Skip to content
← Isaiah

Chapter 8 · Amharic

Isaiah

1እግዚአብሔርም፦ታላቅ፡ሰሌዳ፡ወስደኽ፦ምርኮ፡ፈጠነ፥ብዝበዛ፡ቸኰለ፡ብለኽ፡በሰው፡ፊደል፡ጻፍበት።

2የታመኑትን፡ሰዎች፡ካህኑን፡ኦርዮንና፡የበራክዩን፡ልጅ፡ዘካርያስን፡ምስክሮች፡አድርግልኝ፡አለኝ።

3ወደ፡ነቢዪቱም፡ቀረብኹ፤ርሷም፡ፀነሰች፡ወንድ፡ልጅንም፡ወለደች።

4እግዚአብሔርም፦ሕፃኑ፡አባቱንና፡እናቱን፡መጥራት፡ሳያውቅ፡የደማስቆን፡ሀብትና፡የሰማርያን፡ምርኮ፡ በአሶር፡ንጉሥ፡ፊት፡ይወስዳልና፥ስሙን፦ምርኮ፡ፈጠነ፥ብዝበዛ፡ቸኰለ፡ብለኽ፡ጥራው፡አለኝ።

5እግዚአብሔርም፡ደግሞ፡ተናገረኝ፡እንዲህም፡አለኝ።

6ይህ፡ሕዝብ፡በቀስታ፡የሚኼደውን፡የሰሊሖምን፡ውሃ፡ጠልቷልና፥ረአሶንንና፡የሮሜልዩንም፡ልጅ፡ ወዷ፟ልና፥ስለዚህ፥

7እንሆ፥እግዚአብሔር፡ብርቱና፡ብዙ፡የኾነውን፡የወንዝ፡ውሃ፥የአሶርን፡ንጉሥና፡ክብሩን፡ ዅሉ፥ያመጣባቸዋል፤መስኖውንም፡ዅሉ፡ሞልቶ፡ይወጣል፥በዳሩም፡ዅሉ፡ላይ፡ይፈሳ፟ል፤

8እየጐረፈም፡ወደ፡ይሁዳ፡ይገባል፤እያጥለቀለቀም፡ያልፋል፥እስከ፡ዐንገትም፡ይደርሳል፤ዐማኑኤል፡ ሆይ፥የክንፉ፡መዘርጋት፡የአገርኽን፡ስፋት፡ትሞላለች።

9አሕዛብ፡ሆይ፥ዕወቁና፡ደንግጡ፤እናንተም፡ምድራችኹ፡የራቀ፡ ዅሉ፥አድምጡ፤ታጠቁም፥ደንግጡ፤ታጠቁ፤ደንግጡ።

10ተመካከሩ፥ምክራችኹም፡ይፈታል፤ቃሉን፡ተናገሩ፥ቃሉም፡አይጸናም፤እግዚአብሔር፡ከእኛ፡ጋራ፡ነውና።

11እግዚአብሔርም፡በጽኑ፡እጅ፡እንዲህ፡ተናገረኝ፥በዚህም፡ሕዝብ፡መንገድ፡አንዳልኼድ፡ አስጠነቀቀኝ፥እንዲህም፡አለኝ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

12ይህ፡ሕዝብ፦ዱለት፡ነው፡በሚሉት፡ዅሉ፦ዱለት፡ነው፡አትበሉ፤መፈራታቸውንም፡ አትፍሩ፥አትደንግጡ።

13ነገር፡ግን፥የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔርን፡ቀድሱት፤የሚያስፈራችኹና፡የሚያስደነግጣችኹም፡ርሱ፡ ይኹን።

14ርሱም፡ለመቅደስ፡ይኾናል፤ነገር፡ግን፥ለኹለቱ፡ለእስራኤል፡ቤቶች፡ለዕንቅፋት፡ድንጋይና፡ለማሰናከያ፡ አለት፥በኢየሩሳሌምም፡ለሚኖሩ፡ለወጥመድና፡ለአሽክላ፡ይኾናል።

15ብዙዎችም፡በርሱ፡ይሰናከላሉ፥ይወድቁማል፥ይሰበሩማል፥ይጠመዱማል፥ይያዙማል።

16ምስክሩን፡እሰር፤በደቀ፡መዛሙርቴም፡መካከል፡ሕጉን፡ዐትም።

17ከያዕቆብም፡ቤት፡ፊቱን፡የመለሰውን፡እግዚአብሔርን፡እጠብቃለኹ፥እተማመንበትማለኹ።

18እንሆ፥እኔና፡እግዚአብሔር፡የሰጠኝ፡ልጆች፡ለእስራኤል፡በጽዮን፡ተራራ፡ከሚኖረው፡ከሰራዊት፡ጌታ፡ ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ምልክትና፡ተኣምራት፡ነን።

19እነርሱም፦የሚጮኹትንና፡ድምፃቸውን፡ዝቅ፡አድርገው፡የሚናገሩትን፡መናፍስት፡ጠሪዎችንና፡ ጠንቋዮችን፡ጠይቁ፡ባሏችኹ፡ጊዜ፥ሕዝቡ፡ከአምላኩ፡መጠየቅ፡አይገ፟ባ፟ውምን፧ወይስ፡ለሕያዋን፡ሲሉ፡ ሙታንን፡ይጠይቃሉን፧

20ወደ፡ሕግና፡ወደ፡ምስክር፡ኺዱ! እንዲህም፡ያለውን፡ቃል፡ባይናገሩ፡ንጋት፡አይበራላቸውም።

21እነርሱም፡ተጨንቀውና፡ተርበው፡ያልፋሉ፤በተራቡም፡ጊዜ፡ተቈጥተው፡ንጉሣቸውንና፡አምላካቸውን፡ ይረግማሉ፥ወደ፡ላይም፡ይመለከታሉ፤

22ወደ፡ምድርም፡ይመለከታሉ፥እንሆም፥መከራና፡ጨለማ፡የሚያስጨንቅም፡ጭጋግ፡አለ፤ወደ፡ድቅድቅም፡ ጨለማ፡ይሰደዳሉ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source