Skip to content
← Hosea

Chapter 3 · Amharic

Hosea

1እግዚአብሔርም፦የእስራኤል፡ልጆች፡ወደ፡ሌላዎች፡አማልክት፡ቢመለሱና፡የዘቢብ፡ጥፍጥፍን፡ቢወዱ፡ እንኳ፥እግዚአብሔር፡እንደሚወዳቸው፡አንተም፡ውሽማዋን፡የምትወደ፟ውን፡አመንዝራዪትን፡ሴት፡ውደድ፡ አለኝ።

2እኔም፡በዐሥራ፡ዐምስት፡ብርና፡ባንድ፡ቆሮስ፡መስፈሪያ፡ተኩል፡ገብስ፡ገዛዃት።

3ከእኔ፡ጋራ፡ብዙ፡ወራት፡ተቀመጪ፥አታመንዝሪም፥ለሌላ፡ሰውም፡አትኹኚ፤እኔም፡እንዲሁ፡ እኾንልሻለኹ፡አልዃት።

4የእስራኤል፡ልጆች፡ያለንጉሥና፡ያለአለቃ፥ያለመሥዋዕትና፡ያለዐምድ፥ያለኤፉድና፡ያለተራፊም፡ብዙ፡ ወራት፡ይቀመጣሉና፤ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

5ከዚያም፡በዃላ፡የእስራኤል፡ልጆች፡ተመልሰው፡አምላካቸውን፡እግዚአብሔርንና፡ንጉሣቸውን፡ዳዊትን፡ ይፈልጋሉ፤በዃለኛውም፡ዘመን፡ፈርተው፡ወደ፡እግዚአብሔርና፡ወደ፡በረከቱ፡ይመጣሉ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source