1የእስራኤልም፡ልጆች፡ቍጥር፡እንደማይሰፈርና፡እንደማይቈጠር፡እንደ፡ባሕር፡አሸዋ፡ይኾናል፤እንዲህም፡ ይኾናል፤እናንተ፡ሕዝቤ፡አይደላችኹም፡ተብሎ፡በተነገረበት፡በዚያ፡ስፍራ፡የሕያው፡አምላክ፡ልጆች፡ይባላሉ።
2የይሁዳ፡ልጆችና፡የእስራኤል፡ልጆች፡በአንድነት፡ይሰበሰባሉ፥ለእነርሱም፡አንድ፡አለቃ፡ ይሾማሉ፥ከምድሪቱም፡ይወጣሉ፤የኢይዝራኤል፡ቀን፡ታላቅ፡ይኾናልና።
3ወንድሞቻችኹን፦ዓሚ፥እኅቶቻችኹንም፦ሩሃማ፡በሏቸው።
4እናታችኹ፡ሚስቴ፡አይደለችምና፥እኔም፡ባሏ፡አይደለኹምና፡ተሟገቱ፤ከእናታችኹ፡ጋራ፡ ተሟገቱ።ግልሙትናዋን፡ከፊቷ፥ምንዝርናዋንም፡ከጡቶቿ፡መካከል፡ታስወግድ፤
5ዕራቍቷን፡እንዳልገፋ፟ት፥እንደተወለደችበትም፡ቀን፡እንዳላደርጋት፥እንደ፡ምድረ፡በዳና፡እንደ፡ደረቅ፡ ምድር፡እንዳላደርጋት፥በጥማትም፡እንዳልገድላት፤
6የግልሙትናዋ፡ልጆች፡ናቸውና፥ልጆቿን፡አልምርም።
7እናታቸው፡አመንዝራለች፤የፀነሰቻቸውም፦እንጀራዬንና፡ውሃዬን፥ጥጤንና፡የተልባ፡እግሬን፥ዘይቴንና፡ መጠጤን፡ከሚሰጡኝ፡ከውሽማዎቼ፡በዃላ፡እኼዳለኹ፡ብላ፡አስነወረቻቸው።
8ስለዚህ፥እንሆ፥መንገድሽን፡በሾኽ፡እዘጋለኹ፥መንገዷንም፡እንዳታገኝ፡ቅጥርን፡እቀጥርባታለኹ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
9ውሽማዎቿንም፡ትከተላለች፥ነገር፡ግን፥አትደርስባቸውም፤ትፈልጋቸውማለች፥ነገር፡ ግን፥አታገኛቸውም፤ርሷም፦ከዛሬ፡ይልቅ፡የዚያን፡ጊዜ፡ይሻለኝ፡ነበርና፥ተመልሼ፡ወደቀደመው፡ባሌ፡ እኼዳለኹ፡ትላለች።
10ርሷም፡እኽልንና፡ወይንን፡ጠጅ፡ዘይትንም፡የሰጠዃት፥ለበዓልም፡የተሠራውን፡ብርና፡ወርቅ፡ያበዛኹላት፡ እኔ፡እንደ፡ኾንኹ፡አላወቀችም።
11ስለዚህ፥እኽሌን፡በጊዜዋ፥ወይን፡ጠጄንም፡በወረቷ፡እወስዳለኹ፥ዕራቍትነቷንም፡እንዳትሸፍን፡ጥጤንና፡ የተልባ፡እግሬን፡እገፋ፟ታለኹ።
12አኹንም፡ውሽማዎቿ፡እያዩ፡ነውሯን፡እገልጣለኹ፤ከእጄም፡ማንም፡አያድናትም።
13ደስታዋንም፡ዅሉ፥በዓላቷንም፥መባቻዎቿንም፥ሰንበቶቿንም፥የተቀደሱትንም፡ጉባኤዎችን፡ዅሉ፡ አስቀራለኹ።
14ርሷም፦ውሽማዎቼ፡የሰጡኝ፡ዋጋዬ፡ይህ፡ነው፡ያለችውን፡ወይኗንና፡በለሷን፡አጠፋለኹ፤ዱርም፡ አደርገዋለኹ፥የምድረ፡በዳም፡አራዊት፡ይበሉታል።
15እኔን፡ረስታ፡ውሽማዎቿን፡እየተከተለች፥በጕትቾቿና፡በጌጧም፡እያጌጠች፡ለበዓሊም፡ያጠነችበትን፡ ወራት፡እበቀልባታለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር።
16ስለዚህ፥እንሆ፥አባብላታለኹ፥ወደ፡ምድረ፡በዳም፡አመጣታለኹ፥ለልቧም፡እናገራለኹ።
17ከዚያም፡የወይን፡ቦታዋን፥የተስፋ፡በርም፡እንዲኾንላት፡የዐኮርን፡ሸለቆ፡እሰጣታለኹ፤በዚያም፡ከግብጽ፡ ምድር፡እንደ፡ወጣችበት፡ቀን፡እንደ፡ሕፃንነቷ፡ወራት፡ትዘምራለች።
18በዚያ፡ቀን፡ባሌ፡ብለሽ፡ትጠሪኛለሽ፡እንጂ፡ዳግመኛ፡በኣሌ፡ብለሽ፡አትጠሪኝም፥ይላል፡እግዚአብሔር፤
19የበዓሊምን፡ስም፡ከአፏ፡አስወግደዋለኹና፥በስማቸውም፡እንግዲህ፡አይታሰቡምና።
20በዚያም፡ቀን፡ከምድር፡አራዊትና፡ከሰማይ፡ወፎች፡ከመሬትም፡ተንቀሳቃሾች፡ጋራ፡ቃል፡ኪዳን፡ አደርግላቸዋለኹ፤ቀስትንና፡ሰይፍን፡ሰልፍንም፡ከምድሩ፡እሰብራለኹ፥ተከልለውም፡እንዲኖሩ፡አስተኛቸዋለኹ።
21ለዘለዓለምም፡ለእኔ፡እንድትኾኚ፡ዐጭሻለኹ፤በጽድቅና፡በፍርድ፡በምሕረትና፡በርኅራኄ፡ዐጭሻለኹ።
22ለኔም፡እንድትኾኚ፡በመታመን፡ዐጭሻለኹ፤አንቺም፡እግዚአብሔርን፡ታውቂያለሽ።
23በዚያንም፡ቀን፡እመልሳለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር፤ለሰማይ፡እመልሳለኹ፥ሰማይም፡ለምድር፡ይመልሳል፤
24ምድርም፡ለእኽልና፡ለወይን፡ጠጅ፡ለዘይትም፡ትመልሳለች፤እነርሱም፡ለኢይዝራኤል፡ይመልሳሉ።
25በምድርም፡ላይ፡ለእኔ፡እዘራታለኹ፤ምሕረትም፡የሌላትን፡እምራለኹ፥ሕዝቤም፡ያልኾነውን፦አንተ፡ ሕዝቤ፡ነኽ፡እለዋለኹ፤ርሱም፦አንተ፡አምላኬ፡ነኽ፡ይለኛል።