1ነገር፡ግን፥ተጨንቃ፡ለነበረች፡ጨለማ፡አይኾንም።በመዠመሪያው፡ዘመን፡የዛብሎንንና፡የንፍታሌምን፡ ምድር፡አቃለለ፤በዃለኛው፡ዘመን፡ግን፡በዮርዳኖስ፡ማዶ፡በባሕር፡መንገድ፡ያለውን፡የአሕዛብን፡ገሊላ፡ ያከብራል።
2በጨለማ፡የኼደ፡ሕዝብ፡ብርሃን፡አየ፤በሞት፡ጥላ፡አገርም፡ለኖሩ፡ብርሃን፡ወጣላቸው።
3ሕዝብን፡አብዝተኻል፥ደስታንም፡ጨምረኽላቸዋል፤በመከር፡ደስ፡እንደሚላቸው፥ሰዎችም፡ምርኮን፡ ሲካፈሉ፡ደስ፡እንደሚላቸው፡በፊትኽ፡ደስ፡ይላቸዋል።
4በምድያም፡ጊዜ፡እንደ፡ኾነ፡የሸክሙን፡ቀንበር፡የጫንቃውንም፡በትር፡የአስጨናቂውንም፡ዘንግ፡ሰብረኻል።
5የሚረግጡ፡የሰልፈኛዎች፡ጫማ፡ዅሉ፥በደምም፡የተለወሰ፡ልብስ፡ለቃጠሎ፡ይኾናል፥እንደ፡እሳት፡ ማቃጠያም፡ኾኖ፡ይቃጠላል።
6ሕፃን፡ተወልዶልናልና፥ወንድ፡ልጅም፡ተሰጥቶናልና፤አለቅነትም፡በጫንቃው፡ላይ፡ይኾናል፤ስሙም፡ ድንቅ፡መካር፥ኀያል፡አምላክ፥የዘለዓለም፡አባት፥የሰላም፡አለቃ፡ተብሎ፡ይጠራል።
7ከዛሬ፡ዠምሮ፡እስከ፡ዘለዓለም፡ድረስ፡በፍርድና፡በጽድቅ፡ያጸናውና፡ይደግፈው፡ዘንድ፡በዳዊት፡ዙፋንና፡ በመንግሥቱ፡ላይ፡አለቅነቱ፡ይበዛል፥ለሰላሙም፡ፍጻሜ፡የለውም።የእግዚአብሔር፡ቅንአት፡ይህን፡ያደርጋል።
8ጌታ፡በያዕቆብ፡ላይ፡ቃልን፡ሰደደ፥በእስራኤልም፡ላይ፡ወደቀ።
10በትዕቢትና፡በልብ፡ኵራት፦ጡቡ፡ወድቋል፥ነገር፡ግን፥በተወቀረ፡ድንጋይ፡እንሠራለን፤የሾላ፡ ዛፎች፡ተቈርጠዋል፥ነገር፡ግን፥ዝግባን፡እንተካባቸዋለን፡የሚሉ፡በኤፍሬምና፡በሰማርያ፡የሚኖሩ፡ሕዝብ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ዅሉ፡ያውቃሉ።
11ስለዚህ፥እግዚአብሔር፡በጽዮን፡ተራራ፡ላይ፡ተቋቋሚ፡ያስነሣበታል፥
12ጠላቶቹን፡ሶርያውያንንም፡ከምሥራቅ፥ፍልስጥኤማውያንንም፡ከምዕራብ፡ያንቀሳቅስበታል፤እስራኤልንም፡ በተከፈተ፡አፍ፡ይበሉታል።በዚህም፡ዅሉ፡እንኳ፡ቍጣው፡አልተመለሰችም፥ነገር፡ግን፥እጁ፡ገና፡ተዘርግታ፡ ትኖራለች።
13ሕዝቡ፡ግን፡ወደቀሠፋቸው፡አልተመለሱም፥የሰራዊትንም፡ጌታ፡እግዚአብሔርን፡አልፈለጉም።
14ስለዚህ፥እግዚአብሔር፡ራስና፡ዥራትን፥የሰሌኑን፡ቅርንጫፍና፡እንግጫውን፡ባንድ፡ቀን፡ከእስራኤል፡ ይቈርጣል።
15ሽማግሌውና፡ከበርቴው፡ርሱ፡ራስ፡ነው፤በሐሰትም፡የሚያስተምር፡ነቢይ፡ርሱ፡ዥራት፡ነው።
16ይህን፡ሕዝብ፡የሚመሩ፡ያስቷቸዋል፤ተመሪዎቹም፡ይጠፋሉ።
17ሰው፡ዅሉ፡ዝንጉና፡ክፉ፡ሠሪ፡ነውና፥አፍም፡ዅሉ፡ስንፍናን፡ይናገራልና፥ስለዚህ፡ጌታ፡ በጕልማሳዎቻቸው፡ደስ፡አይለውም፥ለድኻ፡አደጎቻቸውና፡ለመበለቶቻቸውም፡አይራራም።በዚህም፡ዅሉ፡ እንኳ፡ቍጣው፡አልተመለሰችም፥ነገር፡ግን፥እጁ፡ገና፡ተዘርግታ፡ትኖራለች።
18ክፋት፡እንደ፡እሳት፡ይቃጠላል፤ኵርንችቱንና፡ሾኹን፡ይበላል፤ጭፍቅ፡የኾነውንም፡ዱር፡ ያቃጥላል፥ጢሱም፡ተትጐልጕሎ፡እንደ፡ዐምድ፡ይወጣል።
19በሰራዊት፡ጌታ፡በእግዚአብሔር፡ቍጣ፡ምድር፡ተቃጥላለች፤ሕዝቡም፡እሳት፡እንደሚበላው፡ዕንጨት፡ ኾኗል፤ሰውም፡ለወንድሙ፡አይራራም።
20ሰው፡በቀኙ፡በኩል፡ይነቅላል፡ይራብማል፤በግራም፡በኩል፡ይበላል፡አይጠግብምም፤እያንዳንዱም፡ የክንዱን፡ሥጋ፡ይበላል፤
21ምናሴ፡ኤፍሬምን፡ኤፍሬምም፡ምናሴን፡ይበላል፤እነርሱ፡በአንድነት፡የይሁዳ፡ጠላቶች፡ይኾናሉ።በዚህም፡ ዅሉ፡እንኳ፡ቍጣው፡አልተመለሰችም፥ነገር፡ግን፥እጁ፡ገና፡ተዘርግታ፡ትኖራለች።