Skip to content
← Hosea

Chapter 12 · Amharic

Hosea

1ኤፍሬም፡በሐሰት፥የእስራኤልም፡ቤት፡በተንኰል፡ከበበኝ፤ይሁዳም፡ከታመነው፡ቅዱሱ፡ከእግዚአብሔር፡ ጋራ፡አይጸናም።

2ኤፍሬም፡ነፋስን፡ይበላል፥የምሥራቅንም፡ነፋስ፡ይከተላል፤ዅልጊዜም፡ሐሰትንና፡ተንኰልን፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ያበዛል፤ከአሶር፡ጋራ፡ቃል፡ኪዳን፡ያደርጋሉ፥ወደ፡ግብጽም፡ዘይት፡ይወስዳሉ።

3እግዚአብሔርም፡ደግሞ፡ከይሁዳ፡ጋራ፡ክርክር፡አለው፥ያዕቆብንም፡እንደ፡መንገዱ፡ይቀጣል፤እንደ፡ ሥራውም፡ይመልስለታል።

4በማሕፀን፡ውስጥ፡ወንድሙን፡በተረከዙ፡ያዘው፥በጕልማሳነቱም፡ጊዜ፡ከአምላክ፡ጋራ፡ታገለ፤

5ከመልአኩም፡ጋራ፡ታግሎ፡አሸነፈ፤አልቅሶም፡ለመነው።በቤቴልም፡አገኘው፥በዚያም፡ከእኛ፡ጋራ፡ ተነጋገረ።

6ርሱም፡የሰራዊት፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡ነው፤የመታሰቢያው፡ስም፡እግዚአብሔር፡ነው።

7ስለዚህ፥ወደ፡አምላክኽ፡ተመለስ፤ምሕረትንና፡ፍርድን፡ጠብቅ፥ዘወትርም፡በአምላክኽ፡ታመን።

8ከከነዓን፡ወገን፡ነው፤በእጁ፡የተንኰል፡ሚዛን፡አለ፥ሽንገላንም፡ይወዳል።

9ኤፍሬምም፦ባለጠጋ፡ኾኛለኹ፥ሀብትንም፡አግኝቻለኹ፥በድካሜም፡ዅሉ፡ኀጢአት፡የሚኾን፡በደል፡ አይገኝብኝም፡አለ።

10እኔም፡ከግብጽ፡ዠምሬ፡አምላክኽ፡እግዚአብሔር፡ነኝ፤እንደ፡ዓመት፡በዓል፡ቀን፡እንደ፡ገና፡በድንኳን፡ እንድትኖር፡አደርግኻለኹ።

11ለነቢያትም፡ተናግሬያለኹ፥ራእይንም፡አብዝቻለኹ፤በነቢያትም፡እጅ፡ምሳሌዎችን፡አውጥቻለኹ።

12ኀጢአት፡በገለዓድ፡አለ፤ፈጽመው፡ከንቱ፡ናቸው፤ወይፈኖች፡በገልገላ፡ይሠዋሉ፥መሠዊያዎቻቸውም፡ በዕርሻ፡ትልም፡ላይ፡የድንጋይ፡ክምር፡ይኾናሉ።

13ያዕቆብ፡ወደሶርያ፡አገር፡ሸሸ፥እስራኤልም፡ስለ፡ሚስት፡አገለገለ፥ስለ፡ሚስትም፡ጠባቂ፡ነበረ።

14እግዚአብሔርም፡በነቢይ፡እጅ፡እስራኤልን፡ከግብጽ፡አወጣ፥በነቢይም፡እጅ፡ጠበቀው።

15ኤፍሬም፡አስመርሮ፡አስቈጣው፤ስለዚህ፥ደሙ፡በላዩ፡ላይ፡ነው፤ጌታውም፡ስድቡን፡በራሱ፡ላይ፡ ይመልሳል።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source