Skip to content
← Ezekiel

Chapter 7 · Amharic

Ezekiel

1የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦

2አንተ፡የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ጌታ፡እግዚአብሔር፡ለእስራኤል፡ምድር፡እንዲህ፡ይላል፦ፍጻሜ፥በምድሪቱ፡ በአራቱ፡ማእዘን፡ላይ፡ፍጻሜ፡ደርሷል።

3አኹን፡ፍጻሜ፡ባንቺ፡ላይ፡ነው፥ቍጣዬንም፡እሰድ፟ብሻለኹ፥እንደ፡መንገድሽም፡መጠን፡ እፈርድብሻለኹ፥ጕስቍልናሽንም፡ዅሉ፡አመጣብሻለኹ።

4ዐይኔም፡አይራራልሽም፡እኔም፡አላዝንም፤መንገድሽንም፡አመጣብሻለኹ፡ርኵሰትሽም፡በመካከልሽ፡ ይኾናል፥እኔም፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ታውቃላችኹ።

5ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ክፉ፡ነገር፥አንድ፡ክፉ፡ነገር፥እንሆ፥ይመጣል።

6ፍጻሜ፡መጥቷል፥ፍጻሜ፡መጥቷል፥ነቅቶብሻል፤እንሆ፥ደርሷል።

7በምድር፡የምትቀመጥ፡ሆይ፥ተራኽ፡ደርሷል፥ጊዜ፡መጥቷል፥ቀን፡ቀርቧል፤የሽብር፡ቀን፡ነው፡እንጂ፡ በተራራ፡ላይ፡ያለ፡እልልታ፡አይደለም።

8አኹን፡በቅርብ፡መዓቴን፡አፈስ፟ብሻለኹ፥ቍጣዬንም፡እፈጽምብሻለኹ፥እንደ፡መንገድሽም፡መጠን፡ እፈርድብሻለኹ፥ጕስቍልናሽንም፡ዅሉ፡አመጣብሻለኹ።

9ዐይኔም፡አይራራም፡እኔም፡አላዝንም፤እንደ፡መንገድሽም፡መጠን፡አመጣብሻለኹ፥ርኵሰትሽም፡ በመካከልሽ፡ይኾናል፥እኔም፡እግዚአብሔር፡የምቀሥፍ፡እንደ፡ኾንኹ፡ታውቃላችኹ።

10እንሆ፥ቀኑ፥እንሆ፥መጥቷል፤ተራኽ፡ወጥቷል፤በትር፡አብቧል፥ትዕቢትም፡አጀፍጅፏል።

11ግፍ፡ወደክፋት፡በትር፡ተነሥቷል፤ከነርሱና፡ከብዛታቸው፡ከሀብታቸውም፡ምንም፡ አይቀርም፥የሚያለቅስላቸውም፡የለም።

12ጊዜው፡መጥቷል፥ቀኑ፡ቀርቧል፤መዓት፡በብዙዎች፡ዅሉ፡ላይ፡ነውና፥የሚገዛ፡ደስ፡አይበለው፡ የሚሸጥም፡አያልቅስ።

13የሚሸጥ፡ወደሸጠው፡ነገር፡አይመለስም፥ሰውም፡በነፍሱ፡ኀጢአት፡አይጸናም።

14መለከቱን፡ነፍተዋል፡ዅሉንም፡አዘጋጅተዋል፤ነገር፡ግን፥መዓቴ፡በብዙዎች፡ዅሉ፡ላይ፡ነውና፥ወደ፡ ሰልፍ፡የሚኼድ፡የለም።

15ሰይፍ፡በውጭ፡ቸነፈርና፡ራብ፡በውስጥ፡አለ፤በሜዳ፡ያለው፡በሰይፍ፡ይሞታል፥በከተማም፡ያለውን፡ ቸነፈርና፡ራብ፡ይፈጁታል።

16ከነርሱም፡የሚሸሹ፡ይድናሉ፡በተራራም፡ላይ፡ይኾናሉ፤እኔም፡በኀጢአታቸው፡ዅሉን፡እገድላለኹ።

17እጅ፡ዅሉ፡ትደክማለች፡ጕልበትም፡ዅሉ፡እንደ፡ውሃ፡ትቀልጣለች።

18ማቅም፡ይለብሳሉ፥ድንጋጤም፡ይሸፍናቸዋል፤በፊትም፡ዅሉ፡ላይ፡ዕፍረት፡ይኾናል፥ራሳቸውንም፡ዅሉ፡ ይነጩታል።

19ብራቸውን፡በጐዳናዎቹ፡ላይ፡ይጥላሉ፡ወርቃቸውም፡እንደ፡ጕድፍ፡ይኾናል፤በእግዚአብሔር፡መዓት፡ ቀን፡ብራቸውና፡ወርቃቸው፡ያድናቸው፡ዘንድ፡አይችልም።ርሱ፡የኀጢአታቸው፡ዕንቅፋት፡ ኾኗልና፥ሰውነታቸውን፡አያጠግቡም፥ሆዳቸውንም፡አይሞሉም።

20የክብሩንም፡ጌጥ፡ወደ፡ትዕቢት፡ለወጡ፥የርኩስነታቸውንም፡ምስሎች፡አደረጉባት፤ስለዚህ፥እኔ፡ በእነርሱ፡ዘንድ፡ርኩስ፡አድርጌያታለኹ።

21በባዕድም፡እጅ፡ለንጥቂያ፥በምድር፡ኀጢአተኛዎችም፡እጅ፡ለብዝበዛ፡አሳልፌ፡እሰጣታለኹ፤እነርሱም፡ ያረክሷታል። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

22ፊቴን፡ከነርሱ፡ዘንድ፡እመልሳለኹ፥ምስጢሬንም፡ያረክሳሉ፤ወንበዴዎችም፡ይገቡባታል፡ያረክሷትማል።

23ምድር፡ደም፡ባመጣው፡በደል፥ከተማም፡በግፍ፡ተሞልታለችና፡ሰንሰለት፡ሥራ።

24ከአሕዛብ፡ዘንድ፡ከዅሉ፡የሚከፉትን፡አመጣለኹ፡ቤቶቻቸውንም፡ይወርሳሉ፤የኀያላንንም፡ትዕቢት፡ አጠፋለኹ፥መቅደሶቻቸውም፡ይረክሳሉ።

25ጥፋት፡መጥቷል፤ሰላምም፡ይሻሉ፡ርሱም፡አይገኝም።

26ድንጋጤ፡በድንጋጤ፡ላይ፡ይመጣል፥ወሬም፡ወሬውን፡ይከተላል፥ከነቢዩም፡ዘንድ፡ራዕይን፡ ይሻሉ፤ከካህኑም፡ዘንድ፡ትምህርት፥ከሽማግሌዎችም፡ዘንድ፡ምክር፡ይጠፋል።

27ንጉሡም፡ያለቅሳል፥አለቃም፡ውርደትን፡ይለብሳል፥የምድርም፡ሕዝብ፡እጅ፡ትንቀጠቀጣለች፤እንደ፡ መንገዳቸውም፡መጠን፡አደርግባቸዋለኹ፥በፍርዳቸውም፡መጠን፡እፈርድባቸዋለኹ፤እኔም፡እግዚአብሔር፡ እንደ፡ኾንኹ፡ያውቃሉ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source