2መበለቶችም፡ቅሚያቸው፡እንዲኾኑ፥ድኻ፡አደጎችንም፡ብዝበዛቸው፡እንዲያደርጉ፥የድኻውን፡ፍርድ፡ ያጣምሙ፡ዘንድ፥የችግረኛውንም፡ሕዝቤን፡ፍርድ፡ያጐድሉ፡ዘንድ፡የግፍን፡ትእዛዛት፡ለሚያዙ፟፥ክፉንም፡ ጽሕፈት፡ለሚጽፉ፡ወዮላቸው!
3በተጐበኛችኹበት፡ቀን፥መከራም፡ከሩቅ፡በሚመጣበት፡ዘመን፡ምን፡ታደርጉ፡ይኾን፧ለረድኤትስ፡ወደ፡ ማን፡ትሸሻላችኹ፧ክብራችኹንስ፡ወዴት፡ትተዉታላችኹ፧
4ከእስረኛዎች፡በታች፡ይጐ፟ነበሳሉ፥ከተገደሉትም፡በታች፡ይወድቃሉ።በዚህም፡ዅሉ፡እንኳ፡ቍጣው፡ አልተመለሰችም፥ነገር፡ግን፥እጁ፡ገና፡ተዘርግታ፡ትኖራለች።
5ለቍጣዬ፡በትር፡ለኾነ፥የመዓቴም፡ጨንገር፡በእጁ፡ላለ፟፡ለአሶር፡ወዮለት!
6ርሱንም፡በዝንጉ፡ሕዝብ፡ላይ፡እልካለኹ፥ምርኮውንና፡ብዝበዛውንም፡ይወስድ፡ዘንድ፡እንደ፡አደባባይም፡ ጭቃ፡የተረገጡ፡ያደርጋቸው፡ዘንድ፡በምቈጣቸው፡ሰዎች፡ላይ፡አዘ፟ዋለኹ።
7ርሱ፡እንዲሁ፡አያስብም፥በልቡም፡እንዲህ፡አይመስለውም፤ነገር፡ግን፥ማጥፋት፥ጥቂት፡ያይደሉትንም፡ አሕዛብን፡መቍረጥ፡በልቡ፡አለ።
8እንዲህ፡ይላል፦መሳፍንቴ፡ዅሉ፡ነገሥታት፡አይደሉምን፧
9ካልኖ፡እንደ፡ከርከሚሽ፡አይደለችምን፧ሐማትስ፡እንደ፡አርፋድ፡አይደለችምን፧ሰማርያስ፡እንደ፡ደማስቆ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org አይደለችምን፧
10የተቀረጹ፡ምስሎቻቸው፡ከኢየሩሳሌምና፡ከሰማርያ፡ምስሎች፡የበለጡትን፡የጣዖቶችን፡መንግሥታት፡እጄ፡ እንዳገኘች፥
11በሰማርያና፡በጣዖቶቿም፡እንዳደረግኹ፥እንዲሁስ፡በኢየሩሳሌምና፡በጣዖቶቿ፡አላደርግምን፧
12ስለዚህ፥እንዲህ፡ይኾናል፤ጌታ፡ሥራውን፡ዅሉ፡በጽዮን፡ተራራና፡በኢየሩሳሌም፡ላይ፡በፈጸመ፡ጊዜ፡ የአሶርን፡ንጉሥ፡የኵሩ፡ልብ፡ፍሬን፡የዐይኑንም፡ከፍታ፡ትምክሕት፡ይጐበኛል።
13ርሱ፡እንዲህ፡ብሏልና፦አስተዋይ፡ነኝና፡በእጄ፡ኀይልና፡በጥበቤ፡አደረግኹት፤የአሕዛብን፡ድንበሮች፡ አራቅኹ፥ሀብታቸውንም፡ዘረፍኹ፥እንደ፡ዠግናም፡ኾኜ፡በምድር፡የተቀመጡትን፡አዋረድኹ፤
14እጄም፡የአሕዛብን፡ኀይል፡እንደ፡ወፍ፡ቤት፡አገኘች፤የተተወም፡ዕንቍላል፡እንደሚሰበሰብ፡እንዲሁ፡ እኔ፡ምድርን፡ዅሉ፡ሰበሰብኹ፤ክንፉን፡የሚያራግብ፡አፉንም፡የሚከፍት፡የሚጮኽም፡የለም።
15በእውኑ፡መጥረቢያ፡በሚቈርጥበት፡ሰው፡ላይ፡ይመካልን፧ወይስ፡መጋዝ፡በሚስበው፡ላይ፡ ይጓደዳልን፧ይህስ፥በትር፡የሚያነሣውን፡እንደ፡መነቅነቅ፡ዘንግም፡ዕንጨት፡ያይደለውን፡እንደ፡ማንሣት፡ ያኽል፡ነው።
16ስለዚህም፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡በወፍራሞች፡ላይ፡ክሳትን፡ይልካል፤ከክብሩም፡በታች፡ ቃጠሎው፡እንደ፡እሳት፡መቃጠል፡ይነዳ፟ል።
17የእስራኤልም፡ብርሃን፡እንደ፡እሳት፡ቅዱስም፡እንደ፡ነበልባል፡ይኾናል፤ሾኹንና፡ኵርንችቱን፡ባንድ፡ቀን፡ ያቃጥላል፡ይበላውማል።
18ከነፍስም፡እስከ፡ሥጋ፡ድረስ፡የዱሩንና፡የሚያፈራውን፡ዕርሻ፡ክብር፡ይበላል፤ይህም፡የታመመ፡ሰው፡ እንደሚሰለስል፡ይኾናል።
19የቀሩትም፡የዱር፡ዛፎች፡በቍጥር፡ጥቂት፡ይኾናሉ፥ታናሽ፡ብላቴናም፡ይጽፋቸው፡ዘንድ፡ይችላል።
20በዚያም፡ቀን፡እንዲህ፡ይኾናል፤የእስራኤል፡ቅሬታ፡ከያዕቆብም፡ቤት፡የዳኑት፡ከእንግዲህ፡ወዲህ፡ በመቷቸው፡ላይ፡አይደገፉም፤ነገር፡ግን፥በእስራኤል፡ቅዱስ፡በእግዚአብሔር፡ላይ፡በእውነት፡ይደገፋሉ።
21የያዕቆብም፡ቅሬታ፡ወደ፡ኀያል፡አምላክ፡ይምለሳሉ።
22እስራኤል፡ሆይ፥የሕዝብኽ፡ቍጥር፡እንደ፡ባሕር፡አሸዋ፡ቢኾን፡ቅሬታው፡ይመለሳል።ጽድቅ፡ የተትረፈረፈበትም፡ጥፋት፡ተወስኗል።
23የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔርም፡ያለቀ፡የተቈረጠ፡ነገርን፡በምድር፡ዅሉ፡መካከል፡ይፈጽማል።
24ስለዚህ፥የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦በጽዮን፡የምትኖር፡ሕዝቤ፡ሆይ፥አሶር፡በበትር፡ ቢመታኽ፥ግብጽም፡እንዳደረገ፡ዘንጉን፡ቢያነሣብኽ፥አትፍራው።
25ቍጣዬ፡እስኪፈጸም፡መዓቴም፡እስኪያጠፋቸው፡ድረስ፡ጥቂት፡ጊዜ፡ቀርቷልና።
26የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔርም፡ምድያምን፡በሔሬብ፡አለት፡በኩል፡እንደ፡መታው፡ጅራፍ፡ ያነሣበታል፤በትሩም፡በባሕር፡ላይ፡ይኾናል፥በግብጽም፡እንዳደረገ፡ያነሣዋል።
27በዚያም፡ቀን፡ሸክሙ፡ከጫንቃኽ፡ቀንበሩም፡ከዐንገትኽ፡ላይ፡ይወርዳል፤ቀንበሩም፡ከውፍረት፡የተነሣ፡ ይሰበራል።
28ወደ፡አንጋይ፡መጥቷል፤በመጌዶን፡በኩል፡ዐልፏል፤በማክማስ፡ውስጥ፡ዕቃውን፡አኑሯል፤
29በመተላለፊያ፡ዐልፏል፤በጌባ፡ማደሪያው፡ነው፤ራማ፡ደንግጣለች፤የሳኦል፡ጊብዓ፡ኰብላ፟ለች።
30አንቺ፡የጋሊም፡ልጅ፡ሆይ፥በታላቅ፡ድምፅሽ፡ጩኺ፤ላይሳ፡ሆይ፥አድምጪ፤ዐናቶት፡ ሆይ፥መልሽላት። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
31መደቤና፡ሸሽታለች፤በግቤርም፡የሚኖሩ፡ቤተ፡ሰቦቻቸውን፡አሽሽተዋል።
32ዛሬ፡በኖብ፡ይቆማል፤በጽዮን፡ሴት፡ልጅ፡ተራራ፡በኢየሩሳሌም፡ኰረብታ፡ላይ፡እጁን፡ያንቀሳቅሳል።
33እንሆ፥የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡ቅርንጫፎቹን፡በሚያስፈራ፡ኀይል፡ይቈርጣል፤በቁመት፡ የረዘሙትም፡ይቈረጣሉ፥ከፍ፡ያሉትም፡ይዋረዳሉ።
34ጭፍቅ፡የኾነውንም፡ዱር፡በብረት፡ይቈርጣል፥ሊባኖስም፡በኀያሉ፡እጅ፡ይወድቃል።