Skip to content
← Hosea

Chapter 9 · Amharic

Hosea

1እስራኤል፡ሆይ፥ከአምላክኽ፡ተለይተኽ፡አመንዝረኻልና፥እንደ፡አሕዛብ፡ደስ፡አይበልኽ፥ሐሴትንም፡ አታድርግ፤በእኽሉ፡ዐውድማ፡ዅሉ፡ላይ፡የግልሙትናን፡ዋጋ፡ወደ፟ኻል።

2ዐውድማውና፡መጥመቂያው፡አይመግባቸውም፥ጕሽ፡ጠጅም፡ይጐድልባታል።

3በእግዚአብሔር፡ምድር፡ላይ፡አይቀመጡም፤ኤፍሬምም፡ወደ፡ግብጽ፡ይመለሳል፥በአሶርም፡ርኩስን፡ነገር፡ ይበላሉ።

4ለእግዚአብሔርም፡የወይን፡ጠጅን፡ቍርባን፡አያፈሱ፟ም፥መሥዋዕታቸውም፡ደስ፡አያሠኘውም፤የሐዘንም፡ እንጀራ፡ይኾንላቸዋል፥የሚበላውም፡ዅሉ፡ይረክሳል፤እንጀራቸውም፡ለሰውነታቸው፡ይኾናል፡እንጂ፡ ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡አይገባም።

5በዓመት፡በዓል፡ቀንና፡በእግዚአብሔር፡በዓል፡ቀን፡ምን፡ታደርጋላችኹ፧

6እንሆ፥ከጥፋት፡ሸሽተው፡ኼዱ፥ግብጽም፡ትሰበስባቸዋለች፥ሜምፎስም፡ትቀብራቸዋለች፤ሳማም፡ የብራቸውን፡ጌጥ፡ይወርሳል፥ሾኽም፡በድንኳኖቻቸው፡ውስጥ፡ይበቅላል። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

7የበቀል፡ወራት፡መጥቷል፥የፍዳም፡ወራት፡ደርሷል፥እስራኤልም፡ያውቃል፤ከኀጢአትኽና፡ከጠላትነትኽ፡ ብዛት፡የተነሣ፡ነቢዩ፡ሰንፏል፥መንፈስም፡ያለበት፡ሰው፡አብዷል።

8ኤፍሬም፡ከአምላኬ፡ጋራ፡ተመልካች፡ነበረ፤አኹን፡ግን፡ነቢዩ፡በመንገዱ፡ዅሉ፡ላይ፡የወፍ፡ወጥመድ፡ ኾነ፥በአምላኩም፡ቤት፡ጠላትነት፡አለ።

9በጊብዓ፡ዘመን፡እንደ፡ነበረ፡እጅግ፡ረከሱ፤ርሱም፡በደላቸውን፡ያስባል፥ኀጢአታቸውንም፡ይበቀላል።

10እስራኤልን፡በምድረ፡በዳ፡እንዳለ፡ወይን፡ኾኖ፡አገኘኹት፤አባቶቻችኹንም፡ከመዠመሪያዋ፡ዓመት፡ እንደ፡በለስ፡በኵራት፡ኾነው፡አየዃቸው፤እነርሱ፡ግን፡ወደ፡ብዔልፌጎር፡መጡ፥ለነውርም፡ተለዩ፥እንደ፡ ወደዱትም፡ርኩስ፡ኾኑ፥

11የኤፍሬምም፡ክብር፡እንደ፡ወፍ፡በሮ፟፡ይጠፋል፤መውለድና፡መፅነስ፡ማርገዝም፡አይኾንላቸውም።

12ልጆቻቸውንም፡ቢያሳድጉ፡ሰው፡እንዳይቀርላቸው፡ልጅ፡አልባ፡አደርጋቸዋለኹ፤ከነርሱም፡በራቅኹ፡ጊዜ፡ ወዮላቸው!

13እኔ፡እንዳየኹ፡የኤፍሬም፡ልጆች፡ለምርኮ፡ተሰጥተዋል፤ኤፍሬምም፡ልጆቹን፡ወደ፡ገዳዩች፡ያወጣል።

14አቤቱ፥ስጣቸው፤ምን፡ትሰጣቸዋለኽ፧የሚጨነግፍን፡ማሕፀን፡የደረቀውንም፡ጡት፡ስጣቸው።

15ክፋታቸው፡ዅሉ፡በገልገላ፡አለ፤በዚያ፡ጠልቻቸዋለኹ፤ስለሠሩት፡ክፋት፡ከቤቴ፡ አሳድዳቸዋለኹ፤ከእንግዲህ፡ወዲያ፡አልወዳቸውም፤አለቃዎቻቸው፡ዅሉ፡ዐመፀኛዎች፡ናቸው።

16ኤፍሬም፡ተመታ፥ሥሩም፡ደረቀ፥ፍሬም፡አያፈራም፤ደግሞም፡ቢወልዱ፡የማሕፀናቸውን፡ፍሬ፡ እገድላለኹ።

17አልሰሙትምና፡አምላኬ፡ይጥላቸዋል፤በአሕዛብም፡መካከል፡ተቅበዝባዦች፡ይኾናሉ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source