Skip to content
← Ezekiel

Chapter 44 · Amharic

Ezekiel

1ወደ፡ምሥራቅም፡ወደሚመለከተው፡በስተውጭ፡ወዳለው፡ወደመቅደሱ፡በር፡አመጣኝ፤ተዘግቶም፡ነበር።

2እግዚአብሔርም፦ይህ፡በር፡ተዘግቶ፡ይኖራል፡እንጂ፡አይከፈትም፥ሰውም፡አይገባበትም፤የእስራኤል፡ አምላክ፡እግዚአብሔር፡ገብቶበታልና፥ተዘግቶ፡ይኖራል።

3አለቃው፡ግን፥ርሱ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡እንጀራ፡ይበላ፡ዘንድ፥ይቀመጥበታል፤በበሩ፡ደጀ፡ሰላም፡ መንገድ፡ይገባል፥በዚያም፡መንገድ፡ይወጣል።

4በሰሜኑም፡በር፡መንገድ፡በቤቱ፡ፊት፡አመጣኝ፤እኔም፡አየኹ፥እንሆም፥የእግዚአብሔር፡ክብር፡ የእግዚአብሔርን፡ቤት፡ሞልቶት፡ነበር፤እኔም፡በግንባሬ፡ተደፋኹ።

5እግዚአብሔርም፡እንዲህ፡አለኝ፦የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ልብ፡አድርግ፡ስለእግዚአብሔርም፡ቤት፡ሥርዐትና፡ ሕግ፡ዅሉ፡የምናገርኽን፡ዅሉ፡በዐይንኽ፡ተመልከት፥በዦሮኽም፡ስማ፤የቤቱንም፡መግቢያ፡የመቅደሱንም፡ መውጫ፡ዅሉ፡ልብ፡አድርግ።

6ለዐመፀኛው፡ለእስራኤል፡ቤት፡እንዲህ፡በል፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እናንተ፡የእስራኤል፡ ቤት፡ሆይ፥

7እንጀራዬን፥ስብንና፡ደምን፥በምታቀርቡበት፡ጊዜ፡በመቅደሴ፡ውስጥ፡ይኾኑ፡ዘንድ፥ቤቴንም፡ያረክሱ፡ ዘንድ፥በልባቸውና፡በሥጋቸው፡ያልተገረዙትን፡እንግዳዎችን፡ሰዎች፡አግብታችዃልና፥እነርሱም፡በርኵሰታችኹ፡ ዅሉ፡ላይ፡ይጨመሩ፡ዘንድ፥ቃል፡ኪዳኔን፡አፍርሰዋልና፥ርኵሰታችኹ፡ዅሉ፡ይብቃችኹ።

8በመቅደሴ፡ውስጥ፡ለራሳችኹ፡ሥርዐቴን፡ጠባቂዎች፡አደረጋችኹ፡እንጂ፡የተቀደሰውን፡ነገሬን፡ሥርዐት፡ አልጠበቃችኹም።

9ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦በእስራኤል፡ልጆች፡መካከል፡ካሉት፡ዅሉ፡በልቡና፡በሥጋው፡ ያልተገረዘ፡እንግዳ፡ዅሉ፡ወደ፡መቅደሴ፡አይግባ።

10ከእኔ፡ዘንድ፡የራቁ፥እስራኤልም፡በሳቱ፡ጊዜ፡ጣዖታቸውን፡ተከትለው፡ከእኔ፡ዘንድ፡የሳቱ፡ሌዋውያን፡ ኀጢአታቸውን፡ይሸከማሉ።

11ነገር፡ግን፥በመቅደሴ፡ውስጥ፡አገልጋዮች፡ይኾናሉ፥በቤቱም፡በሮች፡በረኛዎች፡ይኾናሉ፡በቤቱም፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ውስጥ፡ያገለግላሉ፤ለሕዝቡም፡የሚቃጠለውን፡መሥዋዕትና፡ሌላ፡መሥዋዕቱን፡ያርዳሉ፥ያገለግሏቸውም፡ ዘንድ፥በፊታቸው፡ይቆማሉ።

12በጣዖቶቻቸውም፡ፊት፡አገልግለዋቸው፡ነበሩና፥ለእስራኤልም፡ቤት፡የኀጢአት፡ዕንቅፋት፡ ኾነዋልና፥ስለዚህ፡እጄን፡በላያቸው፡አንሥቻለኹ፥ኀጢአታቸውንም፡ይሸከማሉ፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።

13ካህናትም፡ይኾኑኝ፡ዘንድ፥ወደ፡እኔ፡አይቀርቡም፥ወደተቀደሰውም፡ነገሬና፡ወደቅድስተ፡ቅዱሳን፡ነገር፡ አይቀርቡም፤ዕፍረታቸውንና፡የሠሩትንም፡ርኵሰታቸውን፡ይሸከማሉ።

14ነገር፡ግን፥ለአገልግሎቱ፡ዅሉና፡በርሱ፡ውስጥ፡ለሚደረገው፡ዅሉ፡የቤቱን፡ሥርዐት፡ጠባቂዎች፡ አደርጋቸዋለኹ።

15ነገር፡ግን፥የእስራኤል፡ልጆች፡ከእኔ፡ዘንድ፡በሳቱ፡ጊዜ፡የመቅደሴን፡ሥርዐት፡የጠበቁ፡የሳዶቅ፡ልጆች፡ ሌዋውያን፡ካህናት፡ያገለግሉኝ፡ዘንድ፥ወደ፡እኔ፡ይቀርባሉ፤ስቡንና፡ደሙንም፡ወደ፡እኔ፡ያቀርቡ፡ ዘንድ፥በፊቴ፡ይቆማሉ፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።

16ወደ፡መቅደሴም፡ይገባሉ፡ያገለግሉኝም፡ዘንድ፥ወደ፡ገበታዬ፡ይቀርባሉ፡ሥርዐቴንም፡ይጠብቃሉ።

17ወደ፡ውስጠኛውም፡አደባባይ፡በር፡በገቡ፡ጊዜ፡የተልባ፡እግር፡ልብስ፡ይልበሱ፤በውስጠኛውም፡አደባባይ፡ በርና፡በቤቱ፡ውስጥ፡ባገለገሉ፡ጊዜ፡ከበግ፡ጠጕር፡አንዳች፡ነገር፡በላያቸው፡አይኹን።

18በራሳቸው፡ላይ፡የተልባ፡እግር፡መጠምጠሚያ፡ይኹን፥በወገባቸውም፡ላይ፡የተልባ፡እግር፡ሱሪ፡ ይኹን፤የሚያወዛም፡ነገር፡አይታጠቁ።

19ወደ፡ውጭውም፡አደባባይ፡ወደ፡ሕዝብ፡በወጡ፡ጊዜ፡ያገለገሉበትን፡ልብሳቸውን፡ያውልቁ፡ በተቀደሰውም፡ዕቃ፡ቤት፡ውስጥ፡ያኑሩት፥ሕዝቡንም፡በልብሳቸው፡እንዳይቀድሱ፡ሌላውን፡ልብስ፡ይልበሱ።

20ራሳቸውንም፡አይላጩ፡የራሳቸውንም፡ጠጕር፡ይከርከሙ፡እንጂ፡ጠጕራቸውን፡አያሳድጉ።

21ካህናቱም፡ዅሉ፡በውስጠኛው፡አደባባይ፡ሲገቡ፡የወይን፡ጠጅ፡አይጠጡ።

22መበለቲቱንና፡የተፈታችዪቱን፡አያግቡ፤ከእስራኤል፡ቤት፡ዘር፡ግን፡ድንግሊቱን፡ወይም፡የካህን፡ሚስት፡ የነበረችዪቱን፡መበለት፡ያግቡ።

23በተቀደሰውና፡ባልተቀደሰው፡መካከል፡ይለዩ፡ዘንድ፥ሕዝቤን፡ያስተምሩ፥ንጹሕና፡ንጹሕ፡ባልኾነው፡ መካከል፡ይለዩ፡ዘንድ፥ያሳይዋቸው።

24ክርክርም፡በኾነ፡ጊዜ፡ለመፍረድ፡ይቁሙ፤እንደ፡ፍርዴ፡ይፍረዱ፤በበዓላቴ፡ዅሉ፡ሕጌንና፡ሥርዐቴን፡ ይጠብቁ፥ሰንበታቴንም፡ይቀድሱ።

25እንዳይረክሱም፡ወደሞተ፡ሰው፡አይግቡ፤ነገር፡ግን፥ለአባት፡ወይም፡ለእናት፡ወይም፡ለወንድ፡ልጅ፡ ወይም፡ለሴት፡ልጅ፡ወይም፡ለወንድም፡ወይም፡ላልተዳረች፡እኅት፡ይርከሱ።

26ከነጻም፡በዃላ፡ሰባት፡ቀን፡ይቈጠርለት።

27በመቅደስም፡ውስጥ፡ያገለግል፡ዘንድ፥ወደ፡ውስጠኛው፡አደባባይ፡ወደ፡መቅደሱ፡በሚገባበት፡ ቀን፥የኀጢአትን፡መሥዋዕት፡ያቅርብ፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።

28ርስት፡ይኾንላቸዋል፤እኔ፡ርስታቸው፡ነኝ፤በእስራኤልም፡ዘንድ፥ግዛት፡አትስጧቸው፤እኔ፡ግዛታቸው፡ ነኝ።

29የእኽሉን፡ቍርባንና፡የኀጢአትን፡መሥዋዕት፡የበደልንም፡መሥዋዕት፡ይበላሉ፤በእስራኤልም፡ዘንድ፡ ዕርም፡የኾነው፡ነገር፡ዅሉ፡ለእነርሱ፡ይኾናል።

30የበኵራቱ፡ዅሉ፡መዠመሪያ፡ከየዐይነቱ፡ከቍርባናችኹም፡ዅሉ፡የማንሣት፡ቍርባን፡ዅሉ፡ለካህናት፡ ይኾናል፤በቤታችኹም፡ውስጥ፡በረከት፡ያድር፡ዘንድ፥የዱቄታችኹን፡በኵራት፡ለካህናቱ፡ትሰጣላችኹ።

31የበከተውንና፡የተሰበረውን፥ወፍ፡ወይም፡እንስሳ፡ቢኾን፥ካህናት፡አይብሉት። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source