Skip to content
← Hosea

Chapter 5 · Amharic

Hosea

1ካህናት፡ሆይ፥ይህን፡ስሙ፤የእስራኤል፡ቤት፡ሆይ፥አድምጡ፤የንጉሥ፡ቤት፡ሆይ፥ልብ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org አድርጉ፤በምጽጳ፡ላይ፡ወጥመድ፥በታቦርም፡ላይ፡የተዘረጋ፡አሽክላ፡ኾናችዃልና፥ፍርድ፡በእናንተ፡ላይ፡ ነው።

2ዐመፀኛዎችም፡ዕርድ፡አብዝተዋል፤እኔ፡ግን፡እነዚያን፡ዅሉ፡እዘልፋለኹ።

3ኤፍሬምን፡ዐውቀዋለኹ፥እስራኤልም፡ከእኔ፡አልተሰወረም፤ኤፍሬም፡ሆይ፥ዛሬ፡ አመንዝረኻል፥እስራኤልም፡ረክሷል።

4ወደ፡አምላካቸው፡ይመለሱ፡ዘንድ፡ሥራቸውን፡አላቀኑም፤የግልሙትና፡መንፈስ፡በውስጣቸው፡ አለና፤እግዚአብሔርንም፡አላወቁምና።

5የእስራኤልም፡ትዕቢት፡በፊቱ፡ይመሰክራል፤ስለዚህ፥እስራኤልና፡ኤፍሬም፡በኀጢአታቸው፡ ይሰናከላሉ፤ይሁዳም፡ደግሞ፡ከነሱ፡ጋራ፡ይሰናከላል።

6እግዚአብሔርንም፡ለመሻት፡በጎቻቸውንና፡ላሞቻቸውን፡ነድተው፡ይኼዳሉ፤ነገር፡ግን፥ርሱ፡ከነርሱም፡ ተመልሷልና፥አያገኙትም።

7ዲቃላዎችን፡ልጆች፡ወልደዋልና፥እግዚአብሔርን፡ወንጅለዋል፤አኹንም፡አንድ፡ወር፡እነርሱንና፡ ርስታቸውን፡ይበላቸዋል።

8በጊብዓ፡መለከትን፥በራማ፡እንቢልታን፡ንፉና፦ብንያም፡ሆይ፥ከአንተ፡በዃላ፥እያላችኹ፡በቤትአዌን፡ ላይ፡እሪ፡በሉ።

9ኤፍሬም፡በዘለፋ፡ቀን፡የፈረሰ፡ይኾናል።በእስራኤል፡ነገዶች፡ዘንድ፡በርግጥ፡የሚኾነውን፡ነገር፡ ገልጫለኹ።

10የይሁዳ፡አለቃዎች፡ድንበርን፡እንደሚነቅሉ፡ኾነዋል፤እኔም፡መዓቴን፡እንደ፡ውሃ፡አፈስ፟ባቸዋለኹ።

11ኤፍሬም፡ከትእዛዝ፡በዃላ፡መኼድን፡ወዷ፟ልና፥የተገፋና፡በፍርድ፡የተጐዳ፡ኾኗል።

12እኔም፡ለኤፍሬም፡እንደ፡ብል፥ለይሁዳም፡ቤት፡እንደ፡ነቀዝ፡ኾኛለኹ።

13ኤፍሬምም፡ደዌውን፥ይሁዳም፡ቍስሉን፡ባየ፡ጊዜ፡ኤፍሬም፡ወደ፡አሶር፡ኼደ፡ወደ፡ንጉሡም፡ወደ፡ ኢያሪም፡መልእክተኛን፡ላከ፤ርሱ፡ግን፡ይፈውሳችኹ፡ዘንድ፥ከቍስላችኹም፡ያድናችኹ፡ዘንድ፡አልቻለም።

14እኔም፡ለኤፍሬም፡እንደ፡አንበሳ፥ለይሁዳም፡ቤት፡እንደ፡አንበሳ፡ደቦል፡እኾናለኹና፤እኔም፡ነጥቄ፡ እኼዳለኹ፡እወስድማለኹ፥የሚያድንም፡አይገኝም።

15በደላቸውንም፡እስኪያውቁ፡ድረስ፥ፊቴንም፡እስኪሹ፡ድረስ፡ኼጄ፡ወደ፡ስፍራዬ፡ እመለሳለኹ፤በመከራቸው፡ጊዜ፡እጅግ፡አድርገው፡ፊቴን፡ይፈልጋሉ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source