Skip to content
← Hosea

Chapter 6 · Amharic

Hosea

1ኑ፥ወደ፡እግዚአብሔር፡እንመለስ፤ርሱ፡ሰብሮናልና፥ርሱም፡ይፈውሰናል፤ርሱ፡መቶ፟ናል፥ርሱም፡ ይጠግነናል።

2ከኹለት፡ቀን፡በዃላ፡ያድነናል፤በሦስተኛውም፡ቀን፡ያስነሣናል፥በፊቱም፡በሕይወት፡እንኖራለን።

3እንወቅ፤እናውቀውም፡ዘንድ፡እግዚአብሔርን፡እንከተል፤እንደ፡ወገግታም፡ተዘጋጅቶ፡እናገኘዋለን፤እንደ፡ ዝናብም፡ምድርንም፡እንደሚያጠጣ፡እንደ፡መጨረሻ፡ዝናብ፡ይመጣል።

4ምሕረታችኹ፡እንደ፡ማለዳ፡ደመና፥በማለዳም፡እንደሚያልፍ፡ጠል፡ነውና፥ኤፍሬም፡ሆይ፥ምን፡ ላድርግልኽ፧ይሁዳ፡ሆይ፥ምን፡ላድርግልኽ፧

5ስለዚህ፥በነቢያት፡እጅ፡ቈረጥዃቸው፥በአፌም፡ቃል፡ገደልዃቸው፤ፍርዴም፡እንደ፡ብርሃን፡ይወጣል።

6ከመሥዋዕት፡ይልቅ፡ምሕረትን፥ከሚቃጠልም፡መሥዋዕት፡ይልቅ፡እግዚአብሔርን፡ማወቅ፡እወዳለኹና። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

7እነርሱ፡ግን፡እንደ፡አዳም፡ቃል፡ኪዳንን፡ተላልፈዋል፤በዚያም፡ላይ፡ወንጅለውኛል።

8ገለዓድ፡ኀጢአትን፡የሚሠሩ፡ሰዎች፡ከተማ፥በደምም፡የተቀባ፡ነው።

9ለሰውም፡እንደሚያደቡ፡ወንበዴዎች፥እንዲሁ፡የካህናት፡ወገኖች፡በሴኬም፡መንገድ፡ላይ፡ ይገድላሉ፤ሴሰኝነትንም፡ያደርጋሉ።

10በእስራኤል፡ቤት፡የሚያስፈራን፡ነገር፡አይቻለኹ፤በዚያ፡በኤፍሬም፡ውስጥ፡ግልሙትና፡ ተገኘ፥እስራኤልም፡ረክሷል።

11ይሁዳ፡ሆይ፥የሕዝቤን፡ምርኮ፡በምመልስበት፡ጊዜ፡ለአንተ፡ደግሞ፡መከር፡ተወስኖልኻል።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source