟፡ ነበር፥ከክብሩም፡የተነሣ፡ምድር፡ታበራ፡ነበር። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

3ያየኹትም፡ራእይ፡ከተማዪቱን፡ለማጥፋት፡በመጣኹ፡ጊዜ፡እንዳየኹት፡ራእይ፡ነበረ፤ራእዩም፡በኮበር፡ ወንዝ፡እንዳየኹት፡ራእይ፡ነበረ፤እኔም፡በግንባሬ፡ተደፋኹ።

4የእግዚአብሔርም፡ክብር፡ወደ፡ምሥራቅ፡በሚመለከት፡በር፡ወደ፡መቅደሱ፡ገባ።

5መንፈሱም፡አነሣኝ፡ወደ፡ውስጠኛውም፡አደባባይ፡አገባኝ፤እንሆም፥የእግዚአብሔር፡ክብር፡መቅደሱን፡ ሞልቶት፡ነበር።

6በመቅደሱም፡ኾኖ፡የሚናገረኝን፡ሰማኹ፥በአጠገቤም፡ሰው፡ቆሞ፡ነበር።

7እንዲህም፡አለኝ፦የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥በእስራኤል፡ልጆች፡መካከል፡ለዘለዓለም፡የምቀመጥበት፡የዙፋኔ፡ ስፍራና፡የእግሬ፡ጫማ፡መረገጫ፡ይህ፡ነው።ዳግመኛም፡የእስራኤል፡ቤትና፡ነገሥታታቸው፡ በግልሙትናቸውና፡በከፍታዎቻቸው፡ባለው፡በነገሥታታቸው፡ሬሳ፡ቅዱስ፡ስሜን፡አያረክሱም፤

8መድረካቸውን፡በመድረኬ፡አጠገብ፥መቃናቸውንም፡በመቃኔ፡አጠገብ፡አድርገዋልና።በእኔና፡በእነርሱም፡ መካከል፡ግንብ፡ብቻ፡ነበረ፤በሠሩትም፡ርኵሰት፡ቅዱስ፡ስሜን፡አረከሱ፤ስለዚህ፥በቍጣዬ፡አጠፋዃቸው።

9አኹንም፡ግልሙትናቸውንና፡የነገሥታታቸውን፡ሬሳ፡ከእኔ፡ዘንድ፡ያርቁ፥እኔም፡ለዘለዓለም፡በመካከላቸው፡ ዐድራለኹ።

10አንተም፡የሰው፡ልጅ፥ከኀጢአታቸው፡የተነሣ፡ያፍሩ፡ዘንድ፥ለእስራኤል፡ወገን፡ይህን፡ቤት፡ አሳያቸው፤አምሳያውንም፡ይለኩ።

11ከሠሩትም፡ሥራ፡ዅሉ፡የተነሣ፡ቢያፍሩ፥የቤቱን፡መልክና፡ምሳሌውን፡መውጫውንም፡መግቢያውንም፡ ሥርዐቱንም፡ሕጉንም፡ዅሉ፡አስታውቃቸው፤ሥርዐቱንና፡ሕጉን፡ዅሉ፡ይጠብቁ፡ዘንድ፥ያደርጉትም፡ ዘንድ፥በፊታቸው፡ጻፈው።

12የቤቱ፡ሕግ፡ይህ፡ነው፤በተራራው፡ራስ፡ላይ፡ዳርቻው፡ዅሉ፡በዙሪያው፡ከዅሉ፡ይልቅ፡የተቀደስ፡ ይኾናል።እንሆ፥የቤቱ፡ሕግ፡ይህ፡ነው።

13የመሠዊያውም፡ልክ፡በክንድ፡ይህ፡ነው፥ክንዱም፡ክንድ፡ተጋት፡ነው።የመሠረቱም፡ቁመቱ፡አንድ፡ ክንድ፡ወርዱም፡አንድ፡ክንድ፡ነው፥አንድ፡ስንዝርም፡ክፈፍ፡ዳር፡ዳሩን፡በዙሪያው፡አለ፤የመሠዊያው፡ መሠረት፡እንዲሁ፡ነው።

14በመሬቱም፡ላይ፡ካለው፡መሠረት፡ዠምሮ፡እስከ፡ታችኛው፡ዕርከን፡ድረስ፡ኹለት፡ክንድ፡ወርዱም፡ አንድ፡ክንድ፡ነው፤ከትንሹም፡ዕርከን፡ዠምሮ፡እስከ፡ትልቁ፡ዕርከን፡ድረስ፡አራት፡ክንድ፡ወርዱም፡አንድ፡ ክንድ፡ነው።

15ምድጃውም፡አራት፡ክንድ፡ነው፤በምድጃውም፡ላይ፡አንድ፡ክንድ፡ወደ፡ላይ፡ከፍ፡የሚሉ፡አራት፡ ቀንዶች፡አሉበት።

16የምድጃውም፡ርዝመት፡ዐሥራ፡ኹለት፡ክንድ፡ወርዱም፡ዐሥራ፡ኹለት፡ክንድ፡ነው፥አራቱም፡ማእዘን፡ ትክክል፡ነው።

17የዕርከኑም፡ርዝመት፡ዐሥራ፡አራት፡ክንድ፡ወርዱም፡ዐሥራ፡አራት፡ክንድ፡ነው፥አራቱም፡ማእዘን፡ ትክክል፡ነው፤በዙሪያውም፡ያለው፡ክፈፍ፡እኩል፡ክንድ፡ነው፥መሠረቱም፡በዙሪያው፡አንድ፡ክንድ፡ ነው፤ደረጃዎቹም፡ወደ፡ምሥራቅ፡ይመለከታሉ።

18እንዲህም፡አለኝ፦የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦የሚቃጠለውን፡መሥዋዕት፡ ያቀርቡበት፡ዘንድ፥ደሙንም፡ይረጩበት፡ዘንድ፥በሚሠሩበት፡ቀን፡የመሠዊያው፡ሕግ፡ይህ፡ነው።

19ያገለግሉኝ፡ዘንድ፥ወደ፡እኔ፡ለሚቀርቡ፡ከሳዶቅ፡ዘር፡ለሚኾኑ፡ለሌዋውያኑ፡ካህናት፡ለኀጢአት፡ መሥዋዕት፡የሚኾነውን፡ወይፈን፡ትሰጣቸዋለኽ፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።

20ከደሙም፡ትወስዳለኽ፥በአራቱ፡ቀንዶቹም፡በዕርከኑም፡በአራቱ፡ማእዘን፡ላይ፡በዙሪያውም፡ባለው፡ክፈፍ፡ ላይ፡ትረጨዋለኽ፤እንዲሁ፡ታነጻዋለኽ፡ታስተሰርይለትማለኽ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

21ለኀጢአትም፡መሥዋዕት፡የሚኾነውን፡ወይፈን፡ትወስዳለኽ፥በመቅደሱም፡ውጭ፡በቤቱ፡በታዘዘው፡ስፍራ፡ ይቃጠላል።

22በኹለተኛውም፡ቀን፡ለኀጢአት፡መሥዋዕት፡የሚኾነውን፡ነውር፡የሌለበትን፡አውራ፡ፍየል፡ ታቀርባለኽ፤በወይፈኑም፡እንዳነጹት፡እንዲሁ፡መሠዊያውን፡ያነጹበታል።

23ማንጻቱንም፡ከፈጸምኽ፡በዃላ፥ነውር፡የሌለበትን፡ወይፈን፡ከመንጋውም፡የወጣውን፡ነውር፡የሌለበትን፡ አውራ፡በግ፡ታቀርባለኽ።

24በእግዚአብሔርም፡ፊት፡ታቀርባቸዋለኽ፥ካህናቱም፡ጨው፡ይጨምሩባቸዋል፥የሚቃጠለውንም፡መሥዋዕት፡ አድርገው፡ለእግዚአብሔር፡ያቀርቧቸዋል።

25ሰባት፡ቀንም፡በየዕለቱ፡ለኀጢአት፡መሥዋዕት፡የሚኾነውን፡አውራ፡ፍየልን፡ታቀርባለኽ፥ነውርም፡ የሌለባቸውን፡አንድ፡ወይፈን፡ከመንጋውም፡የወጣውን፡አንድ፡አውራ፡በግ፡ያቀርባሉ።

26ሰባት፡ቀን፡ለመሠዊያው፡ያስተሰርያሉ፡ያነጹትማል፥እንዲሁም፡ይቀድሱታል።

27ቀኖቹንም፡በፈጸሙ፡ጊዜ፡በስምንተኛው፡ቀን፡ከዚያም፡በዃላ፡ካህናቱ፡የሚቃጠለውን፡መሥዋዕታችኹን፡ የደኅንነትንም፡መሥዋዕታችኹን፡በመሠዊያው፡ላይ፡ያደርጋሉ፤እኔም፡እቀበላችዃለኹ፥ይላል፡ጌታ፡ እግዚአብሔር።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source